ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልማት ኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ድርጅቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት የተለያዩ የመንግስት ይዞታ የነበሩ ተቋማት በጥናት ለህዝብ ጥቅም የመሸጥ የመለወጥ ፤ ስልጣን ተሰጥትቶታል፡፡ ይህን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋች ሁኖብኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
እስካሁንም የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ፣ የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት፣ በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው ኦሞራቴ እርሻ ልማት በመንግስት አመራሮች ጫና በብዙ ሚሊየን ብር ኪሳራ ወደ ግል ተዛውሯል፡፡
በባለሃብቶች እጅ ባሉ ባለስልጣኖች ምክር የሚመነዘሩት የባለሃብቶች እና የባለስልጣናት ትስስር ለሰፊው የህዝብ ጥቅም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ኪስ የሚያደልቡ አሰራሮች መጠቀሚያ እንደሆነ ነው ያመለከቱት ፡፡
ካሁን በፊትም ፤ የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ ወደ ግል የተዛወረበት መንገድ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ነበር ፡፡
የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት በሊዝ ተሺጦ ያለ አግባብ በሚልየኖች የሚቆጠር ብር በአየር ላይ ባክኖ ቀርቱዋል፡፡ በዚህም ከ98 በላይ ቤተሰብ አሰተዳዳሪ ሰራተኛች ያለ የስራ ዋስትና ተብትነዋል፡፡
በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው የሚገኘው ሞራቴ እርሻ ልማት ያለበቂ ተመን ከተሸጡት ድርጅት መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ በስጦታ እንደ ተላለፈ የሚቆጠረው ይህ የኮሪያ ባለሃብቶች የልማት ፕሮጀክት ወደ ግለሰቦች ሲዛወር ከህግ እና አሰራር ቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ነው በማለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ለልማቱ የተገዙትን መኪናዎች ጨምሮ ከመሳሪያዎች ጋር ከ32 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ባለበት ሁኔታ፣ ከገበያ ዋጋ በታች በሆነ ሁኔታ ለሺያጭ ውሎዋል፡፡
ኤጅንሲው የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መቆጣጠር በአግባቡ የመስራት አቅሙን ያዳከመው የኢህአዴግ መንግስት ፣ ሸበሌ ትራንስፖርት ኮምቦልቻ ፤ ወይራን የመሳሰሉ ድርጅቶች ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፈው እንዲሰጡ ከባለስልጣናት በቃል በተላለፈ ትእዛዝ ያለማንም መስረጃ ለሶስተኛ ወገን ተላልፈው ተሰጥተዋል።
የሸበሌ ማዴአዎች ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፉ ከ 397 በላይ ተቀጣሪዎች ያለ ስራ ካሳ ወይም ምትክ የስራ ዋስትና ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
የየረር የዱቄት ፋብሪካ ተዘግቶ 41 ሰራተኛች ተፈናቅለው የስራ ዋስትና አጥተዋል፡፡ የሰራተኞች መብት እና ጥቅም እንዲሁም ውለታቸውን ባላከበረ ሁኔታ ተላልፈው ተሺጠዋል፡፡ የመንግስት ሃብቶች ወደ ግል ሲዛወሩ የሰራተኞችን መብት ባከበረ እና የስራ ዋስትናቸውን በተጠበቀ መካሄድ አለበት ቢልም ህጉ ሳይተገበር ቀርቱዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች በቁሳዊ እና የማህበራዊ ኪሳራ እንዲኖሩ መገደዳቸውን እና ልጆቻቸውን ለማስተማር እና በልቶ ለማደር አቅም እንዳጠራቸው ለዘጋቢያችን ግልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኤጀንሲው ወደ ግል እንዲዛወሩ በ ንግድ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ግብርና ሜካናይዜሽንና ግዮን ሆቴል ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ከሁለት ወራት በፊት በወጣው ጨረታ ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር ሌሎች ሦስት የመንግስት የልማት ድርጅቶችም የባሌና የአርሲ እርሻ ልማት ድርጅቶች፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎችና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለሽያጭ መቅረባቸው ይታወቃል፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታቸውን አየር ላይ እንዳለ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ሦስቱ ድርጅቶች እንዳይሸጡ በመወሰኑ ከጨረታ ሒደቱ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ሁለቱ ማለትም ባሌና አርሲ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ለኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ እንዲሁም የኮንስትራክሽንና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡
በ2004/5 በጀት አመት ጊዮን ሆቴል፣ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ፣ ቡና ቴክኖሎጂና ምህንድስና እንዲሁም የኢትዮጵያ ማእድን አክሲዮን ማህበር ወደ ግል የዛወራሉ ቢባልም ሳይሸጡ ቀርተዋል።
ቢሊቶ እርሻ ልማት፣ ሀማሬሳ የምግብ ዘይት አክሲዮን ማህበርና አርባ ጉጉ እርሻ ልማት በአዲስ ለጨረታ ከሚቀርቡ ድርጅቶች ውስጥ ሲካተቱ ፥ በሰኔ ወር መጨረሻ ለጨረታ ከቀረቡት ውስጥ የባቱ ኮንስትራክሽን ጨረታ ተሰርዞ በሌላ የመንግስት ድርጅት ስር እንዲተዳደር በቦርዱ መወሰኑን በኤጀንሲው የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ይናገራሉ።
ወደ ግል ሳይዛወሩ በመንግሥት እጅ ይቆያሉ የተባሉትና ኤጀንሲው ስትራቴጂክ ካላቸው ተቋማት መካከል የጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ)፣ ሙገር ሲማንቶ ፋብሪካ፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ድርጅት (ኢትፍሩት) ይገኙበታል፡፡
የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ቀደም ሲል በእጁ ላይ 287 ኢንተርፕይዞች ነበሩት፡፡ እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ 236 ኢንተርፕራይዞችን ለግል ካዛወረ በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት የቀሩት 51 የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ሃያዎቹን በ2005 ዓ.ም. ወደ ግል ለማዛወር አውጥቷል፡፡ ኤጀንሲው የመንግሥትን ኢንተርፕራይዞች በሽያጭ ወደ ግል ማስተላለፍ በጀመረበት በ1987 ዓ.ም. አምስት ኢንተርፕራይዞችን ብቻ ነበር ወደ ግል ያዛወረው፡፡ በቀጣዩ ዓመት እስከዛሬ ድረስ ክብረወሰን ሆነው የተመዘገቡትን 127 ኢንተርፕራይዞች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሽያጭ አስተላልፏል፡፡
ከፍተኛ ሙስና እንደተፈጸመባቸው በተነገረው በዚህ ሽያጭ፣ ግብር ከፋዩ ክብረተሰብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ለዘረፋ ተጋልጧል።
No comments:
Post a Comment