Dec 22, 2013
ከአምሳል ጊዮን
aberhanou@gmail.com
ያኔ በነዚያኛው ዘመን የሀገሬ ህዝብ የሀገር ያለህ የመንግስት ያለህ ብሎ ህዝቡን መንግስቱን ሲማፅን እና ሲጮህ አንገቱን ያላዞረ ህዝብም ሆነ መንግስት ያለ አይመስለኝም ። ያኔ ነው አሉ በሰንደቃላማው ወድቃ በተነሳችው ሲባል ወይ ፍንክች ነበር ፣ ግና ዛሬ ዛሬ የሰንደቃላማው እና የሀገር ፍቅር እንዳይገባን ሆነን ተወልደን፣ ያደግን የትውልድ ጭንጋፍ ሆነን ፣የትውልድ የኮመጠጠ ቡኮ ሆነን ሲጋገር የማየርባን ልምሻ ሆነን ፣የዘመኑ የመጨረሻ የሀገር ውራ ማፈርያ ሆነን የትውልድ ፈሪ ሆነን እስከ መቼ ነው???
ነገሩ እንዲ ነው ሀገር እንመራለን ባዮቹ ሀገሬውን ፈተሹት የፍርሀትን መንፈስ ብንረጭበት ሲሉ ተማከሩ አሉ ከዛም በፓርላማ ላይ ምላስ እንቆርጣለን ፣ጣት እንቆርጣለን ምንትስ ምንትስ አሉ ። በመቀጠል ህዝብ በሌላ ፖለትካ ሊደራጅ ቢፈልግ ቀደም ያሉትን የተቁሃሚ ፖለትካ እስረኞች የዕድሜ ልክ እስራት፣ ንብርት መውረስ አና የሞት ፍርድ በመፈርድ በህብረተሰቡ ላይ ፋርሃት (ሜንታል ቶርች ) አስቀድሞ እንደማስጠቀቅ አድርጎ ፍርሃት ለቀቁበት።ከአምሳል ጊዮን
aberhanou@gmail.com
ያኔ በነዚያኛው ዘመን የሀገሬ ህዝብ የሀገር ያለህ የመንግስት ያለህ ብሎ ህዝቡን መንግስቱን ሲማፅን እና ሲጮህ አንገቱን ያላዞረ ህዝብም ሆነ መንግስት ያለ አይመስለኝም ። ያኔ ነው አሉ በሰንደቃላማው ወድቃ በተነሳችው ሲባል ወይ ፍንክች ነበር ፣ ግና ዛሬ ዛሬ የሰንደቃላማው እና የሀገር ፍቅር እንዳይገባን ሆነን ተወልደን፣ ያደግን የትውልድ ጭንጋፍ ሆነን ፣የትውልድ የኮመጠጠ ቡኮ ሆነን ሲጋገር የማየርባን ልምሻ ሆነን ፣የዘመኑ የመጨረሻ የሀገር ውራ ማፈርያ ሆነን የትውልድ ፈሪ ሆነን እስከ መቼ ነው???
ከዚህም በተጨማሪ ቀን እና ማታ በሚያደነቁረን የቴሌቪዥን ጣቤያቸው ላይ ሲዳከር የዋልወና ጎኑን ለማሳረፍ እፎይ አንዳይል በሰንበት የመከላከያ በሚለው የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ ከዚህ በፊት ደርግ ይጠቀምበት የነበረውን የጦር አውሮፕላን የታንክና የመሳሪያ ዓይነቶች የጦሩን ብዛት አያሳዩን ልቡ እስጠኪፋ ያደክሙታል።
አሁንም እነዚህ መንግስት ነን ባዮቹ ተማከሩ አሉ፣ እንዴት ነው የህዝቡ ልብ ውስጥ ምን ተገኘ ? በፍርሃት ተሸበበ ወይ ? የለም ገና ነው ተባባሉ። በ1997 ምርጫ የነበረውን የህዝቡን ወኔና የልብልብ ስሜት ሰልቦ ፣ ፍርሀት በልቡ ወስጥ በማስፈር በየትምህርት ቤቱ ሳይቀር ተማሪው በጠመንጃ አፈሙዝ ነው ምንማረው እስኪል ድረስ ግራ አጋቡት፣ ለአዲስ አበባ ህዝብ በነብስወከፍ የፌደራል ፖሊስ ዘሩበት ሌላው ቀርቶ ከፍ ባል ድምፅ ካስነጠስክ ያቀምስሃል! ለምን? ትእዛዝ ነዋ። ጉድ በይ ሀገሬ ኢትዮጵያ አጆችዋን ወደ ጌታ ትዘረጋለች የሚለውን ቀየረው ወደመንግስት ለያስብሉን??? ዛሬ በሀገሬ ህዘብ ልብ ውስጥ ያለውን ማን ያውቃል ??? ንቃ የሀገሬ ሰው አምቢ በል!!
* እስመ አልቦ ለነገረ ወይስሐኖ ለ እግዚአብሄር *
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
No comments:
Post a Comment