Sunday, November 3, 2013

በሶማሊ ክልል የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአል ፌዝ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

በክልሉ ለረጅም አመታት ኖረው በተለያዩ ምክንያቶች ከአካባቢው እንዲለቁ የተደረጉ አንዳንድ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መስተዳድሩ እንኳንስ የሌሎችን አካባቢዎች ህዝብ መብት ለማክበር ቀርቶ የክልሉን ነዋሪዎች መብት ማክበር አልቻለም ብለዋል።

ከሌላ ክአካባቢዎች የመጡ በተለይም የአማራ ተወላጆች ሶማሊያ መናገር አትችሉም እየተባሉ ከስራ መባረራቸውን የገለጹት እኝህ ነዋሪዎች፣ በንግድ ስራ የሚተዳደሩና በጅጅጋ ቁልፍ የገበያ ቦታዎችን እና ቀበሌ ቤቶችን ይዘዋል የተባሉ  ቦታውን እንዲለቁና እንዲሰደዱ መደረጋቸውን አውስተዋል።
በአሁኑ ጊዜ ክልሉ የኢትዮጵያ አካል ነው ብሎ መናገር አይቻልም የሚሉት ነዋሪዎች፣ በሌሎች አካባቢ ሰዎች ከሚፈጸመው ግፍ ባልተናነሰ በአካባቢው ተወላጆች ላይ ይፈጸማል ብለዋል።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ይከበራል መባሉን በህዝብ ላይ እንደመቀለድ ይቆጠራል ሲሉ እነዚሁ ለደህንነታቸው የሰጉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment