Thursday, January 30, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት የግንቦት7 መሪዎችን ኮምፒዩተሮች በዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ሲሰልል እንደተደረሰበት አንድ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ

የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው  ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን ስፓይ በሚል ስም የሚጠራውን የመሰለያ መሳሪያ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ላሉ አገሮች በመሸጥ ዜጎች እንዲሰለሉና ደህንነታቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማድረጉ  ምርመራ እንዲጀመር” ሲል ጠይቋል።

የግንቦት7 ከፍተኛ አመራር በሆኑት በ ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግል ኮምፒዩተር ላይ የመሰለያ ቫይረሱ መገኘቱን በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የሙንክ ስኩል ግሎባል አፌርስ የምርምር ተቋም የሆነው ሲትዝን ላብ ማረጋገጡን ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል በደብዳቤው ገልጿል።
የመሰለያ መሳሪያው የሰብአዊ መብቶችን በሚጥሱ 36 አገራት ላይ መሸጡን የገለጸው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል፣ በተለይም በቬትናም፣ ማሌዚያና ኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለመሰለያነት እየዋለ ነው ብሎአል።
በኢትዮጵያ የግንቦት7 ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኮምፒተራቸው ሲሰለል መቆየቱን የገለጸው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል፣ በአንድ የብሃሬን የሰብአዊ መብት ተማጓች ኮምፒዩተር ላይም ተመሳሳይ የስለላ ሶፍት ዌር መገኘቱን ገልጿል።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለፕራይቪሴ ኢንተርናሽናል ጠበቃ የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። ፕራይቪሲ ኢንተርናሽናል የስለላ ቫይረሱን የሸጠውን ጋማ ኢንተርናሽናልን የተባለውን ድርጅት ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ማቀዱን ዶ/ር ታደሰ ገልጸዋል፡
ከዶ/ር ታደሰ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ከዜናው በሁዋላ ይቀርባል።
http://ethsat.com/amharic/

የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

January 29, 2014

ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ስላማዊ ስልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ስላማዊ ስልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የስማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታ የሚከተለውን ጽፏል፡
    “ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው … እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።”
ይህ በግልጽ የሚታየው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የስብዓዊ መብቶች አንጸባራቂ ሥዕል ነው። ይህ ሁኔታ በየቀኑ በተለያየ መልኩ ሀግሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለ የመንግሥት ሕገ ወጥነት ነው!
በኤኮኖሚው መስክ ያለው ችግር ግዙፍ ነው። ድህነት ከመቀረፍ ይልቅ፡ ሥር እየስደደ መሆኑን ብዙዎች ያማርራሉ። ለጥቂቶች ግን ሀገሪቱ ምድራዊ ገነት ሆናለች። ሕዝቡ እየተደበደበም፡ በየቀኑ አልዋጥ ባይ ፕሮፓጋንዳ በግድ እየተጋተ ነው!
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ለብዙዎቹ የአዲስ አበባ መሽቀርቀር እንደአጠቃላይ የሃገሪቱ የልማትና ዕድገት መለኪያ ተደርጎ እንዲወሰድ የተቀነባበረ ጥረት የሚድረገው። የምርጫ ዘመን በመቃረቡ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስንዴ ለውጭ ገብያ ሻጭ ልትሆን ነው በማለት ጥር 18፣ 2014 አርሲ ሆነው ማስማታቸው ልብ ሊባል ይገባል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በልማት ገና ሀ ሁ … ላይ ናት – በምግብ 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን በቀን ሶስቴ ሳይሆን፡ አንዴም መመገብ ያልቻለች አገር ናት! ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የምዕራቡ ዓለም፡ በቋሚነት ከ10 በመቶ በላይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክዓመት ዓመት በዓለም አቀፍ እህል ዕርዳታ ሕይወት በመስጠት ላይ ያለው?
ከሁሉም ጎልቶ የሚነገርለትና የሕወሃት ስዎችም ቶሎ የሚስፈነጠሩበት የአገሪቱ ከትላልቅ ጦርነቶች መላቀቋ ነው። ስለዚህም የሕወሃት ስዎችና ደጋፊዎቻቸው በመመጻደቅ ሲናገሩ መስማቱ የተለመደ ሆኖአል። በዚህም መነሻነት፡ እንዲህ ይላሉ: ባለፉት 20 ዓመታት፡ ሕወሃት ለረዥም ዘመናት አገሪቱን ያደሙትን ጦርነቶች አቁሞ ልማት ላይ እንድታተኩር አደረገ የሚባለው በብዛት ይሰማል። የሕወሃት ስዎችም ይህ በተደጋጋሚ እንዲነገርላቸው ብዙ ጥረቶች አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። እራሳቸውም በተደጋጋሚ እራሳቸውን በዚህ ሲያሞካሹ ይሰማል፤ ለውጭ የፕሮፓጋንዳ ድርጅቶችም ይህንን እንዲያስተጋቡላቸው፡ ከፍተኛ ክፍያዎችን በየጊዜው ፈጽመዋል።
እስከዛሬ አጥግቢ ግንዛቤ ያላገኘው ግን፡ ድሮም ሆነ ዛሬ የጦርነቶች አጋጋይ ሕወሃት መሆኑ ነው። የኤርትራንና የትግራይን መገንጠል ጉዞ በተግባር ሲተረጉም ኖረ። ቀኑ ደርሶ ጅብሃ ሲገነጠል፡ ሕወሃት ባዶ የሥልጣን ወንበር ስለታየው፡ ኢትዮጵያዊነትን መረጠ። በትግል አጋሩ ጅብሃ ዘንድ ይህ እንደክህደት እንዳይታበት – በስላም ሂዱ፡ ኢትዮጵያ ከእናነተ ስላም እንጂ ሌላው ቀርቶ የባህር በር እንኳ አያስፈልጋትም አለ። ይህንን አስመልከቶ፡ በየካቲት ወር 1994 ስብሃት ነጋ ለዓለምስገድ አባይ በስጡት ቃለ መጠይቅ የሕወሃት ቀደምት ፓሊሲ መገንጠል ሆኖ እስክ 1985 መቆየቱን ያረጋግጣሉ። ከቃለ መጠይቁ ውስጥ በጣም አሰገራሚው ነገር ግን፡ ብዙ የሕወሃት ተዋጊዎች ኢትዮጵያዊነትን ገና ድሮ አሽቀንጥርረው የጣሉ በምሆናቸው፡ ዛሬም ቢሆን በተለይ ከአማራ ጋር ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኝትን በሙል ልብ አለመቀበላቸውን ነው ያመላከቱት [See Identity Jilted: Re-imagined Identity (1998)]።
ያለፈው አልበቃ ብሎ፡ ዛሬም ሕወሃት ሀገሪቱ ውስጥ ሽብርና ፍርሃት በማንገስ የውስጥ ግጭቶችን በመተንኮስ: የተለያዩ ብሄረስቦችን አባሎች በማፈናቀልና ችግሮችን በማባባስ ተጠቃሚ ለመሆን ሲምክር ይታያል – ድ/ር ቴድሮስ ፍጹም “እኔ ያለሁበት ፓርቲ ውስጥ ይህ አይደረግም!” ብለው ዝናቸውን አጋልጠው ቢገዘቱም። ነገሩ ግን፡ ዛሬም በምሥራቅ በተለያያዩ የኦሮም ክፍሎችና ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች መካከል፡ በደቡብም እንዲሁ በተለያዩ ጎሣዎች መካከል፡ አማራንና ኦርሞችን በማጋጭት፡ ጥላቻና መቃቃርን በዜጎች መካከል ለመፍጠር ብዙ ሲሞክር ቆይቷል። አንዳንድ ቦታዎችም፡ ለምሳሌ ቦረና፡ ተሳክቶለት ስሞኑን የብዙ ዜጎች ደም ፈሷል፤ ሕይወትም ተቀጥፏል። ቤት ንብረቶችም ተደምስሰዋል። ሌላው ቀርቶ፡ የሕክምና ባለሙያ የነበሩት የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩ – የዛሬው የሃይማኖትች ጉዳይና የጸረሽብር ኤክስፐርቱ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም – ኬንያ በሥጋቷ ምክንያት (2012ን በማስታወስ) ልተቀስቅሳቸው ብትሞክርም፡ ነገሩ አውቆ የተኛ ቢነቀንቁት አይሰማ ሆኖ እሳችውም እንደክረምት ድብ ክፉኛ አሸልበዋል።
ለማንኛውም፡ በዓለም ላይ እንደሕወሃት የተሳካለት የለም – ዕድሉን ሃገራችንን ለማሻሻል በሚገባ አልተጠቀመበትም እንጂ! ስለሆነም ክሥራ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ፡ ዕውነትን ተናግሮ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት ይልቅ፡ ሁሉንም ስው ማሞኘት እንችላለን በሚል ትዕቢት ብዙ የሚያሳፍሩ ተግባሮች ሲያከናወን ይታያል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ በበጎነታችው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደጉን የሚመኙ የውጭዎቹ የፖለቲካ፡ የዲፕሎማሲና ኅብረተስባዊ መሻሻሎችን አራማጆች ይህንን የሕውሃትን የሰላም ማስፈን የዋህ መስል ቅጽል በአመኔታ የሚጋሩት በሁለት ተክፈለው ይታያሉ፡ –
(ሀ) በእውነትም ጦርነትና የንጹሃን ዕልቂት መቆሙን፡ ኢትዮጵያ ክድህነት ተላቅቃ ማየት የሚሹ ወገኖች፤
(ለ) ጊዘው የበለጸጉት ሃገሮች ወደታዳጊ ሀገሮች ውስጥ ዘልቀው በመስፋፋትና በኢኮኖሚ ትብብር ስም የራሳቸውን ኤኮኖሚያዊ፡ የበላይነት ማቆየት የሚሹበት፡ ፖለቲካዊና ስትራተጂካዊ ጥቅሞቻቸውን የሚያበራክቱበት በመሆኑ፡ ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተዳብረው፡ የሕወሃትን ገድል መተረኩ፡ ለሚሹት ዓላማ አንድ ጥቅም ትስስሮሽ መፍጠር የሚያስችል መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ወገኖችም እዚሀ ውስጥ ተስልፈዋል።
ከላይ የተመለከቱት ከተለያየ አግጣጫ ተነስተው ሁለቱም አንድ የሚገናኙበት መጋጠሚያ፡ ስለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንዲስተጋባ ማድረጋቸው ነው። በተለይም በሁለተኝው ክፍል የሚገኙት፡ በተቻለ መጠን ስለኢትዮጵያ በጎውን በማጋነን፡ የሕወሃትን የስብዓዊ መብቶች ጽልመት፡ ጎስኝነት፡ ሙሰኝነት የሚሸፋፍን አመለካከት በምዕራባውያንም ሆነ ምሥራቃዊ ሚዲያዎች ላይ በጊዜው ያስደስኮሩላቸዋል።
በተጨማሪም፡ እነዚህ ሀገሮች ለኢትዮጵያ ግዙፍ ዕርዳታ መፍሰሱን ይደግፋሉ። ነገር ግን ይህ ዕርዳታ በብዙ መስኮች – በተለይም በግብርናው – መስክ የሀገሪቱን ችግሮች፡ በምግብ ምርት እራስን ከማስቻል ይዘት ስሌለው፡ ትኩረታችውም ሆነ ጥረታቸው – በዘለቄታ ሀገሪቱን ከምግብ ዕርዳታ ተመጽዋች ነጻ ለማድረግ አላስቻለም። በመሆኑም፡ እየተደረገ ያለው፡ ትላንት እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያ አንድ ሶስተኛ መንግሥታዊ በጀቷን በዓለም አቀፍ ዕርዳታ ተመጽዋችነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ የውስጥና የውጭ ፖሊሲዋን በማክራየት እንድትቀጥል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮባታል።
በአሁኑ ወቅት፡ በተለያዩ ምክንያቶች (የስብዓዊ መብቶች አለመከበር ችግር፡ የየራሳቸው የሀገሮቹ የኢኮኖሚ ችግሮች) መንስኤነት፡ ከለጋሽ ሀገሮች በቀጥታ የሚገኝው ዕርዳታ በክፍተኛ ድረጃ ቀንሷል (ክአሜሪካና እንግሊዝ በስተቀር)። በዚህም ምክንያት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚስጠውን ብዙውን የዕርዳታና ብድር ጫና ድርሻ ተሸካሚ ሆኖአል።
ለምሳሌ፡ ሌላው ቀርቶ ስብዓዊ ዕርዳታን እንኳ በተመለከተ፡ 12 የአውሮፓ ኅብረት ሀገሮች (እንግሊዝን አይጭምርም) በ2012 ለኢትዮጵያ በባይላተራል መንገድ ለዕርዳታ ያዋጡት €24 ሚልዮን ሲሆን፡ በ2013 ይህ መዋጮ ወደ €12.4 ሚልዮን ወርዷል። ከነዚህም መካከል ትልቁን ቅናሽ ያደረገችው ጀርመን ናት – ከ€8.2 ሚልዮን ወ €4.2 ሚልዮን ዝቅ በማድረግ። በመሆኑም፡ከዚህም ከዚያም አስባስቦ የበጀት ምንጮች በማስባስብና ተጨማሪ ምክንያቶች በመፍጠር (ነፍስ ወክፈ መልሶ ማቋቋም) በ2013 እንዳደረገው፡ የአወሮፓ ኮሚሽን በ 2011-2013 12 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት እንዲቻል €130 ሚልዮን ለግሷል።
አሁን ለሁሉም ለጋሾች ከባድ የሆነው “የልማት” ዕርዳታውም እንዲሁ በበዙ ጥያቄዎች ላይ መውደቁ መሆኑ ይሰማል።
በዓለም ዙሪይ ያለፉው ሩብ ምዕተ ዓመት የልማት ጊዜ በመሆኑ፡ ብዙ ታዳጊ አገሮች ከፍተኛ ተጠቃሚ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ይህ ዕድል ቢገጥማትም፡ መሣሪያ ያነገቡት የሕወሃት ሰዎችና አጫፍሪዎቻቸው ግንባር ቀድም ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሥርዓት በመዘርጋቱ፡ የትላንቱ ጦረኞችና የዛሬዎቹ የስላም ደጋፊ-መስል የአንድ ብኄረስብ ሰዎች፡ ሆን ብለው ዕኩልነትን የሚጻረር የፖለቲካ፡ የኤኮኖሚ፡ የደህንነትና ማኅበራዊ ፓሊስዎችን በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ግን ዘላቂ መሠረት ስሌለው፡ ዛሬ የኤኮኖሚው የጥንድ ዕድገት ውደሳው ጋብ ብሎ፡ ሀገራችን የመንግሥት ብልግናና የሃስት ፕሮፓጋንዳ ከሚመገቡት መካክል ወድቃለች። በዚሁም ምክንያት (ሽፋኑ የውሃ ዕጥርረት፡ ድርቀት፡ የሃይማኖትና የብኄረቦች አለመቻቻልና ግጭቶች ላይ ቢመካኝም)፡ ተደጋጋሚ ዓለም አቅፍ ጥናቶችኢትዮጵያ ከሚወድቁት የአፍሪቃአገሮች (Failed States) መካከል ተደምራ፡ የወደፊት ጽዋዋ አስፈሪ እንደሚሆን ቀንደኛ ደጋፊዎቿ ድምዳሜ ላይ መሆናቸውን በግልጽ የምንሰማበት ዘመን ላይ ደርስናል።
ድሮስ ቢሆን፡ የሕዝብ ዓመኔታ ያጣ መንግሥት፡ መሣሪያውን ደግኖ በኅይል ለመግዛት ከመሞከር ውጭ ምን አማራጭ አለው? ጊዜው የጥላቻ፡ የክፋትና የቂም በቀል በመሆኑ፡ በአንድ በኩል፡ የሕወሃት ስዎች ዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፡ በሌላ በኩል ደግሞ፡ የኢትዮጵያውያንን ስብዓዊ መብቶች በመግፈፍና መርገጣቸውን በማባባስ፡ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ጎዳን እየገፉ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕድገት ይኖራል?
እንዲያውም፡ የራሱን የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም ሲል፡ የኢትዪጵያ ሕዝብ ፍላጎትና አመለካከት ሳይጠየቅ ኤርትራን በፊርማው እንድትገነጥል ያደረገ፡ አገሪቱን የባሀር በር ለማሳጣት የደፈረ የመንግሥታዊ ባህልና ኃላፊነትና ግንዛቤ የሌለው ሕወሃት፡ ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ቆርጦ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሕዝቡን በቃ! የሚል ድምዳሜ ላይ ማድረሱ አያጠራጥርም!
በዓለም ታሪክ ውስጥም ሕወሃት “ታዋቂ” የሚሆነው፡ ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት፡ የሀገርን ልኡላዊነትና መሬት ቆርሶ ለጎረቤት ሀገርና ለከፍተኛ ብድር ስጭና ገንዘብ ለዋጭ አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።
ዛሬም ሆነ ነገ፡ ለሀገራችን ዘላቂው መፍትሄ ግን መንግሥት የሕዝብን ፍላጎት ለማክበር መቻሉና ለዚህም ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት መዘርጋቱ ነው። ይህንን ለማድረግ፡ አሁንም ትንሽ የተስፋ መስኮት አለ – የሕውውሃት ስዎች ኃላፊነት የሚስማቸው ቢሁን። ይህ ለሕወሃትና ግብረአበሮቹ ተቀባይ ሳይሆን ቢቀር፡ ቀሪው ምርጫ ሕዝቡ እየተረገጠ መቀጠል፡ ወይንም እነርሱ ከመድረኩ መወገድ ነው።
እስካሁን በዚህ ድህረ ገጽ ይህንን አሳብ አላራመድንም ነበር። የሁኔታው አስከፊነት ግን አሁን የወቅቱ አስፈላጊ እርምጃ አድርጎታል!
    http://ecadforum.com/Amharic/archives/10852/

Saturday, January 4, 2014

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ  ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ሲያሰቃዩ መቆየታቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

አንድ ሹፌር ለኢሳት እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳፋሪዎችን ከመኪና ላይ በማስወረድ ድብደባ እንደፈጸሙባቸውና እርሳቸውም በጥፊ እንደተመቱ ተናግረዋል
“እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም” የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን  ገልጸዋል።
ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።
ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል።
ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።

ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ


- አቶ መላኩ የሞገቱበት የአዋጅ አንቀጽ እንዲስተካከል ተወሰነ
በሙስና ወንጀል የተከሰሱት አቶ መላኩ ፈንታን ክስ መመልከት ያለበትን ፍርድ ቤት በሚመለከት ዛሬ የተወያየው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክሱ መታየት ያለበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት መሆኑን ለማሳየት ተከሳሹ የጠቀሱት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች
አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ሆኖ እንዲስተካከል በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ውሳኔው ስምንት ተቃውሞና ሁለት ድምፀ ተአቅቦ ተመዝግቦበታል፡፡
የአዋጁ ንኡስ አንቀጾች እንደሚያስረዱት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ ሳሉ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚያጠፉት ጥፋት የሚጠየቁት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያደረገው ውይይት ባለሥልጣናቱ በዚህ መልኩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚጠየቁ ከሆነ ጥፋተኛ ወይም ነፃ ቢባሉ እነሱ ወይም መንግሥት ይግባኝ የሚሉበት ዕድል አይኖርም፡፡ ይህ ደግሞ ሁለቱንም ወገን የሚጎዳና የይግባኝ መብትን የሚፃረር ነው፡፡ 
ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የአቶ መላኩ ክስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የመታየት ዕድል አይኖረውም፡፡ 
 https://www.google.no

በጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን (ሰማያዊ ፓርቲ)

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር የማካለሉ ሥራ ከመስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 9, 2009) ጀምሮ እየተከናወነ እንደሆነ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ዕለታዊ የሱዳን ጋዜጣ ሱዳን ትሪቢውን (Sudan Tribune) በመስከረም 8 ቀን 2002 ዓ.ም. (September 18, 2009) መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ ያንገበገባቸው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩት ዜጎቻችንም ራሳቸውን በተለያዩ “ኮሚቴዎች” እና “ግብረ ሃይሎች” በማደራጀት ለጉዳዩ ክፈተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ፓርቲያችን (ሰማያዊ)፣ ለነዚህ ሀገር ወዳድ ዜጎች ያለውን ከፍተኛ አክብሮት ለመግለጽ ይወዳል፡፡
ሆኖም፣ የነዚህን ሀገር ወዳድ ዜጎችና አፍቃሪ-ኢትዮጵያውያን ጥሪና መግለጫዎች ከቁብም ካለመቁጠር፣ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሥውር የሥልጣን ማራዘሚያ ደባዎችን እየሸረበ እንደሚገኝ አጋልጠዋል። ወያኔ ራሱ ያቋቋመው “የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ኮሚቴ” አባላት ራሳቸው በተለያዩ ቃለ-ምልልሶች እንዳጋለጡት፣ ወያኔ በአባቶቻችን ደም ተላቁጦ ለተቦካውና የበርካታ ሰማዕታትን ህይወት ላስከፈለው የኢትዮጵያ ድንበርና የግዛት ሉዓላዊነት ግዴለሽነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊ ግዛትና ድንበር “በጫካ ውሎችና ስምምነቶች” እያመካኘ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
ይህንንም ከፍተኛ የሆነ የሃገር ክህደትና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ለማስተባበል በመገንዘብ፣ የወያኔ-ኢህአዲግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ ላይ በመስከረም 2002 ዓ.ም መጨረሻ ላይ አንድ የማደናገሪያ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከዚህም የማደናገሪያ መግለጫ ውስጥ የሚከተሉትን ሦስት(3) አበይት ጉዳዮች መገንዘብ ይቻላል። እነርሱም፦
1ኛ. የኢትዮጵያና ሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ (Ethio-Sudan Political Committee) ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ አካል መኖሩንና የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) በፖለቲካው ኮሚቴ ሥር እንደሚሠራ አረጋግጧል፤ የዚህ የኮሚቴ መዋቀርና የአሰራር ሂደቱም ለረጅም ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ተደብቆ የቆየ እንደሆነና፣ ወያኔ-ኢህአዲግም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ክትትል መጋለጡን ሲያውቅ ተጨንቆ ያወጣው ምስጢር ነበር።
2ኛ. የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) ከጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 15, 2009) እስከ ግንቦት 2002 ዓ.ም.(May 2010) ድረስ የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይስና ቅኝት እንደሚያደርግም ገልጾ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ ሲጋለጥ ያወጣው ሌላው ምስጢር ሲሆን፣ (ሱዳን ትሪቢውን ያወጣውን ዜና የሚያጎለምስ) እና የሱዳን ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበሩን ለማካለል የሚያደርገውን ዝግጅት የሚያስተጋባ ነው።
3ኛ. የድንበር ክለላው ከግንቦት 2002 ዓ.ም. ( May 2010) በኋላ እንደሚደረግና ከዚህም ጋር አያይዞ ወያኔ-ኢህአዲግ ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት አምነው የተቀበሉት የድንበር ክልል እንዳለ አስምስሎ ለማቅረብም ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ወያኔ-ኢህአዲግ አሁን የሚያካሂደው “የድንበር-ክለላ ሂደት” ዳግም ድንበርን የመከለል ተግባር ( re-demarcation ) እንደሆነ መግለጹ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ይህ ማደናገሪያና ተራ ልፈፋ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማወናበድና ግዛቱን በጫካ ውሎችና ስምምነቶች አማካይነት አሳልፎ ከመስጠት የዘለለ ኢምንት እውነታ የለውም፡፡ ይሄንን በተመለከተም ያጠኑት ሊቃውንትንና በግዛቱ ላይ የሚኖሩትን ዜጎች ምስክርነት ሊያገኝ አልቻለም፤ አይችልምም፡፡
የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት “ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት የተቀበሉት የድንበር ክልል” የሚለው ሀተታ፤ ሜጀር (ሻለቃ) ጉዊን የተባለው የእንግሊዝ ጦር መኮንን በ1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) “አስምሬአለሁ” የሚለውን የወሰን ክልል ነው። ይሁንና አንድ በእንግሊዝ የቅኝ-ገዥነት አባዜ የሰከረ ሻለቃ ያሰመረውን መስመር መሠረት አድርጎ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉዓላዊነትን የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን “ለሱዳን ይገባታል” ብሎ መሟገቱ የፖለቲካ ቅጥፈት እንጂ ታሪካዊ ማስረጃ የለውም፡፡ የሚከተሉትም ታሪካዊ ዳራዎች የወያኔን ሙግት ውድቅ ያደርጉታል፦
1ኛ.ሻለቃ ጉዊን መሬቱን አካልያለሁ ሲልና በወረቀት ሲያሰምር፤ በኢትዮጵያ በኩል አንድም ተወካይ ስለአልነበረ የጉዊን የድንበር ማካለል ተግባር ከቅኝ ገዢዎች ማንአለብኝነት ተለይቶ የማይታይና የውል አፈጻጸም ሥርዓት የማይከተል በመሆኑ የተነሳ ተቀባይነት የለውም፡፡
2ኛ. የ1896 ዓ.ም.(እ.አ.አ.) የአድዋ ጦርነት ድል በቅኝ ገዥዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ መደናገጥ ምክንያት 1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) አካባቢ እንግሊዝና ጣሊያን በጋራ በመመሳጠር የሰሜንና የምዕራብ ኢትዮጵያን ድንበር ለመግፋት የፈፀሙት ሴራ ስለሆነ፣ የሻለቃ ጉዊን ተልዕኮም ከዚያ ሴራ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ስለሆነም ተቀባይነት የለውም፡፡
3ኛ. ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በፊትም ይሁን ከዚያ በኋላ፣ ይህ ሻለቃ ጉዊን ከለለው የሚባለው መሬት ምን ጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይባስ ብሎም፣ በአፄ ቴዎድሮስና በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ግዛት አሁን ሱዳን ተብሎ ከሚጠራው ሃገር በጣም ወደ ውስጥ የገባ ነበር፡፡ ስለሆነም፣ የግዛት ጥያቄ ሲነሳ የይገባኛል ታሪካዊ መሠረት ያላት ኢትዮጵያ መሆኗን ለማስተባበል አዳጋች ነው፡፡
4.አሁን የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት በመጋቢት 22/2006 ዓ.ም ገደማ March 30, 2014 ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ግልጽነትና ተጠያቂነትን መርሆው ያላደረገው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ግን አንዳችም መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያገኝ የተለመደ አፈናውን ገፍቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ በእልፍ-አዕላፍ ድንበር ጠባቂ ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ተጠብቆ የኖረውን ዳር ድንበር፣ ወያኔ በተለመደ “የደጃዝማቾች ፈረስ መጠጫና ጉግዝ መጫወቻ ነው” በሚል ንፍገት አሳልፎ ለሱዳን ሊሰጠው ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሰፊ ውሃ-ገብና ለም ሉዓላዊ መሬት፣ የታሪክ ማስረጃዎችንና የኢትዮጵያውያንን መስዋዕትነት በማናናቅ ለባዕዳን ሊሠጥ አይችልም፡፡
ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ማስረጃዎችና በዓለም-አቀፍ የአሠራር ደንብ መሠረት፤ ወያኔ-ኢህአዲግ ከሱዳን ጋር የሚያደርገው የድንበር ክለላ ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። ከዚህም ባሻገር፤ ከዋናው ባለጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት ይሁን የድንበር ክለላ ተግባር ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም።
ከዚህም ሌላ፣ ወያኔ-ኢህአዲግ የተወሰኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት ቆርሶ በመስጠት ሥልጣኑን በጎረቤት አገር ሱዳን ለማስባረክ ብሎ የሚያደርገው ሽር-ጉድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም፡፡ ውጤቱም “ታግዬላቸዋለሁ የሚላቸውን ብሄሮችና ብሔረሰቦች” ከማዳከምና ብሎም ለማፈራረስ የተጠቀመበተ ዘዴ የቅኝ ገዢዎች ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ ያሰመሩትን የድንበር መስመር በመቀበልና የቅኝ ገዢ ጠበብትን እንደ ምስክር በመጠቀም ነው። ይህም ተግባሩ፣ቀድሞውንም በቋፍ የነበረውን የወያኔ-ኢህአዲግን መንግሥት የፖለቲካ ቅቡልነት የሚያሳጣው መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ አልፎ-ተርፎም በዚህ ተግባሩም ዛሬም የቅጥረኛ ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ህዝቡ እንዲያውቀው እንፈልጋለን፡፡
ይህ የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን ተግባር የሃገራችን ኢትዮጵያን ዓለም-አቀፍአዊ ክብር የሚጎዳ ስለሆነ ከተግባሩ እንዲታቀብ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም፣ ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ዝርዝር መረጃና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበትም ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ ይህን ሳያደርግ ቢቀር ግን፣ ፓርቲያችን የተጣለበትን የአባቶቻችንን ክብርና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መቼም ቢሆን ያለምንም ማወላወል የምንወጣ መሆናችንን ለጉዳዩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ኅዝብ በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡
ሰላም፣ ተስፋ፣ ፍትህና እኩልነት በዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በተከበሩባት ኢትዮጵያ ዕውን ይሆናል!!!

የጃዋር ተቃርኖዎች

ባለመንጫው መቼ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል?

በጌታቸው ሺፈራው
የዛሬን አያድርገውና ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሃመድ በበርካቶች በተለይም በዲያስፖራው ዘንድ ተቀባይነት ነበረው፡፡ ጃዋር በተለያዩ ጊዜያት ሶማሊያና የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሚሰጠው ትንተና ባሻገር ባገኛቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የኢህአዴግን አስተዳደር ሲቃወም ተስተውሏል፡፡ ለአብነት ያህል በአንድ ወቅት ከቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስተር አቶ በረከት ስሞኦን ጋር አልጀዚራ ቴሊቪዥን ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያውያንን ጠበቃ ሆኖ መከራከሩ አይዘነጋም፡፡ ይህ የጃዋር ጥረት ከኦሮሞ ብሄርተኝነትንና የፖለቲካ ተንታኝነት አልፎ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሚል ክብር አጎናጸፈው፡፡ ጃዋር ራሱም ከጠባብ ብሄርተኝነት ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግ መክሯል፡፡ ለአብነት ያህል የብአዴን ጀኔራሎች ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ተለቅመው በታሰሩበት ወቅት ለአማርኛ ተናገሪ ኢትዮጵያውያን ተከራክሯል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቆምም ኢትዮጵያውያን በአንድነት መስራት እንዳለባቸው መክሯል፡፡ በወቅቱ ‹‹Ethiopia: General Tadesse and General Asaminew›› በሚል መጣጥፉ ኢትዮጵያውያን በየ ብሄራቸው ከመታጠር ይልቅ አንድ መሆን እንዳለባቸው ለማሳሰብ ታዋቂውን ጸረ ናዚ አባባል ተቅሶ  እንዲህ መክሯል፡፡ ‹‹መጀመሪያ በኮሚኒስቶቹ ላይ መጡ፡፡ አልተናገርኩም፡፡ ምክንያቱም ኮሚኒስት አልነበርኩም፡፡ በመቀጠልም በማህበራቱ ላይ መጡ፡፡ አልተናገርኩም፡፡ ምክንያቱም ማህበራቱ ውስጥ አልነበርኩም፡፡ ከዚያም በቤተ እስራኤላዊያን ላይ መጡ፡፡ አልተናገርኩም፡፡ ምክንያቱም ቤተ እስራኤላዊ አልነበርኩም፡፡ ከዚያም በእኔ ላይ መጡ፡፡ (አሁን) ለእኔ የሚናገርልኝ ማንም አልቀረም፡፡›› ብሎ ኢትዮጵያውያንን አስጠንቅቆ ነበር፡፡
‹‹በኢትዮጵያውያን መካከል ጥላቻን እየዘራ ለምዕተ አመት ስልጣኑን እያራዘመ የቆየውን አምባገነንነት መበጠስ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ የተረጋጋ አገርና ዴሞክራሲ ለመመስረት ያስችል ዘንድ አንዱን ቡድን ከሌላው ቡድን እያጋጨ የመኖርን አዙሪት መበጠስ ይኖርብናል፡፡ ዜጎቻችን በሰላምና በተድላ ይኖሩ ዘንድ በአገራችን የህግ የበላይነት መስፈን ይኖርበታል፡፡›› ሲልም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከብሄር ድንበር ወጥቶ ለኢትዮጵያውያን መቆሙን እምነት ተጥሎበት ነበር፡፡ በወቅቱ በአማራነታቸው ታሰሩ ያላቸውንም ‹‹የፖለቲካ እስረኞቻችንን በዚህ በዓል ሰሞን እናስታውሳቸው፡፡ ገቢያችን የሚፈቀድልን ደግሞ ለሚወዱት (ለቤተሰቦቻቸው) እጃችንን መዘርጋት ይገባናል›› ሲል በኢትዮጵያውነት መንፈስ ጽፏል፡፡ በእርግጥ እነዚህን ተግባራት በሚያከናውንባቸው ጊዜያት ጃዋር በብሄር ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አሁን ግን ጃዋር ባልታወቀ ምክንያት አቋሙን ቀያይሮ የማይታረቁ ተቃርኖዎች ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡
እንደገና ጠባብ ብሄርተኝነት (ተቃርኖ.1)
የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ በብዛት፣ በኢኮኖሚ፣ በባህልና በሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ትልቁን ቦታ የሚይዝና የሚያበረክት ህዝብ ነው፡፡ ይህን ጃዋርም በተደጋጋሚ ሲሟገትበት ተስተውላል፡፡ ኦነግ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውን ህዝብ ‹‹መገንጠል›› በሚል የአናሳ ጥያቄ ውስጥ አፍኖ ማግኘት የነበረበትን ስልጣንና ክብር አሳጥቶታል፡፡ ጃዋርም ኦነግ ለኦሮሚያ ህዝብ የሚገባውን እንዳልሰራና ህዝብም ተገቢውን ስልጣን አለማግኘቱን ባገኛቸው መድረኮች ይገልጻል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጃዋር በሌሎች ብሄሮች ላይ ተፈጸመ የሚለውን ችግር ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያ አገራችን፣ ወንድሞቻችን›› በሚል በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ሲታገል ቆይቷል፡፡ አንድ ሆነን ብሄርን የሚያጋጨውን ስርዓት እናስወግድ፤ በራሳችን ብቻ ታጥረን ሌሎቹ ላይ የሚደርሰውን ችግር ዝም ብለን በማየታችን ችግሩ የሚደርሰው ‹‹እኛው›› ላይ ነው ብሎም ታዋቂውን ጸረ ናዚ አባባል ጠቅሶ መክሯል፡፡ በዚህ ሰናይ አቋሙም በተለያዩ ወቅቶች እንደ አንድነት ያሉ ህብረ ብሄር የአገር ውስጥ ፓርቲዎችና የዲያስፖራው አካላትም እየተጋበዘ ኢትዮጵያውያን በጋራ ችግራቸውን መቅረፍ እንዳለባቸው ትንታኔውንና አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ይህም ይበልጡን በኢትጵያውያን ዘንድ እንዲታወቅና ትልቅ ክብር እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡
ሆኖም ህዝብን ተጠቃሚ ባለማድረጉ የሚተቸው ኦነግ በተሸነፈበት በአሁኑ ወቅት ብሄር ዘለል ትግል ጀምሮ የነበረው ጃዋርም እንደገና ወደ ኦነጋዊ ጠባብ ብሄርተኝነት ተመልሷል፡፡ በተለይ በቅርቡ ‹‹እኔ በቅድሚያ ኦሮሞነቴን ነው የማስቀደመው›› ብሎ አገራችን፣ ወንድሞቻችን እያለ ሲያነሳው ከነበረው ይልቅ ከኦሮሞ ጉዳይ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጻል፡፡ ምንም እንኳ ይህ የአቋም ለውጥ በጃዋር ያልተጀመረ ቢሆንም ‹‹አንዱን ብሄር ከሌላኛው ብሄር›› በማጋጨት ላይ ተመስርቷ ብሎ ይቀወመው ወደነበረው ያረጀ ያፈጀ ፖለቲካ መመለሱ ትልቅ ቦታ ይሰጡት በነበሩት ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡
ከኦሮሞነት ወደ ሙስሊም ኦሮሞነት (ተቃርኖ.2)
ጃዋር በኢትዮጵያውነት ማዕቀፍ ከሌሎች ጋር ጀምሮት የነበረውን ትግል ትቶ ‹‹ቅድሚያ›› ለኦሮሞ ማለቱ ያልተጠበቀ ቢሆንም መብቱ ነው ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ በዚህ መንሸራተቱ አለመቆሙ ግን ተቃርኖውን ይበልጡን አጠናክሮታል፡ በተለይ አልጀዚራው ‹‹ስትሪም››  በኋላ ጃዋር ከኦሮሞም ወረድ ብሎ ለኦሮሞ ሙስሊም ቅድሚያ እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ በአንድ መድረክ ባስተላለፈው መልዕክት እሱ የተወለደበት አካባቢ ‹‹99 በመቶው›› ሙስሊም በመሆኑ ቀና ብሎ ለመሄድ የሚሞክር ክርስቲያን ኦሮሞ አንገቱን በሜንጫ እንደሚቆረጥ በኩራት ተናግሯል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ማዕቀፍ አምባገነንነትን መዋጋት አለብን ብሎ ጸረ ናዚውን አባባል ጠቅሶ ሲያስተምር የነበረው ጃዋር ወደ ኦሮም ማዕቀፍ መውረዱ ሳይበቃ አሁን ደግሞ ከኦሮሞነትም ወደ እምነት አጥብቦታል፡፡ ‹‹የተወለድኩበት አካባቢ አንገትክት ቀና ያደረክ ክርስቲያን ኦሮሞ አንገትክን በሜንጫ ትቆረጣለህ›› የሚል ‹‹ጃሃዲስት›› መልዕክት አስተላልፏል፡፡ በዚህም ጃዋር ‹‹የኦሮሞ መብት›› ይከበር ሲል የሙስሊም ኦሮሞዎች መሆኑ እንደሆነ አሳብቆበታል፡፡ ምክንያቱም ሙስሊም ኦሮሞዎች ክርሲቲያን ኦሮሞዎች አንገታቸውን ቀና አድርገው ሲሄዱ ሙስሊሞች በሜንጫ እንዲጨፈጭፏቸው እየሰበከ ለክርስቲያን ለኦሮሞ መብት መቆም ስለማይችል ነው፡፡
……ወደ ኢትዮጵያዊ ሙስሊምነት (የማይታረወቅ ተቃርኖ.3)
ስለ ሌሎች ብሄሮች ችግር፣ ስለ ሁሉም ኢትዮጵያዊነት ሰብአዊ መብት አብረን እንስራ በሚል ወደ ኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ እየገሰገሰ የነበረው ጃዋር ወደ ኦሮሞነት ከዚያም ለክርስቲያን ኦሮሞዎች ርህራሄ የሌለው ሙስሊም ኦሮሞነት ተንደርድሯል፡፡ በዚሁ አቋሙ ሳይወጣ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ለመሆንም ይጥራል፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ክርስቲያኖች በሙስሊሙ አንገታቸው እንዲቀላ የሚያበረታታው ጃዋር የጎንደርና የአክሱም ሙስሊሞች ከኦሮሞ ሙስሊሞች ጋር አብረው እንዲሰሩ ሊመክር ሞክሯል፡፡ ከኢትዮጵያውነት ወደ ኦሮሞና ከዚያም ሲጠብ ወደ ኦሮሞ ሙስሊምነት የወረደው ጃዋር የብሄርን ድንበር ጥሶ የእምነት አንድነት ለመፍጠር ሲፍጨረጨር የማይታረቅ ሌላ ተቃርኖ ውስጥ መግባቱን የተረዳ አይመስልም፡፡
የዚህ ተቃርኖ በሁለት መንገድ የሚታይ ነው፡፡ አንደኛው ወደ ጠባብ የኦሮሞ ሙስሊምነት የተንደረደረው ጃዋር በብሄር ለማይመስሉት የትግራይና አማራ ሙስሊሞች መጨነቁ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ እምነትና ብሄር አብረው የማይሄዱና የሚጋጩ ማንነቶች መሆናቸው ነው፡፡ የብሄር ደንበር የማይወስነው የእምነት ማንነት መገንባት ከተፈለገ ‹‹እኔ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ፣ አማራ፣ ጉራጌ…›› ማለት አያስፈልገውም፡፡ ቅድሚያ ሙስሊም አሊያም ክርስቲያን መሆን ነው የሚችለው፡፡ ይህ ከሆነ ጃዋር በቅርቡ ‹‹እኔ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ›› ያለው ማንነቱ ያበቃለታል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ብሄርና እምነት በአገር ማዕቀፍ ሲታዩ የማይጣጣሙ ማንነቶች በመሆናቸው ነው፡፡ ጃዋር መጀመሪያ ሙስሊም ልሁን ካለ አርሲ ውስጥ ከሚገኘው ክርስቲያን ኦሮሞ ይልቅ አክሱምና ጎንደር ከሚገኙት ሙስሊሞች ጋር ዝምድና ይኖረዋል፡፡ በዚህ ወቅት ማንነቱ ኢትዮጵያዊ ነው የሚሆነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም! ሙስሊም ኦሮሞ ነኝ ብሎ ከክርስቲያን ኦሮሞው ይልቅ ሌላውን ሙስሊም ሊያስቀድም አይችልም፡፡ ‹‹ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ!›› ካለ ደግሞ ቀድሞ የሚመጣው የጎንደርና የአክሱሙ ሙስሊም ሳይሆን ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ክርስቲያንና ዋቄ ፈታ ኦሮሞ ነው፡፡ ጃዋር ግን በሁለቱ መካከል ሲምታታ ቆይቷል፡፡
ጃዋር ከዚህም ባሻገር ኦሮሞ ማለት ሙስሊም ማለት ነው በሚል ሌላ የተምታታ ትርጓሜ ውስጥም ገብቷል፡፡ ኦነግና አንዳንዴ የዚሁን ተሸናፊ ፓርቲ አቋም የሚይዘው ጃዋር ኦሮሚያ ምድር ላይ አልደረሱም የሚሏቸው እነ አጼ ዮሃንስና አጼ ቴዎድሮስ በሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ አደረሱ ብሎ የሚያምነውን ጥቃት ኦሮሞን ለመጉዳት መሆኑን ሲገልጽ መታረቅ ወደማይችለው የተቃርኖ አዙሪት ውስጥ አስገብቶታል፡፡ በአንድ ወቅት ሌላኛው ሲጎዳ ዝም ማለት የለብንም በሚል ጸረ ናዚውን አባባል ተቅሶ ሲመክር የነበረው ጃዋር አሁን ወደ ብሄር ከዚያም ወደ እምነት ናዚያዊነት እየወረደ ነው፡፡
ከኦነግነት ወደ ‹‹ጎበናነት›› (ተቃርኖ 4)
ያኔ እንዲህ ሳይምታታበት ጃዋር ኦህዴድን ኦሮሞን የሚያስገዙ አዲሶቹ ‹‹ጎበናዎች›› ብሎ ይተች እንደነበር ይታወቃል፡፡ ያኔ ‹‹ከጎበናዎቹ›› ይልቅ ከእነ አንድነት ጋር በመስራት የበኩሉን አስተዋጽኦም አድርጓል፡፡ እያቆየ ግን ጃዋር ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እየሸሸ አሁን አብሯቸው እየሰራ ከሚገኘው ኢህአዴጎች ጎን መሸጎጥ ጀምሯል፡፡ ጃዋር ‹‹እኔ መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ›› ከሚለው አንስቶ ከህወሓት ጋር እንዲተባበር ያስገደዱት የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንዱና የመጀመሪያው እሱ ‹‹ቀኝ ጽንፍ›› ብሎ የሚጠራቸው ፓርቲዎች ከሌሎቹ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ነው፡፡ ጃዋርና አቶ ቡልቻ ይበልጡን መጥበብ የጀመሩት አንድነት አብሮት መሄድ ካልቻለው መድረክ ይልቅ ከሌሎች ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች ጋር ትብብር ለመፍጠር ፍላጎት እንዳለው በተነገረበት ማግስት ነው፡፡ ሰማያዊና አንድነት በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎች መንገዶች ጠንከር ያለ የፖለቲካ እንቅስቀሴ ሲያደርጉ ደግሞ እነ ጃዋር ‹‹የጠላቴ ጠላት›› ብልሹ ፖለቲካ ውስጥ ገቡ፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲያ በአዲሱ መጽሃፋቸው እንደሚገልጹት 97 ላይ ቅንጅት ጠንካራ እንቅስቀሴ ሲያደርግ ህወሓትም ሆነ ኦህዴድ ‹‹የጸረ ነፍጠኛ›› ግንባር ለቋቋም ጥሪ አድርገውላቸው ነበር፡፡ ዶክተሩ ‹‹አልፈልግም!›› ብለው ባይመልሷቸው እሳቸውም በነ ጃዋር ‹‹አዲስ ጎበና›› ሆነውት አርፈው ነበር፡፡ ይህ ለደ/ር መረራ የቀረበ ጥሪ አንድነትና ሰማያዊ ሲጠናከሩ፣ አሊያም ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኦህዴድ እራሱን ሊያጠናክር፣ ወይንም የዲያስፖራውን ጫና ለመቀነስ ጃዋርና የእነ ለንጮው ኦነግም ‹የጸረ ነፍጠኛው›› ጥሪ ደርሷቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የእነ ለንጮ ለታው ኦነግ በ2007 ዓ/ም ምርጫ ለመድረስ እየተሰናዳ እንደሆነ እየተወራ ነው፡፡ ኦነግ ለ‹‹ጸረ ነፍጠኛ›› ትግሉ ያመቸው ዘንድ አገር ውስጥ የራሱን ጠባብ ሚዲያዎች ማቋቋም ጀምሯል፡፡ ለአብነት ያህል ከወራት በፊት ‹‹ሰፉ›› የተባለች በኦሮምኛና አማርኛ የምትታተም መጽሄት ገበያ ላይ አውሏል፡፡ ለዚህም የተደራዳሪዎቹ የኦህዴድም ሆነ ህወሓት ይሁንታ እንደሚያስፈልግ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የመጽሄቷ ዋና አላማም ስለ አሁኑ ዘመን ጭቆናም ሆነ በደል ሳይሆን ‹‹አማራ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል ማጋለጥ ነው››፡፡ ይህ እንግዲህ የድርድሩም ሆነ የኦነግ ስልት አንዱ አካል መሆኑ ነው፡፡ ህወሓትና ኦነግ የሚስማሙበት አላማ!
በእርግጥ ወደ አገር ውስጥ የሚመለሱት የኦነግ አመራሮች ብቻ አይደሉም፡፡ ጃዋር ሊመለስ እንደሚችልም አንዳንድ ጭምጭምታዎች እየተሰሙ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከሌሎቹ ተቀናቃኞቹ ይልቅ ለጃዋር ርህራሄ ማሰየቱን ማሳየቱ አንድ ፍንጭ ነው፡፡ እነ አቡበክር፣ እስክንድር፣ ርዕዮት…. በእጃቸው ምንም ሳይገኝ፣ በፍጹም ሰላማዊነታቸው ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ሲፈረድባቸውና ፊልም ሲሰራባቸው የሜንጫ ጀብድን ሲያስተምር የታየው ጃዋር ምንም አልተባለም፡፡ ከእሱ ይልቅ ኮፈሌ ውስጥ ለበቅ የያዙ ወጣቶችን ከቦኮሃራም፣ ከታሊባንና አልቃይዳ ጋር እያመሳሰሉ ‹‹አሸባሪዎች›› ብለው ፊልም ሰርተውባቸዋል፡፡
ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ደግሞ ኤሊያስ ክፍሌ ስለ ኤሌክትሪክ ገመድ ማቋረጥ ያወራው ‹‹የአሸባሪዎች ማንነት ማሳያ!›› ተደርጎ ሊቀርብ ነው፡፡ በምን መመዘኛ የኤሌክትሪክ መስመር መቁረጥ የሰው አንገት በሜንጫ ከመቁረጥ በልጦ ‹‹ሽብር›› ሊሆን ይችላል? የጃዋርን ‹‹ጀብድ›› እነ ዶ/ር መረራ፣ ዶ/ር ብርሃኑ፣ የኢሳት ጋዜጠኞች፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ….አውርተውት ቢሆን ኖሮ ስንት ፊልም ይሰራበት ነበር?  ኢህአዴግ ይህንን የጃዋር ጀብድ አሁን ባይጠቀምበትም መቼም አይጠቀምበትም ማለት አይደለም፡፡ ሌሎች እሱ ከእኛ በላይ የሚያውቃቸውንም ሚስጥሮች እንደተደራደረባቸው ሁሉ ወደ አብሯቸው እየሰራ እንዳያፈነግጥም በልጓምነት ይጠቀሙበታል፡፡ እግረ መንገዱን በርካታ ‹‹ፋኦሎችን›› ያሰሩታል፡፡
በእርግጥ ጃዋር በፖለቲካው ከስሮ ወደ አገር ቤት የገባ የመጀመሪያው ሰው አይደለም፡፡ በርካቶቹ ከእሱ በላይ ‹‹ጀግና›› ተብለው ከህወሓት/ኢህአዴግ ብብት ተሸጉጠዋል፡፡ እነ ሰለሞን ተካልኝ ኤርትራ በርሃ ድረስ ሄደው ‹‹በለው!›› እንዳላሉ ተመልሰው ‹‹ይቀጥል!›› ብለዋል፡፡ ሙዚቀኞች፣ ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች፣ የእምነት ‹‹አባቶች›› ብቻ በርካቶች እየከሰሩ ተመልሰዋል፡፡ ሲወናበድ የኖረው ጃዋር ተደራድሮ ቢመለስ የሚገርም አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ ለጃዋር አገሩ ናትና መመለሱን የሚጠላ የለም፡፡ ችግሩ በዚህ ስርዓት ምርጫ እንደሌለ ሲናገር እንዳልቆየ ለምርጫ ሊመለስ መሆኑ መነገሩ ነው፡፡ ለኦሮሞ ህዝብ ባለመቆማቸው ኦህዴዶችን ‹‹ጎበናዎች›› እንዳላለ ከህወሓት፣ ብአዴንና ደኢህዴን ስር የሴቶች፣ የትራንስፖርት……ሚኒስቴር ስር ለመስራት ከፈቀደ ነው፡፡
http://ecadforum.com/Amharic/archives/10641/

አይ ስብሐት ነጋ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)


ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam
በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።
በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን ‹‹አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት፤ ስለሆነም ነበር ከፍተኛ ጥበቃ አልፈን የገባነው፤›› ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ በከባድ ጥያቄም ቢሆን የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ ማረጋገጡ በተማሪዎቹም ቢሆን ውሎ አድሮ ትዝብት ላይ ይጥለዋል።TPLF power broker, Sibehat Nega
ዶር. በድሉ ዋቅጂራ ስለስብሐት ነጋ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ በሚል በጻፈው ላይ ዶር. ዳኛቸውን እንደሚከተለው ይጠቅሳል፤ ‹‹ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት፤ በቃ በአጭሩ (ኢትዮጵያዊ ሆኖ)ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው፤›› በቅንፍ ውስጥ ያለው የኔ ነው፤ ልክ ነው፤ አንድ ግለሰብ በማናቸውም ምክንያት ከኢትዮጵያዊነት ቢወድቅ ኢትዮጵያዊነቱ የከሸፈ ነው ለማለት ይቻላል፤ ነገር ግን ከኢትዮጵያዊነት መውደቅንና ኢትዮጵያዊነትን መጣልን ለይተን ማየት ያስፈልጋል፤ አንድ ሰው በማናቸውም ምክንያት ከፍተኛውን የኢትዮጰያዊነት ባሕርይና ግዴታ መሸከም አቅቶት ቢወድቅ ለዚያ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ከሸፈ፤ ለስብሐት ነጋና ለጓደኞቹ ከከሸፈባቸው የቆየ ይመስለኛል፤ ከራሱ አልፎ የሌሎችን ኢትዮጵያዊነት ለማክሸፍ የሚሞክር ደሞ ከመክሸፍ አልፎአል፤ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት የከሸፈ ኢትዮጵያዊነት ነው ማለት ነው።
ስብሐት ነጋ ዋና ዓላማው በሙሉ ነጻነት የመጣለትን እንደመጣለት መናገር ነው፤ ምሳሌዎችን እንጥቀስ፤– ሀ) ‹‹ከኢትዮጵያ ሕዝብ በላይ የኤርትራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት አለው፤›› ስብሐት ነጋ ስለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ስለኤርትራ ሕዝብ፣ ስለኢትዮጵያዊነት ያለው እውቀት የሚባል ነገር እንዲህ ያለው መዘባረቅ ነው፤ ስብሐት ነጋ ጨረቃ ከጸሐይ የበለጠ ትሞቃለች ቢልም አይደንቀኝም፤ አልከራከረውም፤ ስብሐት ነጋም ብቻውን መናገር እንጂ መከራከር አይፈልግም፤ ለ) ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኤርትራ ሕዝብ የበለጠ የኤርትራን መሬት ይፈልጋል፤›› እንደምሳሌ ያነሣው አሰብን ነው፤ ባድመን አላነሣም!  እሱና ጓደኞቹ የኢትዮጵያን ወጣቶች በከሸፈ ጦርነት ውስጥ የማገዱት ባድመ ለሚባል መንደር ነው እንጂ አሰብ ለሚባል ወደብ አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ ጦርነቱን በመቃወም ድምጼን ያሰማሁት ኢትዮጵያዊ ወይም ኤርትራዊ ሆኜ አልነበረም፤ ሰው ሆኜ ነው፤ ዛሬ ስብሐት ነጋ ሲዘላብድ ኢትዮጵያዊነት የማይታይበትን ያህል ኤርትራዊነትም አይታይበትም፤ በዚህም ጉዳይ ላይ መከራከር አይፈልግም፤ ሐ) ‹‹ለማንኛውም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ መከልከላቸው የማውቀው ብዙ ነገር የለኝም፤ ይከልከሉም አልልም፤ አይከልከሉም አልልም፤ መብታቸው ነው፤›› ይህ መዘላበድ ካልሆነ ምንድን ነው? ምን ቁም-ነገር ይዞ ነው ይህንን የተናገረው? የገለባ ክምር ውስጥ አንድ ፍሬ መፈለግ ይቀላል።
አንድ ሌላ የስብሐት ነጋ ዘዴ (ዘዴ ካልነው!) ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ እንደመጣለት ይናገርና ‹‹አላውቅም›› ይላል! የማያውቀውን መዘባረቅ ግን ይችላል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የምን ፓርቲ እንደሆነ አይታወቅም፤ የእስላም ፓርቲ ነው?›› ስብሐት ነጋ እውቀትን የሚሻ ቢሆን ለፓርቲዎች እውቅናን የሚሰጠውን መሥሪያ ቤት ያውቀዋል፤ ለምን ብሎ ይጠይቅ? ለምን ብሎ እውነቱን በማወቅ ይታሰር? ትክክለኛ መረጃ ባለማወቅ እንደልብ የመናገርን ነጻነት ይገድባልና ‹‹አላውቅም›› ማለት ለመዘላበድ ይጠቅማል፤ ምንም እንኳን የሰላዮች ሠራዊት እንዳለው ብናውቅም ስለእስላሞችና ስለሰማያዊ ፓርቲ የተናገረውን እንደፖሊቲካ ከወሰደው ደረጃውን ከማሳየት አያልፍም፤ ሰማያዊ ፓርቲን በሁሉም ዘንድ ለማስጠላት የሚከተለውን ይላል፤ ‹‹እስላሞች ወንድሞቻችን የሚሉት ደግሞ የት ያውቁናል? ሲቀጠቅጡን የነበሩ፤ ተራ ሕዝቡም አይወዳቸውም፤›› የጤፍ ቅንጣት የምታህል የማሰብ ተግባር ቢኖርበት ስብሐት የተናገረው ያልተጠረነፉትን እስላሞች በሙሉ የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት ይችል ነበር።
ስብሐት ነጋ አንድ መቶ ሃያ ዓመታት ያህል ወደኋላ ቢሄድ ኤርትራ የሚባል አገር አያገኝም፤ በዚያ መሬት ያሉ ሰዎች ላላቸው ወይም ለሌላቸው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የስብሐት ነጋን ምስክርነት እንደማይፈልጉ በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፤ ለሌሎቻችን ኢትዮጵያዊነትም ቢሆን የስብሐት ነጋ ምስክርነት አያሻንም፤ አሰብን አንሥቶ ብዙ ወጣቶች ያለቁበትን ባድመን ሳያነሣ መቅረቱ በአንድ በኩል፣ አሰብንም ሆነ ባድመን ከሚፈልጉ ወገኖች መሀል እሱ መውጣቱን በጣም ግልጽ አደረገ፤ ወዴት እንደገባ ግን ገና አልነገረንም!!!