Wednesday, November 20, 2013

መቋጫ ያጣው የወገኖቻችን ስቃይ እና በደል በሳውዲ አረቢያ አሁንም ቀጥሏል!


ethio saudi 10


ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አማራው አንድነን … ትግሬውም አንድነን … ጉራጌው አንድነን … መብታችን ይከበር … እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሶታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን በከፈቱት ተኩስ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን ይገልጻሉ።
የጸጥታ ሃይሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች በመታገዝ የኢትዮጵያውያኑን ተቃውሞው መግታት ተችሏል ብለዋል። እነዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በማውሳት ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወሰዱ ባሉት የተናጠል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመመለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በኢትዮጵያ መንግስ በኩል ባለመመቻቸቱ ከሳውዲያኑ ወረበሎች አሰቃቂ ግድያ ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ውሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት ቁም ስቅላቸውን እያዩ መሆኑ ተግልጾል።
ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ያልተሟሉበት ማጎሪያ ውስጥ 4 ቀናቸውን እንዳስቆጠሩ የሚነገርላቸው ኢትዮጵያዊያን እና ሪያድ መንፉሃ ጅዳ እና መካ እስከነ ልጆቻቸው በየመገዱ ላይ ወድቀው ለመንገድ ላይ አዳሪ የተዳረጉ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ብሶት ለማድመጥም ሆነ ለማየት ከሃገር የመጣ የመግስት ባለስልጣን አለመኖሩ ታውቋል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ጅዳ ከተማውስጥ ኢትዮጵያውያኑ የሚኖሩበት አካባቢ በሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች እና በኢትዮጵያውያን መሃከል በተነሳ ግጭጥ 76 ሰዎች መቁሰላቸውን የሚገልጹት ምንጮች በዛ ቀውጢ የተኩስ እሩምታ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ ኢትዮጵያዊ ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ተቀማጭነታቸው ሪያድ እና ጃዳ ከተማ በሆኑት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር እና የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች ላይ ተስፋ የቆረጠው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ወገናችንን ለማየት በኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል የተባሉት የልኡካን ቡድን አባላት እሰከአሁን ምንም አይነት የሚጨበጥ ነገር መስራት ባለመቻላቸው ኢትዮጵያውያኑ ለከፋ አልቂት በመዳረግ ላይ መሆናቸው ተገልጾል።
ሰሞኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ያለውን የጅምላ ግፍ እና በደል ይሄን ያህል የሚጋግነን እና ቦታ የሚሰጠው አለመሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት ምሽት መንፉሃ አካባቢ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ17 በሚበልጡ አውቶብስ ተጭነው እንደተወሰዱ የሚነገርላቸው ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ህጻናት ሴቶች አረጋውያን የሚገኙበት አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከሪያድ የ6 ሰአታት ጉዞ በኋላ ያልታወቀ ምድረ በዳ የሆነ አካባቢ እንዲወርዱ መገደዳቸውን እና እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ በውል እንደማይታወቅ ተገልጾል።

Saturday, November 16, 2013

የፌደራል ፖሊሶች በሳውድ አረቢያ የሚፈጸመውን ግፍ ለመቃወም አደባባይ በወጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

ህዳር (ስድስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የሳውዲን መንግስት ለመቃወም በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞዋቸውን ለመግለጽ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበዋል።
ከ100 በላይ ሰዎች ታስረው የነበረ ሲሆን እስከ ምሽት ድረስ 40 የሚሆኑት ተለቀዋል። ሰልፉን ያዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ 15 የአመራር አካላትም በእስር ላይ እንደሚገኙና ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አለመፈታታቸው ታውቋል።
የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ በድብቅ በስልክ እንደተናገረው የድርጅቱን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትንና ምክትላቸው አቶ ስለሺ ፈይሳን ጨምሮ 15 አመራሮች ጃንሜዳ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። ወጣት ጥላየ ታረቀኝ ታስሮና ድብደባ ተፈጽሞበት ከተለቀቁት መካከል አንዱ ሲሆን ፣ የኢትዮጵያን መንግስት ድርጊት ለመግለጽ እንደሚቸገር ገልጿል።
ሌሎች አስተያየት ሰጪዎችም በመንግስት ድርጊት አገር አልባነት እንደተሰማቸው  ይናገራሉ
ሰማያዊ ፓርቲ ከጥቃቱ በሁዋላ ባወጣው መግለጫ ” የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጎን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን በዛሬው እለት አስመስክሯል ብሎአል።
የመንግስት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖች ላይ የተፈጸመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንጹሀን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል ብሎአል።
በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገን መንግስት ህዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ በመቋቋም የኢትዮጵያ ህዝብ አያት ቅድመ አያቶቻችን የሰጡንን አደራ በመቀበል ያስረከቡትን ክብርና ማንነት ለማስመለስ ወደ ሁዋላ እንደማንል እርገኛ መሆናችንን እንገልጻለን ብሎአል።
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ሽመልስ ከማል ለአልጀዚራ  ሰልፈኞቹ የተከለከሉት ባልተፈቀደ ሰልፍ ላይ በመገኘታቸውና ኢትዮጵያን ህዝብ በጸረ-አረብ ስሜት በማነሳሳታቸው ነው ብለዋል።

አንድ አንዳርጋቸውን መግደል የነፃነቱን ትግል ማስቆም አይቻልም

ህወሃቶች የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈሱ የኖሩ ነብሰ ገዳዮች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አሁንም ክብሬንና ነፃነቴን የሚሉ ዜጎችን ይዘው ደብዛቸውን ለማጥፋት ብዙ ዓይንና ብዙ ጆሮዎችን በየቦታው አቁመናል እያሉ ያቅራራሉ። ይሄን ሁሉ ዓይንና ጆሮ ይዘንስ የሚያሸንፈን ማን ነው ? ሲሉም ይደመጣሉ። እነርሱ እንደሚሉት ዓይኖቻቸው ማየት፤ጆሮዎቻቸውም መስማት የሚችሉ አይደሉም። የህወሃት ዓይኖች ማየት የተሳናቸው እውራን፤ ጆሮዎቻቸውም ማድመጥ የማያውቁ ደናቁርት እንደሆኑ የታወቀ ነው። ህወሃቶች ይህን የማይሰማ ጆሮና ፤ማየት የተሳነውን ዓይን ይዘው እየተደናበሩ፤ ይህን ለመደበቅ ህይዎት ያላቸው መስለው ይታያሉ። አዎን ህወሃቶች ጭው ባለ በርሃ ላይ ብቻችሁን እንደቆማችሁ እወቁ። የሚነገረው እና የሚሆነው በሙሉ ስለተሰወረባችሁ በብዙ ሚሊየኖች መሃከል ብቻችሁን እርቃናችሁን ቀርታችኋል። ብዙ ሚሊዮን ዓይኖች እና ጆሮዎች በእናንተ ላይ መተከላቸውን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄ እንደ ህወሃት-ኢህአዴግ ጆሮዉ የተደፈነና አይኑ የታወረ ድርጅት አይደለም። ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚያይ ዓይን፤ የሚሰማ ጆሮና የሚያስተዉል ልቦና ያለው ህያው ንቅናቄ ነው። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ ግልፅ ነው። ነፃነት ! ፍትህ ! እና ዲሞክራሲ ! ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ እንዲያገኙ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተነስተናል ጉዞ ጀምረናል፤ ሺ አንድአርጋቸውን ፈጥረናል። ልብ ይበሉ ነፃነት ፍትህ እና ዴሞክራሲ ለሰው ልጆች የተሰጡ ክቡር ስጦታዎች ናቸው። ህወሃት እነዚህን ክቡር ስጦታዎች ከዜጎች ላይ ነጥቆና ህዝብን ረግጦ መቀጠል የለበትም። ህወሃት የዜጎችን ነፃነት ነጥቆ ፤ ፍትህን አጓድሎና ህዝብን ረግጦ እንደከዚህ በፊቱ በሠላም እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ተሳስቷል። በህወሃት ቅዥት አገራችን ተጎድታለች። ህዝቧም ለማያባራ ጉስቁልናና ውርደት ተዳርጓል። ብዙዎችም አገር አልባ ሁነው በየሰው አገሩ መፃተኛ ሁነው እንዲኖሩ ተገደዋል። በእኛ እምነት በአገራችን ላይ እየደረሰ ላለው ውርደት በዋናነት ተጠያቂው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ዋነኛው ጠላት ነው የምንለውም ዜጎቻችንን ለጉስቁልናና ለውርደት ስላደረገም ጭምር ነው። እኛ ይህን አገር በቀል ጠላት ከሥሩ ነቅለን ለመጣል ተነስተናል። ከዚህ ትግል የሚያቆመን ምንም ዓይነት ምዳራዊ ኃይል እንደሌለ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን። ህወሃቶች አንገታችንን አስደፍተው አይገዙንም። ጥቁር ደም ያፈራቻቸው የቁርጥ ቀን ውድ ልጆቿ የነጻነት ታሪክ በጥቁር ቀለም ይጻፍ ዘንድ የሚያደርጉትን ሀገርን የማዳን ጥሪ እንዲህ በቀላሉ መግታት ከቶ አይቻልም። ወያኔዎች አትደናበሩ! ጋሬጣውን መለየትን ለእኛ ተውሉን።
ታዲያ ይህን ንቅናቄ አንድ አንዳርጋቸውን በመግደል ማስቆም የሚቻል የሚመስለው ጅላ ጅል ቡድን አገሪቷን እየገዛ በመሆኑ ተቆጭተናል። አንዳርጋቸውን መግደል ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊ አንዳርጋቸውን መፍጠርና ትግሉንም የሚያጠናክር እና የሚያፋፍም መሆኑን አልተረዱም። የኢትዮጵያ ህዝብ የእምቢተኝነት፣ የአልገዛም፣ የነጻነት ታሪክን ለማስከበር መሰዋእትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆንን ከአንዳርጋቸው ከተማረ ቆይቷል። መቆጨታችን ግን እንዲሁ በቁጭት ብቻ የሚቀር የሚመስለው ካለም ድግሞ ተሳስቷል። ይሄ ቁጭት በየደረሱበት የንፁሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ አገር መምራት የሚመስላቸውን ህውሃቶች ከተንጠለጠሉበት ዙፋን አውርደን በልካቸውና በአቅማቸው እንዲኖሩ ለማድረግ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ያደርገናል። ህወሃት ውስጥ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ግለሰብ ካለ አሁን ቆም ብሎ እንዲያስብ እናሳስበዋለን። ጀንበር ሳትጠፋባችሁ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገውን ትግል ተቀላቀሉ። እርግጥ ነው ለነፃነት የሚደረገው ትግል በየመስኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ህወሃትም የእጁን እንደሚያገኝ ምንም ዓይነት ብዥታ እንዳይኖራችሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት የቆመበት መሠረት ፅኑ፤ ዓላማውም ህዝባዊ ነው። በዚህ በፀና መሠረት ላይ ህዝባዊውን ዓላማ አንግበው የተነሱ ሚሊዮኖች አሉ። እነዚህ ሚሊየኖች የሌሉበት ሥፍራ የለም። ከቤተ-መንግስት እስከ እርሻ ማሳ፤ ከስለላ ተቋማት እስከ አገሪቷ መከላከያ ኃይል፤ ከሃይማኖት ተቋማት እስከ መንግስት መሥሪያ ቤቶች፤ ከዘመናዊ ትምህር ተቋማት እስከ ተከበሩ ገዳማት ድርስ ለክብራቸው ዘብ የቆሙ ሚሊየኖች አሉ። እነዚህ ሚሊኖች የቆሙት መረቅ የበዛበትን ወጥ ዓላማ አድርገው ሳይሆን በፀናው መሠረት ላይ ለተተከለው ክቡር ዓላማ ነው። ይህ ክቡር ዓላማ ነፃነት፤ ፍትህ ፤እኩልነት እና የህግ የበላይነት እንጂ ሌላ አይደለም። እነዚህ ሚሊየኖች አትኩረው ማየት የሚችሉ ድንቅ ዓይኖች ያሏቸው፤ አጥርተው ማድመጥ የሚችሉ ክቡራን ጆሮዎች ያሏቸው መሆናቸውን ህወሃቶች እንዲያውቁት እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት ማንንም ፍርሃት እና ድንጋጤ ውስጥ መክተት አይፈልግም።እንዲያውም ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚታገለው ዜጎች ሁሉ ከፍርሃት ነፃ ሁነው በደስታ እንዲኖሩ ለማስቻል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ካሁን ወዲያ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዓይንና ጆሮ የሚያመልጥ አንዳችም ነገር እንደማይኖር የሚያሳድደን ቡድን እንዲያውቀው እንፈልጋለን። ዓይንና ጆሯችን በሁሉም ሥፍራ በንቃትና በጥንቃቄ ነገሮችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ህወሃቶች ከትዕቢታችሁ ብዛት የተነሳ የህዝቡን ምክር መናቃችሁን እናውቃለን።የወገኖቻችንንም ድምፅ ጫጫታ እያላችሁ እንደምትሳለቁም እናውቃለን። ይሄ እንደማይጠቅማችሁ ብዙ ግዜ ነግረናችኋል። የህዝቡን ምክር ስሙ፤ የወገኖቻችሁንም ድምፅ አድምጡ ብንላችሁ በእምቢታችሁ ፀንታችኋል። ልቦናችሁ እንደ ፈርዖን ልብ ደንድኗል።ልብ ማደንደን እንኳን እናንተን ለመሠለ ደካማ ፍጡር ይቅርና በዘመኑ እኔ “እምላክ” ነኝ እሰከ ማለት ለደረሰው ለፈርዖንም አልበጀም። እንዲህ ዓይነት የልብ ድንዛዜ እናንተ በዚያ ጠባብ ዓላማችሁ ጣልነው ለምትሉት ለመንግስቱ ኃ/ማሪያምም አልረባውም። አሁንም የእኛ ምክር አጭርና ግልፅ ነው። የመዘዛችሁትን የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው መልሱ። የዘጋችሁትን በር ክፈቱ። የነጠቃችሁትን የዜጎች ነፃነት መልሱ። በህዝቡ ላይ ያወረዳችሁትን የፍርሃት ድባብ አስወግዱ። የተከላችሁትን የዘረኝነት እሾህ ንቀሉ። ከእውነት ጋርም ታረቁ። እንዲህ ብታደርጉ የዚያችን አገር በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን የሚበላችሁን እሳት ማጥፋት አይቻላችሁም። መጥተናል!!
እኛም ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክረናል። የትግል ዘርፋችን ሰፍቷል። በሁሉም አቅጣጫ መረባችን ተዘርግቷል። ከዚህ መረብ የትም አታመልጡም። ማምለጫ መንገዳችሁ አንድ ብቻ ነው። እርሱም የህዝቡን ድምፅ መስማት፤ እውነተኛ መልስ መስጠት እና ለህግ ተገዢ መሆን። አበቃን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ ! ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረዋል

ethio saudi addis1


አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።
መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።
ethio saudi addis2ዘገባዉ አክሎም ፖሊስ አንዳንድ ጋዜጠኞች ያነሱትን ፎቶግራፍ መደምሰሱንም አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይን አስተያየት ማግኘት እንዳልተቻለም ተገልጿል። ለተለያየ ሥራ ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንዲያወጡ የተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ካለቀ ወዲህ እዚያ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት እየደረሰባቸዉ እንደሚገኝ እየገለፁ ነዉ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር። ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሩ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ላይ የሚያደርሠዉን በደል፥ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ እያወገዙት ነዉ። ትናንት እዚህ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ፍራንክፈርት ዉስጥ ባደረጉት ሠልፍ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን፥ ማንገላታት፥ ማሠር፥ መደብደብ መግደሉን እንዲያቆም፥ የኢትዮጵያ መንግሥትም የዜጎቹን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዉ ነበር።የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም፥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፀመዉን በደል በመቃወም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ አደባባይ ወጥተዉ ነበር።
ይሁንና የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጠቀሰዉ ጋዜጠኛ እንዳለዉ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ላይ የተፈፀመዉ አዲስ አበባም ተደገመ። ሠልፈኞቹ ተቃዉሟቸዉን ለማሰማት ገና ከመሠብሰባቸዉ ፖሊስ ደብድቦ አብዛኞቹን በተነ፥ የተቀሩትን አሠረ። ዮሐንስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።
ዩናይትድ ስቴትስ ርዕሠ-ከተማ ዋሽግተን-ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚወስደዉን እርምጃ በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ትናንት የተጀመረዉ የአደባባይ ሠልፍና ዉግዘት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞችም ይቀጥላል።ethio saudi addis
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎችን ከሐገሩ ማባረሩን ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደነገረን በኢትዮጵያዉያንና በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መካካል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ዛሬም ጋብ ብሏል።ከዚሕ ቀደም ኮንትራታቸዉ ተቋርጦ፥ ቀጣሪዎቻቸዉ ጠፍተዉ፥ ወይም ታመዉ ጂዳ ኢትዮጵያ ቆንስላ ዉስጥ ለወራት ተጠልለዉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ ማቆያ ጣቢያ ገብተዋል። ነብዩን ከአንድ ሠዓት በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያዉ ጥያቄዬ ምን አዲስ ነገር — የሚል ነበር። (ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ – ለአሰራር በሚያመች መልኩ ርዕሱን ቀይረነዋል)
ከዚህ በታች የሚገኙትን አስፈንጣሪዎች በመጫን ዝርዝሩን ይመልከቱ
በሌላ በኩል ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ የሚከተለውን ብሏል፡፡
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን በድል እና ስቃይ ለመቃወም አዲስ አበባ በተጠራው ሠላማዊ ሠልፍ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሶች አሰቃቂ ድብደባና እሰር መፈፀማቸው ቀደም ተብሎ መገለፁ የሚታወቅ ነው፡፡
ቀደም ብሎ ስማቸው የተዘረዘሩት እስረኞች በአሁኑ ሰዓት ሁለት ቦታ የተከፈሉ ሲሆን ከዚህ በታች ያሉት ፒያሳ ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሲሆን
1ኛ. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀ/መ
2ኛ. አቶ ስለሺ ፈይሳ የፓርቲው ም/ት ሊቀ/መ
3ኛ. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አላፊ
4ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ አላፊ
5ኛ. ወጣት አቤል ኤፍሬም አባል
6ኛ. ሰለሞን ወዳጄ አባል
7ኛ እመቤት ግርማ አባል
8ኛ. ዳዊት ፀጋዬ ደራሲና ጻሃፊ (በግል)
9ኛ. እየሩስ ተስፋ አባል
የተቀሩት እዛው መስቀል ፍላወር አካባቢየሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ
1ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ የፓርቲው የፋይናስ ጉዳይ አላፊ
2ኛ. አቶ ጌታነህ ባልቻ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ አላፊ
3ኛ. አቶ አብታሙ ደመቀ የብሔራዊ ም/ቤት አባል
4ኛ. አቶ ዮናስ ከድር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
5ኛ. ዮሴፍ ተሻገር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
6ኛ. ፋሲካ ቦንገር አባል
7ኛ. መርከብ ሀይሌ አባል
8ኛ. አስራት አብርሃም ደራሲና ጻአፊ (በግል)
9ኛ. ንግስት ወንድይፍራው አባል

Monday, November 4, 2013

በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ

"የኢህአዴግ የአፈና ገመድ ነትቧል፣ ድርጅቱ ተናግቷል"

tplf1


ኢትዮጵያ ግራ በሚያጋባና ሊተነበይ በማይችል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መገኘቷን ያመኑ የህወሃት ሰዎች መካካል የእርቅ ሃሳብ ላይ ለማተኮር እቅድ እንዲያዝ ሃሳብ ማንሳታቸው ተሰማ። ኢህአዴግ የቀድሞው የአፈና ገመዱ መንተቡን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውና አለመተማመን መንገሱ ተጠቆመ።
ጎልጉል መረጃ በመስጠት የሚታወቁ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራርና ዲፕሎማት እንዳሉት ህወሃት ውስጥ “እርቅ አስፈላጊ ነው” በሚል እቅድ እንዲያዝና እንዲሰራበት ሃሳብ ቀርቧል። በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ሳቢያ ስጋት የገባቸው የህወሃት ሰዎች የእርቅ ሃሳብ እንዲሰራበት ያቀረቡት ሃሳብ ግን በመደበኛ ስብሰባ አይደለም።
በህወሃትና ህወሃት በሚያዛቸው አቻ ፓርቲዎች መካከል ያለው የመከባበርና የመገዛት ስሜት ከመለስ ሞት በኋላ መበላሸቱ፣ በኢህአዴግም ሆነ በህወሃት ደረጃ የተፈጠረው ልዩነትና በሙስና ስም የተጀመረውን ዘመቻ ተከትሎ የተነሳው አለመግባባት አደጋ እንዳያስከትል ተፈርቷል። የመረጃው ምንጭ እንደሚሉት በጣም ጥቂት ካልሆኑ በስተቀር ከሙስና የጸዱ አለመኖራቸው “ማን ንጹህ ሆኖ ማንን ይጠይቃል?” የሚል ቅሬታ አስነስቷል።
ህወሃት ባሰበው በሁሉም መንገድ የበላይ ሆኖ ሊቀጥል እንደማይችል ከየድርጅቶቹ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በስፋት እየተነገረ መሆኑንን ያነሱት እኚሁ ሰው፣ ይፋ ባልሆነ መንገድ የቀረበው እርቅን የመቀበል ጥያቄ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የተነሱት አስደንጋጭ ችግሮች ተከትሎ መሆኑን አልሸሸጉም።
ሊታመን በማይችልና ባልተለመደ መልኩ የሃይማኖት አባቶች ኢህአዴግን አንደበታቸውን ከፍተው በግልጽ ማውገዛቸውን፣ “አገሪቷን ገደላችኋት” በማለት መኮነናቸውን ተከትሎ በኢህአዴግ ዘንድ መደናገጥ እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል። የእምነት ጉዳይ ጥንቃቄ የሚያሻው በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ዲፕሎማት “ኢህአዴግ በቀድሞው ፓትሪያርክ ፈቃድና ውዴታ ያደርግ እንደነበረው አሁንም በደኅንነት ሃይሎች ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠርና አመራሮቹን አንደበታቸውን ማፈን የማይችልበት ደረጃ መድረሱን አምኖ ተቀብሏል። በዚህ ላይ ደግሞ እስካሁን ምላሽ ያላገኘ የድምጻችን ይሰማ ጉዳይ አለ” ኢህአዴግ እንደተምታታበት አመላክተዋል።
ሲኖዶሱ በጉባኤው ያነሳቸው ነጥቦች ኢህአዴግ ነገሮች ቀስ በቀስ ከእጁ እንደወጡበት የሚያሳይ እንደሆነ ያመለከቱት የኢህአዴግ ሰው “ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኢህአዴግ አባላት በልብ ከድርጅቱ ጋር እንደሌሉ ሪፖርት ቀርቧል። አብዛኛው አባልና ደጋፊ ባለሃብቶች የሚባሉትን ጨምሮ ሰላማዊ ለውጥ እንዲካሄድ ኢህአዴግ ወደ እርቅ መንገድ እንዲሄድ ይፋ (ኦፊሴላዊ) ባልሆነ መልኩ ያነሳሉ” በማለት ድርጅቱ የገባውን ስጋትና መሸርሸር ያስረዳሉ።
እርቅ ከተፈለገ ለምን በግልጽ አይቀርብም በሚል ለቀረበላቸው ሃሳብ ዲፕሎማቱ ምላሽ ለመስጠት አልፈለጉም። ይሁን እንጂ “ከማን ጋር ነው የምንታረቀው? እነማንን ነው ለእርቅ የምንጋብዘው? እርቅ ጠያቂ መሆን ያለበትስ ማን ነው?” የሚሉት በግልጽ ባይቀርቡም ተመሳሳይ የስጋት ጥያቄዎች እንዳሉ ሳይገልጹ አላለፉም።
በቅንጅት ጊዜም በተመሳሳይ የዕርቅ ፍላጎትና “ሥልጣን እናስረክብ” የሚል አቋም ተነስቶ እንደነበር ያስታወሱት ምንጫችን፤ በወቅቱ ሃሳቡ ተግባራዊ ያልሆነው “ወያኔዎችን ወደመጡበት ጠራርገን እንመልሳቸዋለን” በማለት አንድ የቅንጅት አመራር ለሕዝብ መፈክር ሲያወርዱ ከተሰማ በኋላ ነበር፡፡
በመከላከያ አዛዦችና በደህንነት የተለያዩ መምሪያዎች የሃላፊዎች ለውጥ እያካሄደ ያለው ኢህአዴግ ከአቻ ፓርቲዎች ጋር ውህደት በማድረግ ብሔራዊ ፓርቲ ለማቋቋም በሁለት ጉባኤዎች ሃሳብ ቢቀርብም ተግባራዊ አላደረገውም። ፓርቲው ህብረ ብሔር ከሆነ ህወሃት የገነባቸው የንግድ ድርጅቶችና በሞኖፖል የያዘውን ቁልፍ ስልጣን እንዲያጣ ስለሚያደርገው ጊዜ ሲያጓትት መቆየቱን ያመለከቱት የመረጃው አቀባይ “ይህ ፍርሃቻ አሁንም ሆነ ወደፊት ለሚፈለገው በሃሳብ ደረጃ ያለ እርቅ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል የውስጥ ለውስጥ ሃሜት አለ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ሆኖም እጅግ የተወሳሰበ የፖለቲካ ትወና ውስጥ ያሉት ካልሆኑ በስተቀር በማናቸውም መልኩ እርቅን ለመቀበል የማያቅማሙ እንደሚበዙ ግን አልሸሸጉም፡፡
በኢህአዴግ ውስጥ አለመተማመን መንገሱን የሚናገሩ ወገኖች “ለራሳቸው መተማመን ያቃታቸው ክፍሎች እንዴት ሌላውን አስማምተው ይመራሉ” በማለት መጠየቅ ከጀመሩ ቆይተዋል። በተለይም አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ መንበሩ ከመጡ በኋላ አገሪቱ በደቦ መመራቷ የኢህአዴግን መሽመድመድ የሚያሳይ እንደሆነም እየተቹ ነው።
sebhat negaሁሉም ሰላም ነው፤ ልማት ነው፤ ዕድገት ነው፤ ህዳሴ ነው … በማለት አንድም ችግር የሌለበት ለመምሰል የሚሞክረው ህወሃት ደግሞ በውስጡ የመከፈል አደጋ አጋጥሞት እንደማያውቅ ምንነታቸውና የስራ ደርዛቸው በውል በማይታወቀው አቶ ስብሃትአማካይነት እያስታወቀ ነው። እሳቸው እንደሚሉት ችግር የህወሃት “ሰማያዊ ስጦታውና በረከቱ ነው” አቶ ሃይለማርያምም በበኩላቸው “ኢህአዴግ መካከል መከፋፈል አለ የሚሉ የዋሆች ናቸው” ሲሉ አንድነት የሰፈነበት አመራር እንዳለ ለማስተጋባት ሞክረዋል።
የእርቅ ሃሳብ ተሰንዝሯል በማለት መረጃውን የሰጡን ዲፕሎማት ግን ይህንን አይቀበሉም። “በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚታይ ነው። አንዱ እኔ ነኝ። ሌሎችም አሉ። ብዙዎች ሰላማዊ ህይወት ናፍቆናል። የተወሳሰበውን አገራችንን ፖለቲካ አካሄድ ለመተንበይ ተቸግረናል። መፍትሔው የእርቅ ሃሳብ ብቻ ነው” በሚል ተከራክረዋል።
በድርጅታቸው ውስጥ የበላይና የበታች መጥፋቱን፣ የበታቹ የበላዩን እንደሚያዘው፣ አንዳንዴ የበላይ መስለው ምንም ዓይነት የውሳኔ ሰጪነት ሚና የሌላቸው ክፍሎች መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር እንደሆነ የሚናገሩት እኚሁ ሰው፣ “እርቅና ዋስትና የሚሰጥ አግባብ ቢያገኝ የመጀመሪያው ስምምነት ፈራሚና ደጋፊ ስብሃት ነው። ቀሪውን የጡረታ ዘመኑንን በትዝታ ያለውን እየበላ መኖር ይፈልጋል። እሱ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ተመሳሳይ ፍላጎት አለን። አስከማውቀው ድረስ ችግሩ ከራስ ምግባርና ከድርጅት ተልዕኮ በመነጨ የተሰሩት ጥፋቶችና ሃጢያቶች መብዛታቸው ከለውጥ በኋላ የሚያመጣቸው የተጠያቂነት ጣጣዎች ናቸው” ብለዋል፡፡
በኢህአዴግ ውስጥ ንጹህ ሰዎች አሉ ለማለት የማይቻልበት ደረጃ መደረሱን የሚያመለክቱት ዲፕሎማት፣ ህወሃትም ሆነ ኢህአዴግ አሁን የጋራ ነጠብ የሌላቸው፣ የርስ በርስ ትስስራቸው የላላና የተለያየ፣ አንዱ ሌላውን ለመንካትና ለመገምገም የሞራል ብቃት ያጣበት፣ እርስ በርሱ በወንጀል የሚጠቋቆምበት የውድቀት ጫፍ ላይ መድረሱን የውጪ አገር ወዳጆቹም ተረድተውለታል፤ አሁን ለእነርሱም ችግር የሆነባቸው ቁጭ ብለው ሥልጣን ላይ የሰቀሉትን ህወሃት አሁን ቆመው እንዴት ማውረድ እንደሚቻል መቸገራቸው ነው ብለዋል። የእርቅ ሃሳቡ ከውጪ አገር ወዳጆቻቸው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ግን ፍንጭ አልሰጡም።
በህወሃትም ሆነ በኢህአዴግ ደረጃ የውስጥ ስጋት ቢኖርም “ሕዝብ እስኪ ዛሬን ልደር” በሚል የሞራል ውድቅት ውስጥ በከተተው ድህነት የተመታ በመሆኑ ለጊዜው ያምጻል የሚል ግምገማ አለመኖሩን ዲፕሎማቱ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ህዝብ በኢህአዴግ ደስተኛ አለመሆኑ፣ የጥበቃና የቁጥጥር መረቡ እንደወትሮው ትጋት ማጣቱ፣ የአካባቢ ስሜትና “ወገኔን ለምንና እስከመቼ አሳልፌ እሰጣለሁ?” የሚል አስተሳሰብ መበራከቱ፣ አጋጣሚ ተቃውሞ ቢነሳ መቋቋም እንደማይቻል፣ ረብሻ ከተነሳ የስርዓቱ ባለሟሎች ህልውና ጉዳይ አስጨናቂ እንደሚሆን ግንዛቤ ስለመኖሩ አላስተባበሉም። በማያያዝም እሳቸው በዚህ ደረጃ ስርዓቱን ከገመገሙና ችግሩን ከተረዱ በይፋ የማይከዱበትን ምክንያት ተጠይቀው “ለጊዜው በምስጢር ጠባቂነት የዝግጅት ክፍሉ ቃሉን ይጠብቅ። የቀረውን ወደፊት እናየዋለን” የሚል ድፍን መልስ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰጥተዋል።

Sunday, November 3, 2013

ድሬዳዋ በወረርሽኝ ሥጋት ላይ ነች በዚህ ወር ብቻ 2ሺ ህሙማን ተመዝግበዋል

የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ናሙና ተልኮ ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡ 

የድሬዳዋ ከተማ በጉንፋን መልክ በሚከሰት የበሽታ ወረርሽኝ ሥጋት ላይ ነች፡፡ በዚህ ወር ብቻ በበሽታው የተያዙ 2ሺ ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡
ከወባ ጋር ተመሣሣይነት አለው በተባለው በዚህ በሽታ የተያዙ ህሙማን፣ በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታልና በተለያዩ የከተማዋ ክሊኒኮችና የጤና ተቋማት ምርመራና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ በበሽታው ተይዘው ህይወታቸው ያለፈ ህሙማን እንዳሉ ምንጮች ቢጠቁሙም፤ የከተማው ጤና ቢሮ ለሞት የተዳረጉ ህሙማን መኖራቸውን አላውቅም ብሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ካሣሁን ኃ/ጊዮርጊስን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው፤ ችግሩ ወረርሽኝ በሚባል ደርጃ ተከስቷል ለማለት እንደማይቻልና ገና ስለሁኔታው ማጣራት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የወባ በሽታ የሚስፋፋበት ወቅት ከመሆኑ አንፃር በአካባቢው ጠበቅ ያለ ዝግጅትና ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ካሣሁን፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከወትሮው የተለየ ቁጥር ያላቸው ህሙማን መመዝገብ መቻላቸው ሁኔታውን ትኩረት እንድንሰጥበት አስገድዶናል ብለዋል፡፡
በዚህ ወር ብቻ 2ሺ ሰዎች መመዝገባቸውንም አቶ ካሣሁን ተናግረዋል፡፡ የበሽታውን ምንነትና የመተላለፊያ መንገዱን ለማወቅ ናሙናውን ወደ አዲስ አበባ የጤናና ሥነ-ምግብ ምርምር ኢንስቲቲዩት (ፓስተር) መላኩንና ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የበሽታው ምንነት ባልታወቀበት ሁኔታ ግን ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩም አቶ ካሳሁን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ሁኔታውን አስመልክቶ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በየዕለቱ ወደ ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እየላኩ መሆናውን እና የበሽታውን ምንነትና የመተላለፊያ መንገዱን በቀጣዩ ሳምንት መረጃው ተጠናቆ እንደደረሳቸው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ከሸንሌና ሔረር ተነስቶ ወደ ከተማዋ ተዛምቷል የሚል ጥርጣሬ ባሳደረው በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ የራስ ምታት፣ ማንቀጥቀጥና ነስር እንደሚታይባቸውና በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የሚታየው ከፍተኛ ሙቀት ለችግሩ መፍጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸውም ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
http://www.addisadmassnews.com

የ“ኢትዮ - ምህዳር” ጋዜጠኛ ከደረሰበት አደጋ ከሞት ተርፏል

የ“ኢትዮ - ምህዳር”  ጋዜጠኛ ከደረሰበት አደጋ ከሞት ተርፏል

ለቀጣይ ህክምና 60ሺህ ብር ተጠይቋል
ጋዜጠኞች ገንዘብ ለማሰባሰብ መክረዋል
ከተመሰረት ጥቂት ወራትን ያስቆጠረው የ “ኢትዮ-ምህዳር” ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ ሚሊዮን ደግነው፣ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ወርቁ እና አዘጋጁ ኤፍሬም በየነ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ወደ ሀዋሳ የተጓዙት ለሽርሽር አልነበረም። በነጋታው ረቡዕ የፍ/ቤት ቀጠሮ ስለነበራቸው ነው፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት “ኢትዮ-ምህዳር”፤ ከሙስና ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዙሪያ በዘገበው ዜና ምክንያት፣ ዩኒቨርስቲው በጋዜጠኞች ላይ የ300ሺ ብር ክስ እንደመሰረተባቸው ይታወሳል። ጋዜጠኛ ኤፍሬም አብሯቸው የተጓዘው አንድም ዜናውን የሰራው እርሱ በመሆኑ፣ ተከራከሩ ቢባል ለፍ/ቤቱ በደንብ እንዲያስረዳ፣ ሁለትም የተከሳሽ ባልደረቦቹን የፍርድ ቤት ውሎ በአካል ተገኝቶ ለመዘገብ እንደነበር ዋና አዘጋጁ ጌታቸው ወርቁ ተናግሯል፡፡
“ማክሰኞ ማታ ራሱ ኤፍሬም አልጋ ፈላልጎ ያዘልን፤ ምክንያቱም የሀዋሳ ልጅ በመሆኑ ከተማዋን በደንብ ያውቃታል” ያለው ጋዜጠኛ ጌታቸው፤ ምሽቱም ሌሊቱም በጥሩ ሁኔታ እንዳለፈ ገልፆ፤ ረቡዕ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ በቀጠሯቸው መሰረት ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መቅረባቸውን ይናገራል፡፡ ሆኖም በዘጠኝ ሰዓት ተመልሳችሁ ኑ ተባልን ይላል። “እኛ በፌደራል ደረጃ ተመዝግበን የምንሰራ በመሆናችን ጉዳያችንም በፌደራል ፍ/ቤቶች ይታይልን፤ እንደገና ዘጠኝ ሰዓት ለመምጣት አንችልም፤ ወደ አዲስ አበባ መመለስ አለብን” ብንልም የግድ ዘጠኝ ሰዓት እንድንመለስ ታዘዝን ብሏል ዋና አዘጋጁ፡፡
ከፍ/ቤት ወጥተው በእግራቸው ወደ መነሀሪያ ከተጓዙ በኋላ ሻይ የሚጠጡበት ቦታ ፈልገው አጭር የኤዲቶርያል ስብሰባ እንዳደረጉ የጠቆመው ጌታቸው፤ “በስብሰባችን የተነጋገርነው የጋዜጣው አብዛኛው አዘጋጆች እዚህ በመሆናችን እስከ ዘጠኝ ሰዓት ባለው ጊዜ ዞር ዞር ብለን ስራ እንስራ፤ ከተሳካልን ከከተማዋ ባለስልጣናት አንዱን የጋዜጣችን እንግዳ እናድርግ” በሚል ተስማማን ይላል ጌታቸው፡፡ ከዚያም የሀዋሳ ጋዜጠኛ ወደሆነ አንድ ጓደኛቸው ይደውላሉ፤ ማንን ብናናግር ይሻላል በሚል እንዲያማክራቸው፡፡ ጋዜጠኛ ጓደኛቸው ግን “ልጄ ታሞብኝ ፒያሳ አካባቢ መድሀኒት እየገዛሁ በመሆኑ፣ ባጃጅ ተሳፍራችሁ ፒያሳ ድረስ ከመጣችሁ እጠብቃችኋለሁ” ይላቸዋል፡፡ ዋና አዘጋጁና ስራ አስኪያጁ በቀጠሮው ሲስማሙ፣ ጋዜጠኛ ኤፍሬም ግን ደስተኛ እንዳልነበር ጌታቸው ተናግሯል፡፡ “ለምን እዚሁ አንጠብቀውም? የእኛ ወደ ፒያሳ መሄድ አልታየኝም” ብሎም ነበር፤ እንደ ጌታቸው ገለፃ፡፡
“ባክህ እንሂድ ጊዜ አናባክን ብየው፣ ፒያሳ ለመጫን ከተደረደሩት ባጃጆች ውስጥ በዥዋዥዌ መልክ ይንቀሳቀስ የነበረ ባጃጅ ላይ ቀድሜ ገባሁ ያለው ጌታቸው፤ ኤፍሬምም ደስ ሳይለው አብሮ ባጃጅ ውስጥ መግባቱን ይናገራል፡፡ “ባጃጁ በጣም ይበራል፤ ትንሽ እንደሄድን ኤፍሬም አሁንም “በቃ” እዚህ እንውረድና ማኪያቶ እየጠጣን እንጠብቀው” ቢልም ጆሮ አልሰጠነውም ነበር ብሏል ጌታቸው በፀፀት፡፡ እየበረረ የነበረው ባጃጅ የበለጠ ፍጥነቱን ሲጨምር “አንተ ቀስ በል! ቀስ በል! ሞተር መጣ፤” እያለው ሞተሩ የተሳፈሩበትን ባጃጅ በሀይል ገጨው፡፡
አደጋው የተከሰተው በግምት ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ እንደሆነ ጌታቸው ተናግሯል፡፡
“ከዚያ በኋላ እኔ ራሴን እንደመሳት አድርጎኝ ስለነበር፣ ብዙም የሆነውን አላውቅም፤ ሰዎች ሊያነሱኝ ሲሞክሩ ግን አመናጭቃቸው ነበር” ሲል በወቅቱ የተፈጠረውን አሰቃቂ አደጋ ገልጿል፡፡ ሰዎች በሌላ ባጃጅ አሳፍረው አዳሬ ወደተባለ ሆስፒታል ሲወስዷቸው፣ አንድ እጁ መጎዳቱን ልብ እንዳለ የሚናገረው ጌታቸው፤ ስራ አስኪያጁ ሚሊዮን ደግሞ ደረቱ ላይ እንደተጐዳ አወቀ፤ የኤፍሬም ጉዳት ግን እጅግ ዘግናኝ ነበር ብሏል፡፡
“ኤፍሬም በደረሰበት አደጋ ከወገቡ በታች ሰውነቱን ማዘዝ አይችልም፤ የማጅራቱ ሰባተኛው አከርካሪ አጥንት ተሰብሯል” መባሉን ስሰማ ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ” በማለት አስረድቷል፡፡
ከአዳሬ ሆስፒታል ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ ለጌታቸውና ለሚሊዮን የመጀመሪያ እርዳታ ሲደረግላቸው፣ በኤፍሬም መጎዳት የተደናገጡት የሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዶክተሮች፤ ልጁ በአስቸኳይ አዲስ አበባ መሄድና ኮሪያ ሆስፒታል መግባት እንዳለበት ገልፀው፤ አንገቱ እንዳይነቃነቅ በጀሶ ካሰሩት በኋላ፣ በሆስፒታሉ አምቡላንስ ወደ አዲስ አበባ ኮሪያ ሆስፒታል ልከውታል፡፡
“አሁን ጥፋተኝነትና ፀፀት የሚሰማኝ የኤፍሬምን ስድስተኛ የስሜት ህዋስ መረዳትና ማንበብ ባለመቻሌ ነው” የሚለው ጌታቸው፤ “ከአንድም ሁለቴና ሶስቴ ወደ ፒያሳ የምናደርገውን ጉዞ ለመሰረዝና እኛን ለማሳመን ጥረት አድርጎ ነበር” ብሏል፡፡
ረቡዕ አመሻሽ ላይ ኮሪያ ሆስፒታል የገባው ጋዜጠኛ ኤፍሬም፤ ከወገቡ በታች ሰውነቱን ማዘዝም ሆነ ሽንቱን መቆጣጠር አይችልም ነበር፡፡ ከትላንት በስቲያ የቀዶ ህክም የተደረገለት ሲሆን፤ ከሌላ የሰውነቱ አካል አጥንት ተወስዶ አከርካሪው ላይ በተሰበረው አጥንት ምትክ ቢገባለትም ሰውነቱን የማዘዝም ሆነ ከዚህ በኋላ ቆሞ የመሄድ ተስፋ እንደሌለው ሀኪሞቹ ተናግረው የነበረ ቢሆንም እንደገና ሰፋ ያለ ቀዶ ህክምና ካደረገ በኋላ ከወገቡ በታችና እግሩ አካባቢ መስማት ጀምሯል፡፡ ለቀጣይ ህክምና 60ሺህ ብር መጠየቁንም ጋዜጠኛ ጌታቸው ገልጿል፡፡
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ጋዜጠኛ ለማትረፍ ሆስፒታሉ እንዲያሲዙ የጠየቃቸውን ብር በአፋጣኝ ለማግኘት ፈተና እንደነበር የሚናገረው ጌታቸው፤ “ኢትዮ-ምህዳር” አዲስ ጋዜጣ በመሆኑና ብዙ ስላልተቋቋምን ተቸግሬ ነበር ብሏል - ጋዜጠኛ ጌታቸው ሀሙስ 11 ሰዓት ላይ ከበርካታ ጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ውይይት፡፡ “ጋዜጠኞች ህይወታችን ለአደጋ የተጋለጠ ነው፤ ራሳችንን ከጥቃት ለመከላከል፣ በአደጋ ጊዜ ለመረዳዳትም ሆነ ለመሰል ጉዳዮች የሚያገናኘን አንድም መድረክ የለም” ሲል ለሙያ አጋሮቹ ንግግር ያደረገው ጋዜጠኛው፤ በሌሎቻችን ላይ አደጋ ላለማድረሱ ዋስትና ስለሌለን በቀጣይ ምን ብናደርግ ይሻላል ሲል ጠይቋል፡፡
በቅርቡ ከስደት የተመለሰውን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ከጉዳቱ እንዲያገገም ለመመኘት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡ ስብሰባውን ያስተባበሩት የ “ነጋድራስ” ጋዜጣ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አንጋፋው ጋዜጠኛ አያሌው አስረስ ናቸው፡፡
የ27 አመቱ ጋዜጠኛ ኤፍሬም፤ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ በ1999 ዓ.ም በጆርናሊዝምና ኮሙዩኒኬሽን ዲግሪውን ከያዘ በኋላ ሥራ የጀመረው በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ ነበር፡፡ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ንግግር በኋላ ጋዜጠኞች የተለያዩ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል፡፡
“በአሁኑ ሰዓት ቅድሚያ ሰጥተን መረባረብ ያለብን ጋዜጠኛ ኤፍሬም ላይ ነው” ያሉት ጋዜጠኞቹ፤ ውጭ አገር ሄዶ መታከም ካለበት፣ባለበትም ሆኖ የሚታከምበትና የሚድንበት መንገድ ካለ ሁላችንም በየፊናችን ገንዘብ በማሰባሰብና ስፖንሰር በማፈላለግ መትጋት አለብን” በማለት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በአደጋው መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁና ማሊዮን ደግነው በፍ/ቤቱ ቀጠሮ መሰረት ዘጠኝ ሰዓት ላይ የቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ፤ ያቀረቡትን አምስት የክስ መቃወሚያዎች ውድቅ በማድረግ ተከራከሩ በሚል ለህዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አደጋውን ያደረሱት የባጃጅና የሞተር ሳይክል ሹፌሮች ዘለው እንደወረዱና ተይዘው ፖሊስ ጣቢያ ገብተው እንደነበረ የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ጉዳዩን ወደያዙት የከተማዋ ትራፊክ ፖሊሶች ደጋግመን ብንደውልም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡
http://www.addisadmassnews.com

“አንድነት” በአባላቶቹ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መባባሱን ገለፀ

“አንድነት” በአባላቶቹ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መባባሱን ገለፀ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ የሚደርስባቸው ጥቃትና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሳቸውን ገለፀ፡፡
ከትላንት በስቲያ ፓርቲው በፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፤ ከ2003 አንስቶ በአባላቱና ደጋፊዎቹ ላይ የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር አቅርቧል፡፡ ፓርቲው “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት” በሚል ባወጣው ሰነድ፤ ከተዘረዘሩ ጥቃቶች መካከል:- በድብደባ አካል ማጉደል፣ በህገወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር ማዋል፣ ማሰቃየት፣ ማስፈራራትና መዛት እንዲሁም በማስገደድ መረጃ ከፓርቲያቸው እንዲያመጡ ማድረግ፣ የመኖሪያ ቦታን በህገወጥ መንገድ መበርበር፣ ይዞታና ንብረትን ያለ ካሳ ነጥቆ መውሰድ… የሚሉት ይገኙበታል፡፡
አቶ ደምሴ መንግሥቱና አቶ ገበየሁ ይርዳው የተባሉ የፓርቲው አመራሮች፤ በአባላትና ደጋፊዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ጠቁመው፣ ጥቃት የደረሰባቸው አራት አዛውንት አባላቶቻቸው ጉዳታቸውን በአካል በማሳየት በህገመንግስቱ እውቅና የተሰጣቸውን:- በህይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት እንዲሁም በህግ ፊት እኩል የመታየት ተብለው የተዘረዘሩት መብቶች መጣሳቸውን ገልፀዋል፡፡
http://www.addisadmassnews.com

በሶማሊ ክልል የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአል ፌዝ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

በክልሉ ለረጅም አመታት ኖረው በተለያዩ ምክንያቶች ከአካባቢው እንዲለቁ የተደረጉ አንዳንድ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መስተዳድሩ እንኳንስ የሌሎችን አካባቢዎች ህዝብ መብት ለማክበር ቀርቶ የክልሉን ነዋሪዎች መብት ማክበር አልቻለም ብለዋል።

ከሌላ ክአካባቢዎች የመጡ በተለይም የአማራ ተወላጆች ሶማሊያ መናገር አትችሉም እየተባሉ ከስራ መባረራቸውን የገለጹት እኝህ ነዋሪዎች፣ በንግድ ስራ የሚተዳደሩና በጅጅጋ ቁልፍ የገበያ ቦታዎችን እና ቀበሌ ቤቶችን ይዘዋል የተባሉ  ቦታውን እንዲለቁና እንዲሰደዱ መደረጋቸውን አውስተዋል።
በአሁኑ ጊዜ ክልሉ የኢትዮጵያ አካል ነው ብሎ መናገር አይቻልም የሚሉት ነዋሪዎች፣ በሌሎች አካባቢ ሰዎች ከሚፈጸመው ግፍ ባልተናነሰ በአካባቢው ተወላጆች ላይ ይፈጸማል ብለዋል።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ይከበራል መባሉን በህዝብ ላይ እንደመቀለድ ይቆጠራል ሲሉ እነዚሁ ለደህንነታቸው የሰጉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በአቶ መለስ ሞት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተፈጥሮ እንደነበር አይኤም ኤፍ ገለጸ

አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ባወጣው የ2004-2005 ግምገማ ኢትዮጵያ ድህነትን ለመቅረፍ የምታደርገውን ጥረት አድንቋል። በኢኮኖሚው ረገድ ስኬት እየታየ መሆኑን፣ አገሪቱም የ7 በመቶ እድገት ማስመዝገቡዋን የገለጸው አይ ኤም ኤፍ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር መንግስት የወሰደውን እርምጃንም አድንቋል።

የአቶ መለስ ሞት በፈጠረው መደናገጥ ሁሉም የውጭ ምንዛሬ ለመግዛት መገደዱን በዚህም ሳቢያ የተፈጠረው የምንዛሬ እጥረት ተጽኖ መፍጠሩን ገልጿል።
የግሉ ዘርፍ ሚና መቀነሱን ያወሳው አይ ኤም ኤፍ ፣ መንግስት በዚህ በኩል ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።
ከዚህ በፊት ባልተለመዱ መልኩ መንግስት ለሽብር ጥቃት የሚውለውን ገንዘብ እንዲሁም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዲቆጣጠር ድርጅቱ ጠይቋል።
ምንም እንኳ ድርጅቱ  ኢትዮጵያ በምን መልኩ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድባት እንዲሁም በየትኛው መልኩ ለሽብርተኞች ጥቅም ላይ የሚውል የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድባት ባይገልጽም፣ በዚህ ረገድ የሰጠው አስተያየት ኢትዮጵያ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የሚካሄድባት አገር መሆኑዋና ያመላከተ ሆኗል።
አይኤም ኤፍ አብዛኛውን ሪፖርቱን ከመንግስት በሚወስደው መረጃ የሚያወጣ በመሆኑ በኢኮኖሚስቶች የተቻል። ይህን ትችት ግምት ውስጥ ያስገባ በሚመስል መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት መረጃዎችን በማሰባሰብ በኩል ጥራት ያለው ስራ እንዲሰራ ፣ ድርጅቱም እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
በአገሪቱ ውስጥ ነጋዴዎች ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ እንዲወዳደሩ ሁኔታዎች ሊመቻቹ እንደሚገባም አይኤም ኤፍ መክሯል።

ኦህዴድ በግምገማ እየተናጠ ነው

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አባላቱን እየገመገ ሲሆን፣ ግምገማው በእርስ በርስ ሽኩቻና መጠላላፍ እየተካሄደ ነው።

ከድርጅቱ አመራሮች መካከል አንዱ ለኢሳት እንደገለጹት ድርጅቱ ህልውና አደጋ ውስጥ ወድቋል።የዝምድና አሰራር እንዲሁም በቡድን ተደራጅቶ አንዱ ሌላውን የሚያጠቃበት ሁኔታ በሰሞኑ ግምገማ በስፋት የታየ ሲሆን፣ አብዛኛው ከታች እስከ ላይ ያለው አመራር በሙስና የተዘፈቀ በመሆኑ አንዱ ሌላውን እንደማያከብር ገልጸዋል።
ድርጅቱ የሚያካሂደው ግምገማ የይስሙላ መሆኑን የሚናገሩት አመራሩ፣ ከፍተኛው አመራር ሳይቀር በሙስና የተዘፈቀ ፣ በቡድን የተደራጀና ጥንካሬ የሌለው በመሆኑ ፣ ታች ያሉትን የድርጅቱ አባላትን ለመገምገም የሞራል ጉልበት አጥቷል ብለዋል።
ኦህዴድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳክሞ ይገኛል የሚሉት አመራሩ፣ ከድርጅቱ መዳከም ጋር ተያይዞ በክልሉ ውስጥ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ነው
አባላቱ ድርጅታቸው በመጪው ምርጫ  በኦሮሚያ ክልል ያለምንም ችግር የሚያሸንፍበትን አሰራር ለመቀየስ ውይይት አካሂደዋል። ምንም እንኳ ድርጅቱ ምርጫውን በተለያዩ መንገዶች እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ቢሆንም፣ በኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው መጠላለፍ ገዢው ፓርቲ ምርጫውን እርሱ በሚፈልገው መንገድ ለማስኬድ ሊከብደው ይችላል ብለዋል አመራሩ።
በኦህዴድ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዋናዎቹ የኢህአዴግ ድርጅቶች ማለትም በህወሀት እና በብአዴን ውስጥም ተመሳሳይ ችግር እንዳለ ጠቁመዋል።

እረፍት የሚነሳው ህምም

የኮንትራት ሰራተኞች ስቃይ፣ የእኛ ፍርሃትና የፖለቲከኞች ጭካኔ

saudi 1


እረፍት አደርግ ብየ ከማህበራዊ መገናኛ መድረኩ ገለል ባልኩባቸው እንደ ብርሃን ፍጥነት በሚወረወሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበርካታ ወዳጆቸ በርካታ መልዕክቶች ይደርሱኛል። ብዙው መልዕክት ደግሞ የሚያጠነጥነው በጅዳ እና በአካባቢው በተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች አሰቃቂ ስቃይ ላይ ያተኮራል … ለነገሩ የአብዛኞቹ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆኑ ከመልዕክቶች ጋር የሚላኩልኝ መረጃዎች እረፍት የሚነሱ ናቸው! …
አዎ ተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በመረጃነት የታጨቀባቸውን የመልዕክት መረጃ ጭብጦች እውነታ ለማረጋገጥ ወደ ጅዳ ቆንስል አመራሁ … መኪናየን አቁሜ ትንሽ እንደ ተራመድኩ እያለ ከፊት ለፊቴ  አንዲት ልጅ እግር ኢትዮጵያዊ ብቻዋን እያወራች ስታልፍ ስመለከት በመደናገጥ ሰላምታ አቅረብኩላት፣ መልስ ሳትሰጠኝ አለፈች!  ደነገጥኩና ባለሁበት ቆሜ በአይኔ ተከተልኳት … በፈጣን እርምጃ የሚያቃጥል የሚለበልበውን መሬት የምትደቃበትን የጠቆረ ባዶ እግሯን፣ እንደነገሩ ከላይዋ ላይ ደረብ ያደረገችውን ጥቁር “አበያዋን” እና ከፍ ሲል የተንጨፈረረ ጸጉሯን እያየሁ ፈዝዠ ቀረሁ … ከድንጋጤና ከፍርሃት ለአፍታ ነፍሴ መለስ ሲልልኝ ጠደፍ ጠደፍ ብየ ወደ ሔደችበት አቅጣጫ ተከተልኳት … ርቃኛለች … ሮጨ ልደርስባት ባለመቻሌ መኪናየን ወዳቆምኩት በመሔድ አስነስቸ ተከተልኳት … በደቂቃዎች ልዩነት ተሰወረችኝ! ምናልባት በዙሪያው በቆሙት መኪኖች መካከል፣ በመንገዱ ዳርም ሆነ በቤቶች አጥር ጥላ ፈልጋ ደክሟት አረፍ ብላ እንደሆነ በማለት መኪናየን አቆሜ ፍለጋየን ቀጠልኩ … ብዙ ሞክሬ አልተሳካልኝም … ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሰላም እያልኳት ገላምጣኝ የሄደቸው እህት የለችም!
በትካዜ ተውጨ በአሳቻ መንገድ አገኛት እንደሁ በሚል ዙሪያ ገባው እያማተርኩ ሳቀና ከጅዳ ቆንስል ግቢ በግምት 600 መቶ ሜትር ርቀት በአንድ አረብ ቱጃር ቤት አጥር ስር በሚገኝ አንድ ዛፍ ስር፣ ከመንገዱ ዳር አንዲት እህት ወድቃ ተመለከትኩ! ክው ክው ብየ ደነገጥኩ … ተጠጋኋት! የሚያምረው አይኗ ወይቧል፣ ሰውነቷ ደግሞ ዝላለች፣ ላብ ፊቷን አውዝቶታል፣ አፏ ግን አመድ መስሎ ደርቋል!  ጠይም ባለ ሰልካካዋ አፍንጫ ለግላጋ መልከ መልካሟን እህት ከብዙ ጉትጎታ በኋላ ማውራት ቻልኩ … ለነገሩ ማውራት አይባልም! ለረጅም ደቂቃዎች ለማውራት ያደረግኩት ሙከራ በሰጠችኝ ጥቂት መልስ አፏ ተፈታ ማለቱ ይቀላል! ዝርዝር ማውራት ግን አትፈልግም … ምንም አይነት እርዳታ እንደማትፈልግ በአጭሩ ገለጸችልኝ! … በቃ ከዚህ ባለፈ ብዙ ማውራትና መቀጠል አልቻልኩም!  የማደርገው ባጣ ቢያንስ በቆንስሉ መጠለያ ግቢ ከታጨቁትና በከፋ አደጋ ላይ እንዳሉ ከሰማሁትና አይቸ ካረጋገጥኩት 150 ከሚሆኑት ተፈናቃዮች ጋር ቢደባልቋት በሚል ለጅዳው ቆንስል ሃላፊ ለአቶ ዘነበ ከበደና ለዲያስፖራው እና በመጠለያ ላሉት ተፈናቃዮች እህቶች ተጠሪ ዲፕሎማት ለወ/ሮ ሙንትሃ ደጋግሜ ስልክ ደወልኩላቸው አያነሱም …
የማደርገውን እያሰላሰልኩ ሳልራመድ በአጋጣሚ አይኔን ወደ ቀኝ አሻግሬ ስመለከት አንድ ሌላ እህት ከቅርብ ርቀት ወድቃ ተመለከትኩ … ይህችው እህት በቁራጭ ካርቶን ቢጤ ተቀምጣና ጀርባዋን ለመንገዱ ሰጥታ እጇን እያፍተለተለች ትዘፍናለች ትስቃለች! ይህችንም ደጋግሜ ጠየቅኳት እየገላመጠች እያየችኝ መልሳ ትስቅና ትዘፍናለች! ዘፈኑ ኦሮምኛ መሆኑን እንጅ ዘፋኝና ትርጉሙን አላውቀውም! …  ፈዝዠ ቀረሁ!
saudi 2ደጋግሜ ወደ ቆንስሉ ሃላፊዎች፣ ወደ ኮሚኒቲ ሹሞች ብደውልም ስልኬን አይመልሱትም! … እንዲህ ስባዝን አንድ ለቆንስል እና ከኮሚኒቲ ሃላፊዎች ቅርበት ያለው ወንድም ከበስተኋላየ መጥቶ ጀርባየን ቸብ አድርጎ አስደነገጠኝ!  ድንጋጤየ ገርሞት “አቶ ነብዩ ምነው? ደነገጥክኮ!” አለኝ በአግራሞት እንደ መሳቅ እያለ  … የደነገጥኩት ከበስተኋላ የተኛቸው እህት ተነስታ የነረተችኝን መሰሎኝ መሆኑን እውነቱን ገልጨለት እንደ ቀልድ አድርገን ተሳሳቅን፣ ብዙም ሳንቆይ ስለ ወደቁት ለእህቶች አንስተን ተጨዋዎትን … ወዳጀ በቅርብ ርቀት የወደቁ እህቶች እያሳየኝ እንዲህ አለኝ “አየህ ይህችኛዋ ለሶስት ቀናት አንዴ እዚህ ትወድቃለች አንዴ እዚያ ታገኛታለህ ፣ ያችኛዋንም እንደዚያው …” ብሎ ሊቀጥል ሲል በጥያቄ አስቆምኩት ታዲያ ምን አደረግክ?  “እኔ ምን አደርጋለሁ!  የእኛ ዜጋ ረክሷል እኮ … እስኪ ወደ መጠለያውና ግባ፣ ያበዱ የታመሙ ደህና መጥተው በመጠለያው የሚያብዱትን ሲያዩ እነሱም የሚያብዱት ቁጥር እኮ ቀላል አይደለም!” ሲል የመርከሳችን ነገር ሊያስረግጥልኝ ሞከረ!   ግን ይህንን ስታይ ለምን ወደ ምትቀርባቸው ሃላፊዎች ደውለህ አታስረዳቸውምና ሌላው ቢቀር ከግቢው ውስጥ ከተደባለቁ ይበዱም ይሙቱ ማንነታቸው ቢያንስ ይታወቃል?  አልኩት፣ ከግቢ ውጭ እንዲህ ሲወድቁ የሚከተልባቸው አደጋ እንደሚከፋ፣ ከወራት በፊት ከቆንስሉ እና ከመጠለያው ግቢ በር  ካለው ዛፍ ራሷን ሰቅላ ስለሞተቸው፣ ከቅርብ ርቀር ከሚገኘው ሌላ ዛፍ ወድቃ ስለሞተችው እህት የሚያውቀው የምናውቀውን አሳዛኝ ክስተት ለማስረዳትም ላማስረዳትም  እየሞከርኩ ብየ አከልኩለት … አይገባህም እንደ ማለት የለበጣ ሳቁን ከፊቱ ላይ እየነሰነሰ ምላሽ ንግግሩን  ቀጠለ …  “ያንተ ነገር እኔ መቸም እንዳንተ አላበድኩም፣ ፓስፖርት ማደስ፣ ቤተሰቦቸን ሃገር ቤት ሔጀ መጠየቅ እፈልጋለሁ፣ አንተ እንኳ ዱላውንና መገፋቱን ለምደህዋል፣ በል አሱን ተወው!” ሲል እያሳሳቀ ደገመና “እንዳንተ መች አበድኩ!” ብሎኝ አረፈው …
ፍርሃትን ፈርቶ ሰብዕናውን የደፈጠጠበት ይህ አጋጣሚ ቢያስቆጣኝም የተሰማኝን አፈንድቸ ወዳጀን ላስበረግገው አልፈለግኩም … እንዲያውም ላግባባው ሞከርኩ … ለሁሉም እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲያጋጥም አንድም ለሃላፊዎች አለያም ያገባኛል ለምንል ሰወች መረጃውን ብታቀብሉን መልካም ነበር በማለት ሃላፊዎች ለማግኘት እና ለማሳወቅ ፈልጌ አይመልሱም ብየ ወሬየን ሳልጨርስ ንግግሬን ከአፌ አቋረጠው እና መለሰልኝ “አትድከም ማናቸውም ላንተ አይመልሱልህም፣ እያጋለጥካቸውና ድክምታቸውን ለአለም እያሳየህ ባይመልሱልህ አይደንቀኝም፣ በነገራችን ላይ ሳልፈልገው ልንገርህ አስገደድከኝ፣ ባለቤቴ የፌስቡክ ጓደኛህ ነች፣ በጣም ትከታተልሃለች፣ ታከብርሃለች፣ ባንተ ነገር ሁሌ እንጣላለን። እኔ በሃላፊዎች አካባቢ የምትባለውን ስለምሰማ ለእለት ጉርሱ ሳያነሰው ለምን ይጽፋል፣ ለምን ከመንግስት ጋር ይፋጠጣል፣ ልጆቹን ለምን አርፎ አያሳድግም ባይ ነኝ። እርሷ ግን በእኔ ሃሳብ ፍጹም አትስማማም። መረጃውን የሚቀበል አጣ እንጅ ጠቃሚ ነው ትላለች። እኔም የምለው ያንን ነው ሰሚ ሳይገኝ መጮህ አንተን ይጎዳሃል ባይ ነኝ … እና ብዙ ጊዜ በዚህ ተጣልተን ሁሉ እናውቃለን። አንድ በቅርቡ የሰራችውን ልንገርህ … ከሁለት ቀን በፊት ስለ መጠለያው ቪዲዮ በፌስቡክ መልዕክት መቀበያ አልደረሰህም?” ሲል ጠየቀኝ፣ ማን እንደላከው ንገረኝና ልነገርህ አልኩት፣ ነገረኝ፣ መረጃው እንደደረሰኝ አረጋገጥኩለት፣ ተግባባን … ንግግሩን ቀጠለ …saudi 3
“አየህ ሚስቴ እኔ እንድታየው ብሰጣት ላንተ ላከችልህ። ያበዱትን እና በጸሃይ ላይ የሚንቀለቀሉ እህቶች ቢያሳዝኑኝ፣ በቅርቡ በድብቅ በመጠለያው ያነሳሁት ነው። እንግዶች ሃገር ቤት ይመጣሉ ስለተባለ እና ለሃላፊዎች ሁኔታውን ለማሳየት ያነሳሁትን ቪዲዮ ነው!” ብሎ በጠራራው ጸሃይ አቁሞ ካወራኝ በኋላ ከእኔ ጋር እዚህ አካባቢ መቆሙን ከአሸባሪ ጋር እንደ መተባበር ይቆጠራል የሚል በነገር ቀልድ ሸንቁጦኝ መልሴን ሳይጠብቅ እየሳቀ ተሰናብቶኝ እየተጣደፈ ወደ ቆንስሉ ግቢ አመራ  …
ፊቴን ወደ ወደቁት ሁለት እህቶች መለስ ቀለስ እያደረግኩ ብቻየን ቀረሁ! የማደርገው ጠፋኝ … አሁንም መልሸ መላልሸ ወደ ቆንስል ሃላፊዎች ደወልኩ … ወዳጀ እውነቱን ነው፣ አያነሱም!… ሁሌ ሲከፋኝ እና መፍትሔ ሳጣ የምጠይቀውን ጥያቄ ራሴን ጠየቅኩት … ግን ለምን?  አልኩ … መልስ ባላገኝም …!
ብዙም ሳልቆይ ወደ ቆንስሉ ግቢ አመራሁ፣ ወደ ግቢው ዘልቄ ገባሁ፣  ግቢው በሰው ተሞልቷል። ኢትዮጵያዊው ወገን የሳውዲ ምህረት አዋጅ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከመጠናቀቁ በፊት የተለያዩ ሰነዶችና አገልግሎት ፈልጎ የመጣ መሆኑን አውቃለሁ፣ እኒህኞቹ ችግር ቢገባኝም፣  ዛሬ አንገብጋቢ ሆኖ አልታየኝም። ተጋፍቸ ወደ ቆንስል ሃላፊው የሚወስደው በር ብደርስም ወደ ፎቅ የሚወስደው በር በካሜራና በአውቶማቲክ በር ተጠርቅሟል። የበሩን መክፈቻ በመጫን አያንጫረርኩት ለማስከፈት ሞከርኩ፣ አልተቻለም … ተሰላችቸ ልመለስ ስል መልስ ተሰጠኝ “ሁሉም ዲፕሎማቶች ስብሰባ ላይ ናቸው”  የሚል መልስ! ከቶ ለማን ይሆን የሚሰበሰቡት?  አልኩ … ለእኛ መሆኑ አልዋጥልህ አለኝ እና እያጉረመረምኩ ግቢውን ለቅቄ ወደ መጠለያው አመራሁ …
ወደ መጠለያው ከመግባቴ በፊት ወድቀው ያየኋቸውን እህቶች ለማንሳት ከመጠለያው በር ያገኘኋትን እህት ትተባበረኝ ዘንድ ለምንኳት፣ “እሽ!” አለችኝ! ተያይዘን ወደ ወደቁት እህቶች  አመራን … አገኘናቸው አግባብተን ማስገባት ቀርቶ ማነጋገር አልቻልነም …  ይህች እህቴ ያየችውን ማመን አቅቷት በእንባ ተሞላች፣ ሳታስበው ሃዘን ውስጠ ከተትኳት፣ አዘንኩ! እሷኑ አይዞሽ ብየ ሸኝቸ፣ ለራሴው ሰላም አጥቸ ወደ መጠለያው አመራሁ …
ከዚህ ቀደም በደረሰኝ መረጃ የተመለከትኳቸው ያበዱ የታመሙትን ጨምሮ ጤነኞች ተፈናቃይ እህቶች ከግቢው ፈሰው ተመለከትኩ … ልብስ ታጥቦና ሳይታጠብ እንደ ሃገር ቤት በየአጥሩ፣  በደረጃው፣ በመሰላሉና በበሮቹ ላይ ተሰቅሏል … ሻንጣው በአንድ ጥግ ተከምሯል … ይህን ጨምሮ አሳዛኙን የተፈናቃዮች ውሎ በፎቶ ሆነ ቪዲዮ ማንሳት ክልክል ነው ስለተባለ ማንሳት አልፈልግኩም! ግቢው ጉስቁልናቸው ከፊታቸው በሚነበብ እህቶች፣  ባዘኑ በተጨነቁ፣ በውስጥ ደዌ የተደቆሱ፣ በአዕምሮ ጭንቀት በተለከፉ፣ በተዳከሙ፣ ተስፋ በቆረጡ እህቶች ጢም ብሎ ሞልቷል፣ ወደ 150 ደርሰዋል፣ የሚያድሩት በጠባቧ ክፍልና ሜዳ ላይ እንደሆነ ሰምቻለሁ … ያየሁት አንገቴን አስደፍቶ አሳፈረኝ!  ወደ ካፍቴሪያው ዘለቅኩ …
በካፍቴሪያው እንደገባሁ መቀመጫ ስፈልግ ቅድም በር አግኝቸው የነበረው ወንድምና ካፍቴርያውን ሳይሳለሙ ውለው ከማያድሩት ሌሎች ባልንጀሮቸ ተቀምጦ አየሁት … የደመቀ ወሬ ይዘዋል።እንዴት እንዳየኝ ባይገባኝም እጁን እያወናጨፈ ጠርቶ እንድቀመጥ ጋበዘኝ! ራመድ ራመድ ብየ ሄጀ ሰላምታ ከተለዋዎጥኩ በኋላ ተቀመጥኩ፣ ከቀናት በፊት በካፍቴርያው ያለውን የሟች ጠቅላይ ሚኒስትርን ፎቶ በቦርሳዋ ስትደበድብ ያየኋት እህት በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከጓኛዋ ጋር ተረጋግታ ተቀምጣለች። ዛሬ ተሽሏታል ብየ ሳላበቃ “ወግዱልኝ!” ብላ አምባርቃ ጮኸች …  ከወዳጆቸ ጋር ወንበር ስቤ ከተቀመጥኩባት ቅጽበት እስክነሳ በጠረጴዛው ይወራ የነበረውን ወሬ ለመጻፍ ግን ይከብደኛል … ብቻ በግቢው ችግረኛ ግፉዕ ወገን እየተንገላታ እንደሆነ ተረስቷል … ሰብዕና ሳይሆን ተራ የፖለቲካ ቡትቶ ጉዳይ ሆኖ እና የባጥ የቆጡን  ወሬ እያመጡ የማውራቱ እና የመፈላሰፉ ወሬ ግን ያስጠላል …. በሽታ ሆነኝ …
ከቶ ይህ መከራ እየታየ እንዴት ይታረፋል! ብጣቂ መረጃ እንኳ እንካችሁ! ከእረፍት ስመለስ ከደረሰኝ እና ከማውቀው መረጃ አልፎ አልፎ ጨልፊም ቢሆን በቅርቡ ሳላስቃኛችሁ አልቀርም …
ለሁሉም አንድየ ቸር ያሰማን! የምስራች የምናዎራ ያድርገን!
ነቢዩ ሲራክ

ከእሁድ እስከ እሁድ


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች ከተለያዩ ምንጮች)
mk


“መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤ መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ” በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤ በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ፣ በርካታ ጳጳሳት ተሳትፈውበታል፡፡ መጽሐፉ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየታተመ ሲሆን በዚህ ሳምንት ከተጠናቀቀ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ሊመረቅ እንደሚችል ታውቋል፡፡ (አዲስ አድማስ)
በኬንያና በዚምባብዌ የታሠሩ ኢትዮጵያውያን ይከሰሳሉ ተባለ
በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያና ወደ ዚምባብዌ ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘው የታሰሩ መቶ ያህል ኢትዮጵያውያን ክስ ይጠብቃቸዋል ተባለ፡፡
ሰሞኑን ወደ ናይሮቢ ሊገቡ ሲሉ በፖሊስ የተያዙት ሀምሳ ሶስት ወጣት ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ፓስፖርት እንደሌላቸውና ከአማርኛ ውጪ በእንግሊዝኛ መግባባት እንደማይችሉ የሳምራ ፖሊስ ኮማንደር ኤል ሙታሚያ ተናግረዋል፡፡ ከስደተኞቹ ጋር፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚያካሂዱ ደላሎች ናቸው የተባሉ ኬንያዊያንም ታስረዋል፡፡Ethiopia, Abudrafi, treating kala azar and HIV, November 2010.
በሌላ በኩል የዚምባቡዌን ድንበር አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄዱ የነበሩ ሰላሳ ስምንት ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ ፖሊስ ተይዘዋል፡፡ ወጣት ስደተኞቹ ወደ ዙምባብዌ የገቡት በህገወጥ መንገድ ስለሆነ ክስ ይመሰረትባቸዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ በኬንያና በዙምባቡዌ ለታሰሩ ስደተኞች ከመንግስት እገዛ ይደረግላቸው እንደሆነ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው፣ “መንግስት ሁልጊዜም ዜጐቹን የመርዳት ፍላጐት አለው፤ በየአገሩ ያሉ ኤምባሲዎቻችንም በዚህ ፖሊሲ መሰረት እየሰሩ ነው” ብለዋል፡፡
በቅርቡ የወጣው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መረጃ እንደሚለው በየአመቱ ከሀያሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያዊያን በኬንያ በኩል ደቡብ አፍሪካ ይገባሉ፡፡ (አዲስ አድማስ)
አውራምባ ታይምስ አገሯ ገባች
ኢህአዴግ ለህይወቴ ያሰጋኛል በሚል አሜሪካን አገር ከላላ አግኝቶ የነበረው የአውራምባ ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ አቶ ዳዊት ከበደdawit k አገሩ መግባቱ ተገለጸ። ዳዊት በ1997 ምርጫ ወቅት ከታሰሩት ጋዜጠኞች ጋር እስር ቤት ነበር። ከሌሎች የሙያ ባልደረቦቹ ጋር ከእስር ሲፈታ ሌሎች በሙያቸው ለመስራት ጠይቀው ፈቃድ ሲከለከሉ ዳዊት ግን ዳግም የጋዜጣ ፈቃድ ማግኘት ችሎ ነበር። ከእስር መልስ ከሁለት ዓመት በፊት ከዳዊት ጋር ኢህአዴግን በመሸሽ የተሰደደችውን አውራአምባ ታይምስን ወረቀት አልባ በሆነ መልኩ አቋቁሞ የነበረው ዳዊት ወደ አገር ቤት ለመመለሱ የሰጠው ምክንያት የዲያስፖራው ጽንፈኛ አስተሳሰብና መወቀስን አለመውደድ አንደሆነ አስታውቋል። ጋዜጠኛነት አሸባሪነት በሆነባት ኢትዮጵያ ዳዊት ሥራው ያለው እዚያ ነው ቢልም “ዳያስፖራውን በጥብጦ ሲያበቃ ተልዕኮውን አሳክቶ ተመለሰ” ብለውታል፡፡ በስፋት የተቃውሞ አስተያየት የሚሰነዝሩበት ክፍሎች ግን “ስለከሸፈበት አገሩ ተመልሶ ኢህአዴግን ተቀላቀለ፤ አድዋ ገባ” ብለውታል።
ኢዴፓ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እውቅና ጠየቀ
በገዥው ፓርቲ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኢዴፓ ባካሄደው ግምገማ፣ ኢሕአዴግ የአገሪቱን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለና እያጠናከረ ከመሄድ ይልቅ፣ ይበልጥ እየተዳከመ እንዲመጣ ማድረጉን ገልጿል፡፡ ገዢው ፓርቲ ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ለዴሞክራሲ ሥርዓት መጠናከር ምንም ዓይነት ተጨባጭ ዕርምጃ እየወሰደ እንዳልሆነና ይህም በአገሪቱ የጽንፈኝነት ፖለቲካና አክራሪነት የበለጠ እየተጠናከረ እንዲመጣ አድርጓል ይላል የኢዴፓ ግምገማ፡፡
“በአሁኑ ወቅት በአገራችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሙስና፣ የፖለቲካ ጽንፈኝነትና አክራሪነት ለዘለቄታው ዕድገት ብሎም ለሰላምና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት በመሆን፣ አገራዊ አደጋ እየሆነ መጥቷል፤” ይላል ኢዴፓ ገዢው ፓርቲን በገመገመበት ወቅት የደረሰበትን ድምዳሜ ሲገልጽ፡፡edp
ኢዴፓ በጉባዔው ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ተችቷል፡፡ ተቃዋሚዎች የኢዴፓን የተቃዋሚነት ሚናና ህልውና የካዱና፣ በሕዝቡ ዘንድ በበጎ መንፈስ እንዳይታይ ሆን ብለው ሴረኛ አሉባልታዊ ዘመቻ የሚያካሂዱ መሆናቸውን መገንዘቡን ገልጿል፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች የወቅቱ ትግል ተጠናክሮ ለድል እንዳይበቃ ዋነኛ እንቅፋት መሆናቸውን ገልጾ ሕዝቡ የእነዚህን ተቃዋሚ ኃይሎች ትክክለኛ ማንነት እንዲገነዘብ ጠይቋል፡፡
በመቀጠልም ተቋዋሚ ፓርቲዎች ራሳቸውን ቆም ብለው መመርመርና ካለፈው ስህተታቸው መማር ካልቻሉ በስተቀር፣ በትብብር ለመሥራት ሙከራ እንደማያደርግና ከዚህ ተግባራቸው ተላቀው ዕውቅና እንዲሰጡት ኢዴፓ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የኢዴፓ ሥራ አስፈጻሚ የጠቅላላ ጉባዔውን አቋም ከገለጸ በኋላ ከጋዜጠኞች ለቀረቡለት ጥያቄዎች ማብራርያ ሰጥቷል፡፡ ከቀረቡለት ጥያቄዎች መካከል ከፀደቀ ጊዜ ጀምሮ መነጋገሪያነቱ ያልቀዘቀዘው የፀረ ሽብርተኝነት ጉዳይ ላይ ኢዴፓ ያለውን አቋም እንዲገልጽ የቀረበው አንዱ ነው፡፡የፓርቲው አዲሱ ፕሬዝዳንት አቶ ጫኔ ከበደ እንደገለጹት፣ ኢዴፓ የፀረ ሽብር ሕጉን ይደግፋል፡፡ ሥልጣን ቢይዝ የፀረ ሽብር ሕጉ እንደሚያስፈልገው አቶ ከበደ ገልጸው፣ ነገር ግን መሻሻል ያለባቸው ነጥቦች መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡
መሻሻል ካለባቸው ነጥቦች መካከልም ሰብዓዊ መብቶችን የሚጥስ ይዘት ያላቸው ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ነጥቦች ሕጉ አቅጣጫውን እንዲስት ማድረጋቸው አቶ ጫኔ ገልጸዋል፡፡ለዚህም ማሳያው ጋዜጠኞችና መብታቸውን የሚጠይቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡ (ሪፖርተር)
አየር ሃይል አዲስ አዛዥ ተመደበለት
የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ለስልሳ ከፍተኛ መኮንኖች የጀነራልነት ሹመት ያደለው ኢህአዴግ በመከላከያና በደህንነት ተቋማቱ ሃላፊዎች ዙሪያ ሹም ሽር እንደሚያደርግ በተለያዩ መንገዶች ሲገለጽ መሰንበቱ ይታወቃል። በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የአንድ ብሄርና የህወሃት አባላት ብቻ አመራሩን መያዛቸው ቅሬታ መፍጠሩም በስፋት እየተነገረ ይገኛል።
eth afይህንን ተከትሎ ኢህአዴግ የጀነራሎች አዲስ ሹም ሽር ማካሄዱን አዲስ አድማስ ምንጮቹን ገልጾ አስታወቀ። ጋዜጣው እንደጠቆመው የአየር ሃይል አዛዥ በመሆን ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ ተሹመዋል። በቀድሞው የአየር ሃይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ  የተሾሙት ጀነራል አደም የአየር ሀይል ፓይለት የነበሩና በሱዳን አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ፣ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ እንደነበሩ ጋዜጣው አመልክቷል።
በሌሎች የመከላከያ የስራ ምድብ ቦታዎች ላይ የአዛዦች የምደባ ለውጥ ተደርጓል።  አዲስ የሀላፊነት ምደባ ከተሠጣቸው ውስጥ ሌተናል ጀነራል ሠአረ መኮንን፣ ሌተናል ጀነራል አበባው፣ ሜጀር ጀነራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ያስታወቀው አዲስ አድማስ የሃላፊዎቹን የሹመት ምድብ ቦታ አላስታወቅም።
በርሊን፤ የሜርክል የእጅ ስልክና አሜሪካ
የጀርመን መራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል የእጅ ስልክ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የስለላ ተቋም ተጠልፏል የሚለዉ ዜና እያነጋገረ ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ድርጊቱን እንዳልፈፀመች በመጥቀስ አስተባብላለች። ጉዳዩ በአውሮጳ መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል።
ጀርመን የመራሂተ መንግስቷ ስልክ ሳይሰለል አይቀርም በሚል በበርሊን የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርን ዛሬ ለማነጋገር መጥራቷ ተዘገበ። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በጀርመን ለአሜሪካኑ አምባሳደር ጆን ኤመርሰን በዚህ ረገድ የጀርመንን ግልጽ አቋም እንደሚያቀርቡም ተገልጿል። የጀርመን መገናኛ ብዙሃን የአሜሪካን የስለላ ተቋም NSA የመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን የእጅ ስልክ ሳይጠለፍ አልቀረም የሚል መረጃ ይፋ አድርገዋል። ዋሽንግተን ግን አስተባብላለች። ይህ ከተሰማ በኋላም ሜርክል ራሳቸዉ ለፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ስልክ በመደወል የተባለዉ እዉነት ከሆነ ፍፁም ተቀባይነት የለዉም ማለታቸዉን ቃል አቀባያቸዉ ሽቴፈን ዛይበርት ገልጸዋል። የመከላከያ ሚኒስትር ቶማስ ደሚዚየር በበኩላቸዉ፤ “የሰማነዉ እዉነት መሆኑ ከተረጋገጠ በጣም መጥፎ ነዉ። አሜሪካዉያን እዉነተኛ ጓደኞቻችን ነበሩ አሁንም ናቸዉ፤ ሆኖም እንዲህ ሊቀጥል አይችልም።”am
ኋይትሃዉስ ኦባማ ትናንት ከሜርክል ጋር ባደረጉት የስልክ ዉይይት የአሜሪካን የስለላ ተቋም እሳቸዉን እንደማይሰልል ማረጋገጣቸዉን ቢገልጽም ከዚህ ቀደም ስለመደረጉ ያለዉ የለም። የኋይት ሃዉስ ቃል አቀባይ ኤይ ካርኔ፤
“እኔ ልገልጽ የምንችለዉ ፕሬዝደንቱ ዩናይትድ ስቴትስ መራሂተ መንግስቷን በወቅቱ እንደማትሰልል፤ ወደፊትም እንደማትሰልል እንዳረጋገጡላቸዉ ነዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ከጀርመን ጋ ሰፊ የጸጥታ ችግሮችን በተመለከተ ላለን የቀረበ ትብብር ትልቅ ዋጋ ትሰጣለች።”
ስለሜርክል ሞባይል መጠለፍ የተሰማዉ የNSA በቀድሞዉ ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖዉደን ጉዳዩን አጋልጦ በርካቶች መራሂተ መንግስቷ ነገሩን ያደባብሳሉ የሚል ጥርጣሬ እየተሰነዘረ ባለበት ወቅት ነዉ። የስልካቸዉ መጠለፍ ያስቆጣቸዉ ሜርክል በሳምንቱ መጀመሪያ ከ70 ሚሊዮን በላይ የስልክና ኢሜል ልዉዉጦች መጠለፋቸዉ ካናደዳት ፈረንሳይ መሪ ፍራንስዋ ኦሎንድ ጋ በጉዳዩ ላይ ዛሬ እንደሚነጋገሩ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ከብራስልስ ዘግቧል።
am1ይህ በእንዲህ እንዳለም ብራስልስ ላይ የተሰባሰቡት የአዉሮፓ ኅብረት አባል መንግስታት መሪዎች የግለሰብ ዜጎችም ሆነ የመሪዎች የግል ጉዳይ ላይ የሚደረግ ስለላ ተቀባይነት እንደማይኖረዉ አመልክተዋል። የፈረንሳይ የዜና ወኪል የኅብረቱ የፍትህ ኮሚሽነር ቪቫነ ሬዲንግ ቃል አቀባይ ኮሚሽነሯ መረጃን የመከላከል ርምጃ የአንጌላ ሜርክል የእጅ ስልክንም ሆነ የግለሰብ ዜጎችን የኢሜል ልዉዉጥ ላይ በእኩልነት ተግባራዊ ልሆን ማለታቸዉን ዘግቧል። ኮሚሽነሯ የኅብረቱ ጉባኤ ማብራሪያ የሚጠይቅበር ሳይሆን ርምጃ የሚወስድበት ጊዜ አሁን ነዉ ማለታቸዉም ተጠቅሷል። ከወራት በፊት ለአዉሮፓ የመረጃ መከላከል ህግ እንዲጸድቅ ቀርቦ 28 አባል መንግስታት በጉዳዩ ልዩነት ስለነበራቸዉ ታግዷል። የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽነር ሆሴ ማኑዌል ባሮሶም በበኩላቸዉ አዉሮጳዉያን የግለሰብን የግል ጉዳይ ማክበርን እንደመሠረታዊ መብት ይመለከቱታል ነዉ ያሉት። የኅብረቱ አባል ሃገራት መሪዎች ዛሬ እና ነገ የኤኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ጉባኤ ለማካሄድ የተሰባሰቡ ሲሆን የጀርመን መራሂተ መንግስት ስልክን የመጠለፍ ወሬ ትኩረታቸዉን ወደሌላ ሳይስብ እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። (ከጀርመን ሬዲዮ የተወሰደ)
ሶስት የአማራ ክልል አመራሮች ታገቱ
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ በአማራ ክልል ላኩማ ወረዳ ሁለት የሚሊሽያ ሀላፊዎችንና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪን በቁጥጥር ስራ ማገቱን ኢሳት ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ ም አስታወቀ።
ንቅናቄው ቀደም ሲል  22 የፖለቲካ አመራሮች በላኩማ ወረዳ በሚገኘው በሰላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ መልቀቁን ገልጾ፣ ሶስቱን አመራሮች ግን አሁንም ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጎ እንደሚገኝ
ኢሳት አመልክቷል። የተያዙት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት ፓለቲከኞች ዋነኛ እና የአካባቢውን ህብረተሰብ በመበደል የሚታወቁ እንደሆነ ንቅናቄው አመልክቷል፡፡
አቶ አልዩ ጋሹ የላኩማ ወረዳ አስተዳደር ስብሳቢ፣ አቶ አንበሱ በዙ የሰገላ ወረዳ ሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊ፣ እንዲሁም አቶ ኢያና ካሳ የባምበል ወረዳ ሚሊሽያ ዘርፍ ሀላፊ ሶስቱም በቁጥጥር ስር የሚገኙ ሀላፊዎች እንደሆኑ ንቅናቄው መግለጹኢነ ያመለከተው ኢሳት ዜናውን ከገለልተኛ አካል አለማረጋገጡን ጠቁሟል።
ላኩማ ወረዳ ብዙ የሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት ያለባት ስፍራ እንደሆነች የገለጸው ንቅናቄው ከዚህ በፊት የአካባቢውን ሰዎች ሲያጉላላ የነበረ ሀላፊ እርምጃ ተወስዶበት እንደነበር አስታውሷል፡፡ ንቅናቄው በክልሉ ባሉ ህዝቦች ላይ የሚፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሰቃይ እንዲቆም መጠየቁንና የጎጃም ዞን ዋና የህወሀት ባለስልጣን በነበሩት አቶ ዳኘ ገብረማርያም ላይ በቅርቡ እርምጃ መወሰዱን መዘገቡን ኢሳት በዜናው አመልክቷል።