Sunday, October 27, 2013

ለወያኔ ፋሽስታዊ ግፍና የውገን ሰቆቃ ምላሽ መስጠት ይገባል

የሂውማን ራይትስ ዋች የሰሞኑ ዘገባ

በኤፍሬም የማነብርሃን

በዓለም ታዋቂው የሰብዓ መብቶች ትሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watch) ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ፡ የአፍሪቃ አንድነት ዋና ከተማ በምትባለው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እያካሄደ ያለውን የግፍ ግፍ ለዓለም አጋልጧል፡፡ በዚች ደቂቃ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ እየተባለ በሚጠራው የሰቆቃ ቦታ በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ለኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ክብር በሌለው የወያኔ ወንጀለኛ መንግስት ይህ ነው የማይባል ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል። በ”ሕጋዊ” መንገድ እንዲሰሩ “ተፈቅዶላችው” የሕዝቡን ሰቆቃ በመስማትና የሚፈጸመው ግፍና በደል እንዲቀርና በሰላማዊ መንገድ በውድ አገራችን ላይ ደሞክራሲ እንዲለመልም እየታገሉ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ፤ የወያኔ ፋሽስታዊ መንግስት በአንድ ወገን ዓለምን ለማታለልና ዲሞክራሲ እንዳለ ለማስመሰል ፓርቲ ማቋቋም ይቻላል ብሎ ካስወራ በኋላ፤ ከዓለም እይታ በስተጀርባ ግን ይህ ነው የማይባል ፋሽስታዊ ጭካኔ በንጹኅን ኢትዮጵያውያን ላይ እያካሄደ አንደሚገኝ የመብት ትሟጋች ድርጅቱ አጋልጧል። እንዲህ ያለ ወንጀል በውዲቷ ዋና ከተማችንና በታላላቆች የሃይማኖት መጻሕፍት በቅድስናዋ ደጋግማ በምትጠቀሰው አገራችን ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለን እናያለን? እያንዳንዱ እትዮጵያዊ ባለው ዐቅሙ ሊያደርግ የሚገባውን ለማድረግ ለምን አይረባረብም?
ይህ ግፍ በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸምባቸው የቆየ መሆኑን ከሥርዓቱ ተጠቃሚዎች በስተቀር ሁሉም የሚያውቀው ቢሆንም፡ እንደዚህ በዓለም ደረጃ ታውቆ በግላጭና ቁልጭ ብሎ መነገሩ ወያኔ አትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን፤ ከአሁን በኋላ የዓለምን ሕዝብ ጭምር አያታለለ ሊቆይ እንደማይችል ያስገነዘብው ዪመስለኛል። ለዚህም የሂውማን ራይትስ ዋችን በሚቻል ሁሉ መርዳትና ምስጋናችንንም ማቅረብ ይገባናል።
በተጨማሪም እያንዳንዱ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ “አሁንስ በቃ በጋራ እንኳን ምንም ማድረግ ቢያቅት በግሌ ማድረግ የሚገባኝን ማድረግ አለብኝ” ብሎ መነሳትና ይህንንም የግል ውሳኔ በስራ ለመተርጎም መወሰን አለበት፡፡ የግፉ አይነት፡ ብዛት፡ እና የጭካኔው መጠን ውስጣችንን የሚረብሽና ሰላምን የሚነሳ እንደመሆኑ መጠን፤ ይህን የውስጥ ንዴታችንን ወደ ወደተጨባጭ ትግል ለመቀየር በኢትዮጵያ ላይ ይግፍ መረቡን ዘርግቶ የተቀመጠውን ይሕን እርኩስ መንግስት ባለን ዐቅም ፊት ለፊት ተጋፍጠን “በዚህማ ልትቀጥል አትችልም ፡ይብቃህ እርኩስ ኃይል ይብቃህ“ ማለት መቻል አለብን።
በአገሪቱ ዋና ከተማ መሃል ላይ እንዲሁም ስላልታወቀ ነው እንጂ በጣም በብዙ የአገሪቱ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ይህን የመሰለ የግፍ ግፍ እየተካሄደ እያለና ሕዝቡ የመከራ ገፈፉን እየቀመሰ ያለ መሆኑን ሁላችንም በልባችን እያወቅነው እንዴት ብለን ቁጭ እንላለን፤ እንዴትስ በልተን ጠጥተን እንውላለን አናመሻለን፤ እንዴትስ ተኝተን እናድራለን፤ እንዴትስ ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰን፤ መስጊድ ተሳልመን ቤታችን እንገባለን፤ እንዴትስ አገር አለን ብለን ስለ አገር ዕድገትና ልማት እናወራለን፤ እንዴትስ ስለዚህ ወንጀለኛ መንግስት መልካምነት እንናገራለን።
ከሂውማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ትንሽ ቀንጨብ አድርገን እንመልከት፡፡
“ በኢትዮጵያ ከ1997ቱ አወዛጋቢ ምርጫ በኋላ በሰላማዊ ተቃዎሞ ላይ የሚደረገው ጫና ተባብሷል። በማዕከላዊ ተይዘው ምርመራ የሚካሄድባቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች … በተለይ በምርመራ ጊዜ ታሳሪዎቹ በጥፊ፣ በእርግጫ እንዲሁም በብትር እና በሰደፍ በተደጋጋሚ እንደተመቱ … ሰውነታቸውን ለህመም በሚዳርግ ሁኔታ እንዲሆኑና በተለይም እጆቻቸውን ከግድግዳ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ ተደርጎ ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ እንደሚደበደቡ ተናግረዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመጣ አንድ ተማሪ ብቻውን ተነጥሎና በሰንሰለት ታስሮ ለበርካታ ወራት እንዲቆይ እንደተደረገ ተናግሯል፡፡ ‘ለመቆም ስሞክር እቸገራለሁ፡ ለመቆም ጭንቅላቴን፣ እግሮቼን እና ግድግዳውን መጠቀም ነበረብኝ ፡፡ ምግብ ስመገብ እንኳ በሰንሰለት ታስሬ ነበር። ስመገብ እጆቼ በፊት ለፊት በኩል እንዲታሰሩ ይደረጋል ስጨርስ ደግሞ መልሰው ወደ ኋላ ያስሩኛል።’”
እንግዲህ ይህ መረጃ በአጋጣሚ ሕዝብ ዘንድ ወሬው ሊሰማ የቻለው ከእስር ወጥተው ለወሬ ነጋሪነት የበቁ ሰዎች ስለተገኙ ነው። ክዚህ ጀርባ እንዲህ ያልታወቁ፡ በድብቅ በአገሪቱ ዙርያ በወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቡድኖች በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸሙ ስፍር ቁጥር የማይገኝላቸው ወንጀሎች እንዳሉ መገመት አያዳግትም። ቤት ይቁጠረው። የወንጀለኞቹ መሪ መለስ ዜናዊ በተገኘበት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ወርቅነህ ገበየሁ በደህነነት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተናገረውን ለመጥቅስ ወያኔ እንደ ልዩ የስራ ችሎታው አድርጎ የሚትቀምበት ዘዴ “በተቀናጀ ኦፐሬሽን ለረጅም ጊዜ ለመንግስት ሥጋት ሆነው የቆዩ ሰዎች እንዲወገዱ” ማድረግ መሆኑን ወርቅነህ በኩራት ሲገልጽ ሁሉም በስብሰባው የነበሩ የምክር ቤቱ አባላት ከመለስ ጭምር የዜናው አስፈሪነትና ከባድነት ለመቅጽበት እንኳን በመንፈሳችው ውል ሳይል ስብሰባውን ሲቀጥሉ ታይተዋል።
በቅንጅት መሪዎች በተልይ ደግሞ በእህት መሪያችን በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተፈጸመውን ግፍና መከራ እንዲሁም በአሁኑ ውቅት በእስክንድር ነጋ፤ በአንዷለም አራጌ፤ ወዘተ በዚች ሰዓት የሚፈጸመውን ግፍና መከራ ሁሉም የሚያውቀው ነው ። በሞቱ የተገላገልነው መለስ ዜናዊና የወያኔ መንግስት በሃሰትና ውሽት ላይ የተመሰረተውን የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በማሰብ፤ የቅንጅትን መሪዎችን ለዓመታት በእስር ቤት በማንገላታትና በማሰቃየት፤ በጨለማ ቤት ለወራት በማቆየት፤ ከጉልበትና ከማስፈራራት በተገኘ የሃሰት የእምነትቃል ላይ እንዲፈርሙ በማድረግ በኢትዮጵያ ሕዝብና በደጋፊዎቻቸው ዘንድ እነዲጠሉና የመሪነት ድጋፋቸው እንዲቀንስና እንዲናቁ ያደረጉትን ሙከራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ነው።
ይህ የወንጀለኞች መንግስት በኢትዮጵያ ላይ በመሳርያ ኃይል ከተፈናጠጠ በኋላ አገሪቱን በዘር መከፋፈሉ፤ አገሪቱን ያለባሕር በር ማስቅረቱ፤ ለምለም የአገሪቱን መሬቶች ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱ፤ የአንድን አናሳ ብሔረሰብ አባላትን የኢኮኖሚው፡ የቢሮክራሲው፡ የሚሊታሪው፡ የፍርድ ቤቶች፡ የቤት ንብረትና መሬት ይዞታዎች የበላይ አስተዳዳሪና ባለቤት ወዘተ ማድረጉ፤ የአገሪቱን ብርቅዬ መምህራን ከዩኒቨርሲቲ ማፈናቀሉ፤ ሕዝብን ለምርጫ ካልወጣህ ካለ በኋላ መሸነፉን ሲያውቅ በዲሞክራሲ የተመረጡትን መሪዎች ማስገደሉ ማሰሩና ንጹሃን ወጣትና ህጻናትን መጨፍጨፉ፤ ሰሞኑን ደግሞ የወንጀለኛ ድርጅት አባል ካልሆናችሁ ስራ፡ እድገት አታገኙም ማለቱ ወዘተ አልበቃው ብሎ አስከፊ በሆኑት አሥር ቤቶቹ ውስጥ መሪዎችንና አዛውንቱን ለዚሕ ለሚዘገንን መከራና ሰቆቃ መዳረጉ ምን ያሕል ሕዝቡን የናቀ መሆኑን ያሳያል።
እንዲያውም ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚያበሳጨው መንግስቱ ኃይለማርያምን በኢትዮጵያውያን ላይ ትልቅ በደል ሰርቷል እያለ የሚያብጠለጥለው የወያኔ መንግስት፡ ከመንግስቱ ኃይለማርያም በማያንስ ጭካኔ ከፖለቲካ ልዩነት በቀር ምንም ያልሰሩ ንጹሃንን ይህን ለመሰለ ስቃይና መከራ የዳረጋቸው መሆኑ ነው። በተጨማሪም በመንግስቱ ኃይለማርያም የተጀመረው የዚህ ለመከራ የተዳረገ ሕዝብ ፍዳ በዚህ ዘረኝነት ባሰከረው የወንጀለኞች መንግስት በጣም በተራቀቀ ድርጊት መቀጠሉ “ያገር ያለህ” ወደሚያስብል ነጥብ ላይ አድርሶናል።
በተለይ ደግሞ በዚህ ኢንተርኔት፡ ተዟዟሪ ስልክ፡ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እና በአጠቃላይ የሚዲያ ቴክኖሎጂ በዓለም በተንሰራፋበት ዘመን የወያኔ መንግስት ኢትዮጵያውያን የዚህ ዕድገት ሙሉ ተካፋይና ተሳታፊ እንዳይሆኑ አፍኖ፡ የዓለምን ሕዝብ ይሉኝታ ሳይፈራ የጭካኔና የግፍ መረቡን በአገሪቱ ላይ ዘርግቶ በማናለብኝነት አስከፊ ሴራውን ሲያከናውን ለብዙ ኢትዮጵያውያን “አሁንስ አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የማያስብል ደረጃ የደረስን ይመስላል ። እስከመቼ ችለን ልናየውና የወያኔን የግፍ ቀንበር ተሸክመን ኑሮን መቀጠል እንደምንችል ማሰብና አስቸኳይ ውጤት ለማግኘት መረባረብ ይገባናል።
ይህን የሂዩማን ራይትስ ዋች ዘገባ ያነበብነውንና እንዲሁ እንደማንኛውም ዜና የምናልፈው መሆን የለበትም። ተጨባጭ የሆኑና የወንጀለኛው መንግስት እንዲሰማው የሚያስችሉ፤ ከባድ ያልሆኑ ነገርግን ተፈጻሚነት ሊያገኙ የሚችሉ፤ ሰላማዊ ዘዴና እርምጃዎች ላይ ተወያይተን በዝርዝር በማስቀመጥ በውጭ አገር ተቀማጭ የሆንነው ኢትዮጵያዊ ያን በስራ ልንተረጉማቸው ይገባናል። ለመነሻ፤ መወያያና መንደርደሪያ ያህል የሚከተሉት እነሆ።
1. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላዎች ከኢትዮጵያውያን የሚያገኙትን ገቢ ለመቀነስ፤ እነደ ፓስፖርት የማሳደስ ቪዛ የማስመታት፤ የውክልና ሰነዶችን የማጻፍ፤ ቤትና መሬት ለማሰራትና ለመግዛት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ወዘተ የሚጠይቁ ሥራዎችን ወደነዚህ የመንግስት አውታሮች ዘንድ ሄዶ ወይም በፖስት ቤት አማካኝነት ልኮ አለማሰራት።
2. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት በውጭ አገር በሚገኙ በግልጽ በወያኔ ካድሬዎች በሚንቀሳቀሱ ወይም የወያኔን ካፒታልና ቢዝነስ በሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ በማድረግ ምንም ዓይነት የዕቃ ግዢ ወይንም የገንዘብ ልውውጥ እንዲህ ካሉ ሰዎች ጋር ከማድረግ መቆጠብ። ይህንን ዐቀብ በምናካሂድበት ወቅት እንቅስቃሴው በዘር ላይ ያልተመሰረተና ያለበቂ ማስረጃ በአንድ ብሔር ተወላጆች ላይ ያላነጣጠረ እንዲሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ወደዚያ ዓይነት የትግል አቅጣጫ ሊመሩ የሚፈልጉትን ግለሰቦች በሙሉ መምከርና ካልሆነም መገሰጽ ይገባል።
3. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት የመንግስት አውታር ለሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሆነ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ለሚያደርሱ እንደ ዌስተርን ዩኒየን የመሳሰሉ ወደ ወያኔ ካዝና የውጭ ምንዛሪ (ፎርን ኤክስቼንጅ) በሚያስገቡ ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ ገንዘብ አለመላክና የሚኖሩበትን አገር ሕግ ሳይጥሱ በሌላ ዘዴ አገር ቤት ለሚገኝ ወዳጅ ዘመድ ብር መላክ።
4. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት የወያኔን ዓላማ በግላጭ ከሚያስፈጽሙ የወያኔ ካድሬዎች ጋር በማንኛውም አጋጣሚ ድጋፋቸውን የሚሰጡት መንግስት በደምና ግፍ የተጨማለቀ መንግስት መሆኑን ባላሰልሰ በማስረዳት ላጭር ጊዜም ቢሆን ከጋራ ተሳትፎ ማግለል። ይህንን ዐቀብ በምናካሂድበት ወቅት እንቅስቃሴው በዘር ላይ ያልተመሰረተና ያለበቂ ማስረጃ በአንድ ብሔር ተወላጆች ላይ ያላነጣጠረ እንዲሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ወደዚያ ዓይነት የትግል አቅጣጫ ሊመሩ የሚፈልጉትን በሙሉ መምከርና ካልሆነም መገሰጽ ይገባል።
5. ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አለመጠቀም። ወያኔ በአሁኑ ጊዜ የጭካኔና የግፍ ሥራውን ለማካሄድ ብዙ የገንዘብ ዐቅም ስለሚያስፈልገው ይህንን የገቢ ምንጩን መቀነስ ለትግላችን መፋጠን ይጠቅማል።
6. ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ መልካም ሥራ እያካሄደ እንዳለ ሊናገሩ የሚፈልጉ ሞኝና ተላላዎች አገሪቱ በደም የተነከረችና የንጹሃን ሰቆቃ የሚጮህባት አገር እንደሆነች ባላሰለሰ በመንገር በእጅ አዙር የወያኔ ቱልቱላ ቃል አቀባዮች እንዳይሆኑ መምከርና የኢኮኖሚ ዕድገትም እውነትነቱም ሆነ ተፈጻሚነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው የሰው ልጅ በሰውነቱ ሲከበርና ያች ሃገር የጥቂቶችና የዘረኞች ሳትሆን የሁሉ ኢትዮጵያዊያን በመሆኗ ጥቂቶች ዘረኞች የብዙዎችን መብት ረግጠው ላንተ እኛ ብቻ ነን የምናውቅልህ እያሉ የሚያናፍሱት ወሬ በሰለጠነው ዘመን ሊሰራና ሊቀጥል የማይችል ተራ ቱልቱላ መሆኑን እንዲገነዘቡ ማድረግ።
7. ወያኔ ሰሞኑን በዳያስፖራ የሚገኙትን የዋህ ኢትዮጵያውያን ገንዘባችውን ለመቀማት የያዘው ዘዴ “ኢትዮጵያ ውስጥ መሬትና ኮንዶ ለመሥራት ኢንዲያስችላችሁ 60/40 የሚባል ፕሮግራም ተዘጋጅቶላችኋል፤ 60 በመቶ (60%) በውጭ ምንዛሪ ካስቀመጣችሁ ቀሪዊን አርባ በመቶ (40%) በአነስተኛ ወለድ የሚከፈል ብድር አዘጋጅቼላችኋለሁ፤ ነገር ግን የውጭ ምንዛሪውን በቀጥታ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባችኋል” በማለት ኢትዮጵያውያንን በግፍ ቀንበሩ ለረጅም ጊዜ ሊይዝ የሚያስችለውን ሃብት ለመሰብሰብ ጥረት ኢያደረገ ስለሆነ ቢያንስ ለሶስት አለያም ለስድስት ወራትም ሆነ ለአንድ ዓመት ይህን ከመሰለ ለወያኔ የውጭ ምንዛሪ መሰብሰቢያ ማታለያ ዘዴ ውስጥ ከመውደቅ መቆጠብ።
እነኝህ ከላይ የተዘረዘሩት ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ ባጭሩ ለመስጠት የታቀዱ ናቸው እንጂ ሁሉንም ዘዴ አያካትቱም። የተለያዩ ኢትዮጵያውያን በዝርዝሮቹ ላይ ተጨማሪም ሆነ ማሻሻያ ወይም አዳዲስ ገንቢ ሃሳቦች ቢያቀርቡ ጥረታችን ውጤታማ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ፡
የወያኔ የክፋት የጭካኔና የበደል ቀንበር አንድ ቀን ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ ወድቆ ይፈጠፈጣል!!
የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የማለቂያው ቀን ሩቅ አይደለም!!
ውድ አገራችን ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!

የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሲ ትግርኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያዉያንን የበይ ተመልካች እያደረገ መሆኑን የግንቦት 7 ጥናታዊ ሪፖረት አጋለጠ


የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሲ ትግርኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያዉያንን የበይ ተመልካች እያደረገ መሆኑን የግንቦት 7 ጥናታዊ ሪፖረት አጋለጠ

ethio-metal-coorporation_jan_2013-small

ባለፈዉ ሳምንት ኢትዮ ተሌኮም ዉስጥ ስር እየሰደደ የመጣዉን የወያኔ ዘረኝነት በመረጃ በተደገፈ ጥናታዊ ዘገባ ለህዝብ ይፋ ያደረገዉ የግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ በተመሳሳይ ደረጃ አደረጃጀቱን፤ አወቃቀሩንና የሰዉ ኃይል አመዳደቡን ለአንድ አመት ሙሉ በቅርበት የተከታተለዉን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺንን ጥናታዊ ዘገባ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ አድርጓል። ለኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ግንባታ መሠረት ለመጣልና በአገሪቱ ኮንስትራክሺን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ታስቦ የተዋቀረዉ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን የኢትዮጵያ መሆኑ ቀርቶ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሀት መኮንኖች እጅ መግባቱን ያጋለጠዉ የኸዉ የግንቦት 7 ጥናት ኮርፖሬሺኑ ከዋና ዳይረክተር እስከ ተራ ቴክኒሺያኖች ስረስ የህወሀት አባል በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር ወድቋል ብሏል። የጥናቱ ሙሉ ዘገባ እንደሚገተለው ቀርቧል።

መነቀል ያለበት ስር የሰደደ የወያኔ ዘረኝነት  (ሙሉ ጥናቱን በPDF ከዚህ ላይ ዳውሎድ ማድረግ ይቻላል)

(በግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ የተጠናና የተዘጋጀ)

ዘረኛዉ የወያኔ ስርአት የኢትዮጵያን ህዝብ ለጥቂት አመታት ኢትዮጵያዊያንን ባሰረና በገደለ ቁጥር ገንዘብ የሚሰጡትን አለም አቀፍ ድርጅቶችና አርዳታ ሰጪ አገሮች ደግሞ 21 አመት ሙሉ ካታለለበት መንገድ አንዱ የፌዴራል ስርአት መስርቼ ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር አደረኳት የሚለዉ ባዶ አባባሉ ነዉ። ይህንን ተጋልጦ እርቃኑን የቀረ አባባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተገንዝቦ ወያኔን መታገል ከጀመረ ቆይቷል፤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ ለጋሾችም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ግድ የሌለዉ ወያኔ ወጣቶቻችንን እየገበረ ጥቅማቸዉን ስለሚያስከብርላቸዉ ነዉ እንጂ ወያኔ እንኳን እየደገፉ እርዳታ የሚሰጡት በአንድ ተርታም አብረዉ ለመቀመጥ የማይመች የእኩዮች ስብስብ እንደሆነ ካወቁ ቆይቷል።

ህወሀት በፌዴራል ስርአቱ ዉስጥ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ በሚጠራዉ ፓርላማ ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ 8 ብቻ ነዉ። እዚህ ፓርላማ ዉስጥ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ህወሀት ነዉ፤ ትግራይ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ክልል ናት። የተቀሩት 8 ክልሎች በዚህ የእኩልነት ምልክት በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ ያላቸዉ የመቀመጫ ብዛት 569 ነዉ። ሆኖም በወያኔ መንደር የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን ጠመንጃ ነዉና ወያኔ ፓርላማዉ  ዉስጥ 8 ወንበር ብቻ ይዞ 569 ወንበር ያላቸዉን የኦሮሚያን፤ የአማራን፤ የደቡብ ክልልንና የተቀሩትን አምስት ክልሎች እንደ መኪና ይነዳቸዋል። የየክልሉን መሪ ይሾማል፤ ይሽራል ወይም የማይስማማዉን የክልል ባለስልጣን ያስራል። ፓርላማዉ ዉስጥ አንድ መቶ ሰባ ስምንት፤ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንትና አንድ መቶ ሀያ ሦስት መቀመጫ ያላቸዉ የኦሮሚያ፤ የአማራና የደቡብ ክልል ፓርቲዎች በራሳቸዉ ጉልበትም ሆነ ህልዉና ስለሌላቸዉ አንዱ ከሌላዉ የበለጠ ስልጣን ወይም ሹመት ለማግኘት አንጋጥጠዉ ወደ ላይ የሚመለከቱት ህወሀትን ነዉ።

ለመሆኑ ወያኔ የፌዴራል ስርዐት መስርቼ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አረጋገጥኩ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? እኩልነቱ የፖለቲካ ነዉ  የኤኮኖሚ? ወይስ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ የፌዴራልዝም ቀን ሲከበር እንደምናየዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠዉ በዘፈን ብቻ ነዉ? የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዐት ከላይና ከታች የሚቆጣጠረዉና ይህንኑ የፖለቲካ ስርአት የሚደግፍ የኤኮኖሚ መዋቅር ዘርግቶ የአገራችንን ኃብት የሚቦጠብጠዉ ህወሀት ብቻ ነዉና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ተረጋገጠ የሚባለዉ አባባል ከተራ የቃላት ድርደራ ዉጭ ሌላ ምንም ትርጉም የለዉም።

አፄ ቴዎድሮስን እንደ ልጅነት ሞዴሉ የሚመለከተዉ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የመጀመሪያዉን የኢትዮጰያ ዘመናዊ ወታደራዊ እንጂኔሪንግ ተቋም ሲመሰርት ስሙን “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ ነበር የሰየመዉ። ስያሜዉ የአፄ ቴዎድሮስ ስራና ስም ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር ግልጽ ነዉ። የኢትዮጵያን የቀድሞ መሪዎች በጅምላ የሚዘልፈዉ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከአንዲት የአገር ዉስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ ያሰሩትን መድፍና መንግስቱ ኃ/ማሪያም “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ  የሰየመዉን ወታራዊ ተቋም አስመልክቶ ሁለቱንም መሪዎች ሲያንቋሽሽ ተደምጧል። የሚገርመዉ ዛሬ ወያኔ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺን ብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የሲቪልና ወታደራዊ እንዱስትሪ ተቋምና በዚህ ተቋም ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ፋብሪካዎች ደርግ  “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የጀመራቸዉ የከባድ እንዱስትሪ ጅምሮች ናቸዉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ስራዉን ሲጀምር የፋብሪካዉ ሀላፊዎች፤ እንጂኔሮች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና ቴክኒሺያኖች የስራ ዕድል የሚያኙት የትምህርት ደረጃቸዉ፤ ችሎታቸዉና የሰራ ልምዳቸዉ ብቻ እየታየ ነበር፤ ወይም ትግርኛ ስለተናገረ ስራ የሚከለከል አማርኛ፤ ኦሮምኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ስለተናገረ አድሎ የሚደረግለት ዜጋ አልነበረም። ዛሬ ወያኔ ከደርግ ስርአት ተረክቦ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ብሎ በሰየመዉ እንዱስትሪ ዉስጥ አብዛኛዉን የሀላፊነት ቦታ የያዙ ሰዎች ለቦታዉ የበቁት በስራ ልምዳቸዉና ችሎታቸዉ ሳይሆን የተወለዱበት ዘርና የሚናገሩት ቋንቋ እየታየ ነዉ። ወታራዊዉ አምባገነን ደርግም ሆነ  ወያኔ ይህንን እንዱስትሪ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት ይሆናል የሚል ራዕይ ነበራቸዉ። ልዩነታቸዉ የእንዱስትሪዉ አስፈላጊነት ላይ ሳይሆን እንዱስትሪዉን ማን ይቆጣጠረዋል የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ። ደርግ በሱ መሪነት ለማንም ችሎታ ላለዉ ኢትዮጵያዊ የእንዱስትሪዉን በር የከፈተ ሲሆን ወያኔ ግን እንዱስትሪዉ እንዳለ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እንዲገባ አድርጓል።  ደርግም ወያኔም አምባገነኖች ስለሆኑ አንዱስትሪዉን ከህዝብ ቁጥጥር ዉጭ አድርገዉታል፤ ወያኔ ግን ከአምባገነንም የጎሳ አምባገነን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር አድርጎታል።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለለፉት ሦስት አመታት ይህንን ወያኔ ገነባሁ የሚለዉን የፌዴራል ስርአትና በስርአቱ ዉስጥ የተለያዪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚጫወቱትን ሚና በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አቅርቧል። የዛሬ ሁለት አመት ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ መላከያ ሰራዊት ዉስጥ የተዘረጋዉን የወያኔ የዘረኝነት መረብ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮቴሌኮምን የዘረኝነት አደረጃጀት በመረጃ በማስደገፍ ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺንን የዘረኝነት አደረጃጀትና በዚህ አደረጃጀት ዉስጥ ማን ምን እንደሆነ ያጣናዉን የጥናት ዉጤት በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል።  ግንቦት ሰባት ሃያ አራት ሰአት ሙሉ የሚከታተሉትን የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ከበባ ጥሶ የወያኔን ዘረኝነት የሚያጋልጡ መረጃዎችን ከራሱ ከወያኔ ጓዳ እየጎተተ አዉጥቶ ለህዝብ የሚያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኝነት አያውቀዉም በሚል አስተሳሰብ አይደለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ የፈጠረዉ ከፍተኛ የመረጃ ጉድለት አለ ብሎ ያምናል፤ስለሆነም ህዝቡ የወያኔን ዘረኝነት ቢረዳም መጠኑን፤ስፋቱንና ጥልቀቱን በሚገባ ላያዉቅ ይችላል ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቀኑ ደሙን እንደ መዥገር የሚመጠዉን ወያኔን የመሰለ የጀርባ ላይ አጥንት ተሸክሞ መኖር የለበትም ብለን ስለምናምን ህዝብን ለትግል ከምናዘጋጅበትና ከምናነሳሳባቸዉ መንዶች ዉስጥ አንዱ እንደዚህ ህዝብ በገዛ አገሩ “እኩል አደረግንህ” ብለዉ በሚነግሩት ከሀዲዎች ቅኝ አገዛዝ እየተገዛ መሆኑን በማሳወቅ ነዉ።

ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዋና ዳይረክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ ፓርላማ ዉስጥ ተገኝቶ የኮርፓሬሺኑን የሁለት አመት የስራ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ኮርፓሬሺኑ የግል ባለኃብቶችን አያሳትፍም እንዳዉም እያቀጨጫቸዉ ነዉ፤ ለሙስና የተጋለጠ ነዉ፤ ደግሞም አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል ነዉና ይህ አሰራር  ሠራተኞችን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አይሆንም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዉለት ነበር። የግሉን ዘርፍ መቅጨጭ በተመለከተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉንም ቢሆን “የወያኔ ዘርፍ” እንጂ የግል ዘርፍ የሚባል ነገር የለምና ጥያቄዉ መቅረብም አልነበረበትም።  ሙስናም ቢሆን የወያኔ ስርዐት ዋናዉ መገለጫ ባህሪይ ስለሆነ ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ሙስና  “ሙስናን እናጠፋለን” ስለተባለ ብቻ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ግንቦት ሰባትን እጅግ በጣም ያሳዘነዉና ያስገረመዉ ነገር ያንን ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ የሚናገርለትን ፓርላማ ያስጨነቀዉ (ተጨንቆ ከሆነ) የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ሳይሆን አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉ ነዉ። በእርግጥ የአንድ ትልቅ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ  የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ የአሰራርና የአስተዳደር ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም የሠራዊቱ ታማኝነት  ለህዝብ ታዛዥነቱ ደግሞ ለህገ መንግሰስቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር በቀላሉ የሚወገድ ችግር ይሆን ነበር።

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአምሰት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሺን ፕላን ዉስጥ የሚጫወተዉን ቁልፍ ሚና ፓርላማዉ በሚገባ የሚገነዘበዉ ይመስለናል፤ ታዲያ ይህ በአገር እድገት ዉስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተዉ ኮርፖሬሺን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ሲወድቅ ምነዉ የብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት የሆነዉ ፓርላማ አፉን ዘግቶ ተመለከተ? ፓርላማዉን ይበልጥ የሚገድደዉ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሌሎቹ ብሔረሰቦች ተመልካች ሲሆኑ ነዉ ወይስ የአንድ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች  በአብዛኛዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሆኑ ነዉ? ለመሆኑ የወያኔ ዘረኝነት በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዉስጥ ምን ያህል ዘልቆ ገብቷል? የኦሮሞ፤ የአማራ፤ የሶማሌ፤ የሲዳማና ሌሎቹም ብሔር ብሔረሰቦች በዚህ ለአገር እድገት ቁልፍ በሆነ ኮርፖሬሺን ዉስጥ የሚጫወትቱት ሚና ምን ይመስላል?

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በአስራ አንድ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን ያስተዳድራል፤ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀቀበት ቀን ድረስ ቁጥራቸዉ በዉል ተለይቶ ባይታወቅም አስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎችም እያንዳንዳቸዉ በስራቸዉ ብዙ ፋብሪካዎችንና የማምረቻ ተቋሞችን ያቀፉ ናቸዉ። የኮርፖሬሺኑን  አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይረክተርነተና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ 29 የከፍተኛ አመራር አባላት አሉ። ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ ህወሀት ሆን ብሎ ያስቀመጣቸዉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያንዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም  ሰዉ የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ እንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በሲቪልና ወታራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎች ይገኛሉ። እነዚህን እንዱስትሪዎች በማስተዳደሩ በኩል የብሔር ብሔረሰቦችን ድርሻ ወይም ኮታ ስንመለከት  ከአስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተዳድሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በኮርፖሬሺኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ እነ ብረጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ  የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይረክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም  በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮጀክቶች አስተደዳደር ሀላፊ፤ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ልማት ዳይረክተርና  ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይረክተርን የመሳሰሉ የህወሀት ታጋይ መኮንኖች ይገኙበታል።

ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ። በ2004 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ 90 ሚሊዮን አንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ከዚህ ቁጥር ዉስጥ በትግራይ ክልል  5.4 ሚሊዮን ህዝብ በተቀሩት ስምንት ክልሎች ደጎሞ 84.6 ሚሊዮን ሀዝብ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ይህ ጥናት በዋናነት የሚያመለክተዉ በዋና ዋና የሀላፊነት ቦታ የተቀመጡትን ግለሰቦችና ግለሰቦቹ የመጡበትን ብሔር ስለሆነ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺንን የሰዉ ኃይል ምደባና የደረጃ እድገትን ጠለቅ ብለን ስንመለከት አብዛኛዎቹ እንጂኔሮችና ቴክኒሻኖች የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ፤ የደረጃ እድገትን በተመለከተም ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ሲነፃፃር በፍጥነት የደረጃ እድገት የሚያገኙት እነዚሁ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። ይህ ደግሞ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ሳይሆን ወያኔ በረሀ ዉስጥ እያለ አቅዶት ባለፉት ሃያ አመታት በስራ ላይ ያዋለዉ የረጂም ግዜ እቅድና ዝግጅት ዉጤት ነዉ።  ለምሳሌ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ ኤም አይ ቲ  ወይም የመቀሌ ቴክኖሎጂ እንስቲቲዩት ብሎ የሚጠራዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ተቀብሎ የሚያስተምረዉ የትግራይ ተወላጆችን ሲሆን ከዚህ ተቋም የሚመረቁ እንጂኔሮችና ተክኒሺያኖች ናቸዉ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን የሚሊታሪ ክንፍና በኢትዮቴሌኮም የስለላ ተቋሞች ዉስጥ ተመድበዉ ከፍተኛ የስለላ ስራ የሚሰሩት።

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝና አገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ቡችሎቹ የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ድርጅቶች በተለይ በዳያስፖራ ዉስጥ የሚገኘዉን ለእናት አገሩ ተቆርቋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጅምላ “የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች” እያሉ ለአመታት ሲዘልፉን ኖረዋል። የፖለተካ ትግላችን አላማና ግብ ከጥላቻ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለዉ ቢሆንም – ለመሆኑ ይህንን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተና አንዱን አለቃ ሌላዉን ተላላኪ፤ አንዱን የሚሾም ሌላዉን የሚሽር፤ አንዱን አብልቶ የሚያጠግብ ሌላዉን የበይ ተመልካች የሚያደርግ፤ አንዱን የአገር መሪነት ቦታ ተረካቢ ሌላዉን ኮብልስቶን ድንጋይ ጠራቢ የሚያደርግ ስርዐት የሚወድ ማን አለ? ይህንን በንጹህ ዜጎች ደም እጁ የቆሸሰና ያደፈ ዘረኛ ስርአት ዉደዱ የሚለንስ ማነዉ? በምድርም በሰማይም የከሰሩ እነ ሚሚ ስብሀቱን የመሳሰሉ የፖለቲካ ሴሰኞች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ትግላችን የትግራይ ወንድሞቻችንንና እቶቻችንን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የትግላችን ብቸኛ አላማ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ሊያጋጩን የሚሞክሩትን የህወሀት ወንጀለኞች አስወግደን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር ማድረግ ነዉ።

በደቡብ ክልል የመምህራን ተቃውሞ እየተስፋፋ ነው

መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል  የመስከረም ወር ደሞዛቸው ያለፈቃዳቸው ተቀንሶ ከተሰጣቸው በሁዋላ የጀመሩት ተቃውሞ እየተስፋፋ መሆኑን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።

የጨንጫ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች መምህራን የተቆረጠው ደሞዛችን ካልተመለሰ ስራ አንሰራም በሚል አድማ ከመቱ በሁዋላ፣ በዛሬው እለት ደግሞ በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ” የተቆረጠብን ደመወዝ የማይመለስ ከሆነ ስራ አንሰራም በሚል ” በስፍራው ለተገኙት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የወረዳው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና የወረዳው የመምህራን ማህበር ተወካይ በስፍራው ተገኝተው መምህሩን ለማወያየት የሞከሩ ሲሆን፣ መምህራኑ ግን ደሞዛችን ተመልሶ እስካልተሰጠን ድረስ ከእናንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኛ አይደለንም የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ባለስልጣናትም መምህራኑ ” አመጹን እንዲያቆሙ፣ የተቆረጠባቸው የመስከረም ወር ደሞዝ እንደሚመለስና በጥቅምት ወርም ያለ ፈቃዳችሁ እንደማይቆረጥባቸው”  ቃል ገብተው ለማረጋጋት ሞክረዋል።
ባለስልጣናቱ መምህራኑን ይቅርታ በመጠየቅ ለማረጋጋት ቢሞክሩም፣ መምህራኑ ይቅርታውንም ለመቀበል ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል ። ስለአባይ ግድብ ከእናንተ የተሻለ  በቂ መረጃ አለን በማለትም መምህራኑ በባለስልጣናቱ የቀረበውን ልመና ውድቅ አድርገዋል።
በዚሁ ወረዳ የአይዶ አንደኛ ደረጃ፣ ወሌ አንደኛ ደረጃ፣ ምእራብ አንደኛ ደረጃ፣ ገልዶ አንደኛ ደረጃ እና የሌሎችም ትምህርት ቤቶች መምህራን የተቃውሞ ፊርማ አሰባስበው ለወረዳው ትምህርት ቤት ጽህፈት ቤት አቅርበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከምእራብ አባያ መሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 15 የኢህአዴግ አባላት የሆኑ መምህራን ከድርጅት አባልነት ለመሰናበት የመልቀቂያ  ደብዳቤ አስገብተዋል። መምህራኑ ድርጅቱን ለመልቀቅ  ካቀረቡዋቸው መክንያቶች መካከል፣ “የኢኮኖሚ ችግር፣ የድርጅቱ ኢ- ዲሞክራሲያዊ ባህሪና በየጊዜው የሚፈጠርውን ጫና  ለመቋቋም አለመቻል” የሚሉ ይገኙበታል።
ቀድም ብሎ በመሰናዶ ትምህርት ቤቱ ውስጥ 75 የኢህአዴግ አባላት መምህራን የነበሩ ሲሆን፣ 47 መምህራን ድርጅቱን በመልቀቃቸው 28 አባላት ብቻ ቀርተው ነበር። ከ28ቱ መምህራን መካከል ደግሞ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ 15ቱ መምህራን የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል።

ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ

ህወሃትን ገልብጦ “ከየትኛው ክልል ድጋፍ ሊገኝ?”

sebhat nega
አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት “አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል” በማለት ነበር የመለሱት። አንዴ በመከላከያ ውስጥ የመከፋፈልና የመበታተን አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት አግባብ እንደሌለ፣ ጠያቂው እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የህወሃት ስጋት እንዳልሆነ አስመስለው አቶ ስብሃት የመለሱት የክልሎችን ስም በመጥራት ተቀባይት እንደማይኖረው ነው። ይህም አባባላቸው እኛን ገልብጦ አገር አንድ አድርጎ መምራት አይቻልም የሚል እንደምታ ያለው ቢመስልም፤ “ሪፑብሊክ” ለመመሥረት የተነሳውና እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን ህወሃት የመጨረሻ የመጥበብ ዓላማ በማስረጃ የገለጹበት ነው፡፡
ህወሃት “ኢህአዴግ” የሚባለውን ድርጅት ሲያበጀው የአገልግሎት ዘመን መድቦለት እንደሆነ ስለ ድርጅቱ የወደፊት መድረሻ ድንበሩ ከሚያወሱ የድርጅቱ የተለያዩ ማረጃዎችና ነባር አባሎቹ መጠቆሙ ይታወሳል። ህወሃት 40ና 50 ዓመት ኢትዮጵያን በብሔር ፖለቲካና በዘር እያጋጨ ለመግዛት የሳለው ስዕል እንዳሰበው ካላዘለቀው እንዴት ጠቦ እንደሚጠናቀቅ የጠቆሙት ስብሃት፣ አስተያየታቸው አካሄዱ የገባቸውን በሙሉ አበሳጭቷል።
በ1997 የምርጫ ወቅት ተፈጥሮ በነበረውና በራሱ በቅንጅት ሰዎች ሽኩቻ በተኮላሸው ህዝባዊ ድል ግለት ወቅት ኢንዲያን ኦሽን የተሰኘው ጋዜጣ “ህወሃት ወደ ትግራይ የማፈግፈግ እቅድ ይዟል” በማለት የዘገበውን ዘገባ በማስታወስ በአቶ ስብሃት መልስ ላይ አስተያየት የሰጡ፤ በቅድሚያ አቶ ስብሃትን “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም” በሚል ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ “የስብሃት ንግግር ህወሃት ታሪኩ ሲጠናቀቅ ጠቦ እንደሚቋጭ ነው። ለዚህ ሲል ነው ህዋሃት ከአንቀጽ 39 ጋር ቅበሩኝ የሚለውና የአማራ ክልል መሬትን እየዘረፈ የመውጫ ቀዳዳ ፍለጋ ሌት ከቀን መሬት እየቆረሰ አዲስ ካርታ የሚያመርተው፤ ዓለምአቀፋዊ ድንበርም ለትግራይ እንዲኖራት ያደረገው” ብለዋል።
“ህወሃት ካለውና ከተፈጠረበት  ክፉ ዓላማ አንጻር በቀጣይዋ ኢትዮጵያ ‘ቦታ አይኖረኝም’ የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ ሁልጊዜ ሲጨንቀው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስዕል ያሳያል። የስብሃትም ንግግር ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው” በማለት ምልከታቸውን የተናገሩት የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ውሳኔውና ህልሙ ስኬት የናፈቀው የቅጥረኞቹ የህወሃት ሰዎች ጭንግፍ ምኞት ቢሆንም መላው የትግራይ ህዝብ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርት ያለ አቋም በመያዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚቆም መሆኑን ማሳየት እንደሚገባው” አመልክተዋል።azeb 3
ከህወሃት ሊቀመንበርነታቸውና ከስራ አስፈጻሚነታቸው አራት ጊዜ ማመልከቻ በመጻፍ በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ያመለከቱት ስብሃት ነጋ በኤፈርት ጉዳይ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ስምምነት እንዳልነበረቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አያይዘውም ህወሃት የመከፋፈል አደጋ አጋጥሞት እንደማያወቅ፣ እንዲያውም በየጊዜው የሚነሱ የሃሳብ ልዩነቶች የድርጅቱ ልዩ ስጦታውና በረከቱ አንደሆነ ተናግረዋል። ልዩነትና በልዩነት ጥግ ድረስ ደርሶ መፋጨት የህወሃት የጥንካሬው መሰረት እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ስብሃት በድህረ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ህወሃት ለሁለት ተከፍሎ አደጋ ላይ የወደቀበትን ጊዜ አስተባብለዋል። እነ አቶ ስዬንም “የተባረሩ” ሲሉ አቅመ ቢስ አድርገው ስለዋቸዋል።
ኤርትራ ራሷን በወጉ መከላከል እንኳ የማትችል አገር እንደሆነች የጠቆሙት ስብሃት ኤርትራን ተማምኖ የሚከናወን የተቃውሞ ትግል የጤና ነው ብለው እንደማያምኑ “እብደት ነው” በማለት ኢህአዴግም ሆነ እሳቸው በእንቅስቃሴው ላይ ስጋት እንደሌለባቸው ለመግለጽ ሞክረዋል። ስብሃት በአሜሪካ ከተለያዩ ወዳጅ ሚዲያዎች ጋር እየተወደሱ ጥያቄና መልስ ያካሄዱ ሲሆን በተለይም ስለ መለስ ቅንድብ ከዘፈነው ሰለሞን ተካልኝ ሲቀርቡላቸው የነበሩት ጥያቄዎች የሚያዝናኑ ነበሩ። ጥያቄና መልሱን የተከታተሉ “ጠያቂው መልሱን አስቀድሞ ጥያቄ ማስከተሉ ጥሩ ተማሪ መሆኑንን በማረጋገጥ የምስክር ወረቀት የፈለገ አስመስሎታል” ሲሉ የለበጣ አስተያየት በማህበራዊ ገጾች ላይ አስፍረውበታል። አቶ ስብሃት በአሜሪካ ከጠባቂዎቻቸው ጋር በመሆን መደባደባቸውና በፖሊስ ይፈለጉ እንደነበርም መዘገቡ ይታወሳል። አቶ ስብሃት ከፖለቲካው ፈላጭ ቆራጭነት ወጥቻለሁ ቢሉም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንቢቶች አሁንም “የህወሃት የኋላ ዘዋሪ” እንደሆኑ አመላከች እንደሆነ ተጠቁሟል።

“በአንድ ቀን ትምህርት ፎቶ አንሺ ሆኜ ቁጭ አልኩ” የ69 ዓመቷ አረጋዊ ወ/ሮ ባዩሽ


bayush
ካዛንቺስ አካባቢ በልመና የሚተዳደሩ አንድ አይነሥውር ሽማግሌ አሉ፡፡ የሚለምኑት ከካዛንቺስ ስድስት ኪሎና ፒያሳ ለመሄድ ታክሲ ከሚጠብቁ ተሳፋሪዎች ነው፡፡ አንድ ቀን በእለቱ የለመኑትን ገንዘብ ታክሲ እየጠበቅሁ ባለሁበት ቁጠርልኝ አሉኝ፡፡ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት አርባ ብር ለምነዋል፡፡ በሌላ ቀን ተመልሼ ጠየቅኋቸው። በልመና ከሚያገኙት ገንዘብ ልጃቸውን ኮሌጅ አስተምረዋል፡፡ ልጃቸው ሥራ ከያዘ ከዓመታት በኋላም ግን ልመና አላቆሙም፡፡ አሁንም እዚያው ካዛንቺስ እየለመኑ ነው፡፡
“ለምን ልመና አያቆሙም?” አልኳቸው፡፡
“ምን ላድርግ ቁጭ ልበል እንዴ?” በማለት እኔኑ መልሰው ጠየቁኝ፡፡ እዚያው ካዛንቺስ የሚለምኑ ሌላ አረጋዊ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለባቸው፡፡ በምፅዋት የሚያገኙትን ሳንቲም ይዳብሱና አምስት ሳንቲም ከሆነ መልሰው ይወረውሩታል፡፡
በአንፃሩ የእይታም የአቅምም ችግር ያለባቸው የማይመስሉ አንዲት አሮጊት፤ ኡራኤል ቤተክርስትያን አካባቢ ከጥቂት ወራት በፊት አገኘሁ፡፡ የእሳቸው የአለማመን ዘይቤ ከተለመደው የተለየ ነው፡፡
“ቤቴ ልደታ ነው፤ መሳፈርያ አልያዝኩም” አሉኝ፡፡
“ኑ፤ እኔ እከፍልሎታለሁ፤ በዚያ አቅጣጫ ነው የምሄድው” አልኳቸው፡፡
“ባትሰጥ አትተወውም” ብለው እየተቆጡ ትተውኝ ሄዱ፡፡
ከቀኑ 11 ሰዓት ግድም ብሔራዊ ትያትር አካባቢ ሲለምኑ ያገኘኋቸው መስራት የሚችሉ ሴት ለልመናው ምክንያት የሰጡት “ልጄ ታሞብኝ ማሳከሚያ አጣሁ” የሚል ነው፡፡ እኒህኑ ሴት ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ኡራኤል ቤተክርስትያን አካባቢ ሲለምኑ አገኘኋቸው፡፡
አሁን ደግሞ “ገንዘቤን ዘረፉኝ” ሲሉ ሰማኋቸው፡፡
በየቦታው መሥራት እየቻሉ ልመና የወጡ አረጋውያን አያሌ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ አመል ሆኖባቸው ነው እንጂ ሠርተው በገቢ ራሳቸውን መደጐም ይችላሉ፡፡ ለዚህም ይመስላል “ኸልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናል”፣ የኢትዮጵያ አረጋውያን ማህበር እና ሌሎች አጋሮቻቸው ባለፈው ሳምንት አረጋውያን ሰርተው መጠቀም የሚችሉ መሆኑን የሚያሳይ የአራት ቀናት አውደርእይ ቦሌ አካባቢ በትሮፒካል ጋርደን ያዘጋጁት፡፡ ሰርተው ራሳቸውን በመደጐማቸው ደስተኞች መሆናቸውን ያነጋገርኳቸው አረጋውያን ይገልፃሉ፡፡
በ1993 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አረጋውያን ማህበር፤ 38 አባል ማህበራት ያሉት ሲሆን “ጤነኛ አረጋውያን ሰርተው መኖር ይችላሉ” በሚል መርህ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ማህበሩ፤ በአረጋውያን ሊተገበሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን የሚቀርፅ ሲሆን አረጋውያንን በስልጠናና በልምድ ልውውጥ ያግዛል፡፡
የልምድ ልውውጡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ይከናወናል፡፡ ባለፈው ዓመት ለምሳሌ በእንግሊዝ የፖትስማውዝ ከተማ አረጋውያን ማህበር የአዲስ አበባ አቻውን ለልምድ ልውውጥ ጠርቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ለማህበሩ ፕሮጀክት ኦፊሰር ብቻ ሲፈቀድ የአረጋውያን ማህበር ፕሬዚደንቱ፤ “የከተማ ቦታ የለዎትም፤ ጡረታዎም ሃያ ፓውንድ አይሞላም፤ ሄደው ሊቀሩ ይችላሉ” በሚል የእንግሊዝ ኤምባሲ ቪዛ መከልከሉ ቅሬታ አሳድሯል፡፡ እናም የፖትስማውዙ ማህበር ለእንግሊዝ ፓርላማ ክስ አቅርቧል፤ ምላሹ ባይታወቅም፡፡ ቪዛ የተሰጠው ፕሮጀክት ኦፊሰር ግን እንግሊዝ ቀርቷል፡፡
የአረጋውያን ማህበር አባላት፤ ህብረተሰቡ ለአረጋውያን ያለው አመለካከት የተዛባ መሆኑ ችግራቸውን የከፋ እንዳደረገባቸው ይናገራሉ፡፡ ይሄን አመለካከት ለማስወገድም ትግል ላይ ናቸው፡፡ የህብረተሰቡ የተዛባ አመለካከት እንዲወገድ እየሰራን ነው የምትለው የ”ኼልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናል” የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኤርና ምንተስኖት ሃንዝ፤ በአረጋውያን ላይ የሚደርስባቸው መብት ረገጣ እንዲቆም ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑንና ቅሬታቸውን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚያቀርቡ ተናግራለች፤ ሕግ እንዲበጅለት፡፡በሰሞኑ አውደርእይ ብዙ መንቀሳቀስ የማይችሉ አረጋውያን አትክልት ውሃ ሲያጠጡ፣ ለራሳቸው ምግብ ለማሰናዳት ሽንኩርትና ድንች ሲልጡ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ቀርበዋል፡፡ ሥራዎቻቸው ከቀረቡላቸው ማህበራት አንዱ “እንረዳዳ” የአረጋውያን ማህበር ሲሆን አረጋውያን የተረጅነት ስሜት እንዳይሰማቸው እያደረግሁ ነው የሚለው ማህበሩ፤ የተወሰነ ሥራ እንደየአቅማቸው እየሰሩ መሆኑን ገልጿል፡፡ የማህበሩ አባላት የሰሯቸው የሽመና ውጤቶችም በአውደርእዩ ላይ ቀርበዋል። አረጋውያኑ እንደየስራቸው መጠንም ገንዘብ ያገኛሉ፡፡ ጋቢ የሰራ የጋቢ ዋጋ፣ ፎጣ የሰራ የፎጣ ዋጋ ያገኛል፡፡ አባላቱ ዱቄት፣ ዘይት፣ ሳሙናና የመሳሰሉትም ይሰጣቸዋል፡፡ ተቀጥረው የመስራት አቅም ያላቸው ደግሞ በወጥ ቤትነት፣ በጥበቃ፣ በአትክልተኝነትና በፅዳት ሥራዎች እንደሚቀጠሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡የአረጋውያኑ ምርቶች ወደ ገበያው ገብተው የሚሸጡበት ሁኔታ የጠየቅኋት የአውደርዕዩ አስጐበኚ፤ “በባዛር እና በዕቁብ ይሸጣል፡፡ ለምሳሌ ብርጭቆ ፋብሪካ በወር ስምንት ጋቢ ይገዛል” ብላለች፡፡
የ75 ዓመቱ አረጋዊ አቶ መኩርያ፤ የጉለሌ አካባቢ ነዋሪ ሲሆኑ በፊት ገበሬ ነበሩ፡፡ አሁን ግን ሸማኔ ሆነዋል፡፡ በቀን ሦስት ክንድ እና ከዚያ በላይ እየሸመኑ በሳምንት አንድ ጋቢ እንደሚያደርሱ የተናገሩት አረጋዊው፤ “እኔ ተሯሩጬ መሸጥ ስለማልችል ማህበሬ ነው የሚሸጥልኝ” ብለዋል፡፡
ሌላው የ70 ዓመት አረጋዊ አቶ ኃይሌ ሀብተማርያም፤ ከበቾ አካባቢ ያርሱ ነበር፡፡ አቅም እያነሳቸው ሲሄዱ እየተረዱም ቢሆን አምራች አረጋዊ በመሆን አንዳንድ ወጪዎቻቸውን ራሳቸው እንደሚችሉ ገልፀውልኛል፡፡
“ውድ የአረጋውያን በጐ አድራጐት ድርጅት” በየወሩ ለእያንዳንዱ አረጋዊ 100 ብር የሚሰጥ ሲሆን አረጋውያኑ አትክልትና ፍራፍሬ በመነገድ ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ፡፡
የ69 ዓመቷ ወይዘሮ ባዩሽ ወልደአረጋይ፤ እድሜያቸው ሳያግዳቸው ፎቶ አንሺ ሆነዋል፡፡
“ፎቶ ማንሳት መቼ ጀመሩ?” ብዬ ጠየቅኋቸው፤ ወይዘሮ ባዩሽን፡፡ “እዚህ አረጋውያን ድርጅት ውስጥ እየሰራሁ “ኼልፕኤጅ ኢንተርናሽናል” ለልምድ ልውውጥ የውጭ ሰዎች አመጣ፡፡ በማግስቱ ካሜራ ሰጡን፤ ለማስተማር፡፡ እዚያው አስተማሩን። ሦስት አረጋውያን ነን በእለቱ ስልጠና የተሰጠን። አሰልጣኛችን እንዴት እንደምናነሳ አሳይቶን “ነገ ታሳዩኛላችሁ” ብሎ ሄደ፡፡ ራሳችን ያሳነውን የታጠበ ፎቶም ለኛ አሳይቶን ካሜራው ለእያንዳንዳችን ቀረ። ይኸውልህ ልጄ፤ በአንድ ቀን ትምህርት ፎቶ አንሺ ሆኜ ቁጭ አልኩ፡፡ ከዚያን ወዲህ ሠርግ ላይ ‘እቴቴ እስቲ ፎቶ አንሺን’ ተብያለሁ”
“እና ለወደፊት ምን አሰቡ ታዲያ?”
“ጥሩ ነው፤ ደግሞም ፎቶ እያነሳሁ ገንዘብ ማግኘቱም ይጠቅማል፡፡ እግዚአብሔር ካለ በዚህ ካሜራዬ ተአምር እሰራበታለሁ፡፡ ትልቅ ሥራ እሰራበታለሁ፤ ራሴንም እደጉምበታለሁ” ብለዋል፤ ወ/ሮ ባዩሽ፡፡
ከ86 ሚ. የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ አምስት ሚሊዮን ያህሉ አረጋውያን እንደሆኑ የ”ኼልፕ ኤጅ” መረጃ ይጠቁማል፡፡ (መልካሙ ተክሌ: አዲስ አድማስ)

Friday, October 25, 2013

ጫልቱ እንደ ሄለን ከቡርቃ ዝምታ የቀጠለው መርዛማ ብዕር

October 24, 2013

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ተራሮች አንቀጠቀጥኩ ያለው ትውልድ አካል ነኝ ባዩ ወንድማችን በቡርቃ ዝምታው በማር የተለወሰ መርዝ አሰናድቶ አማራና ኦሮሞ ሲተራረድ ዙርያ ከበው በለው! አትማረው! የሚሉትን የአባቱን ሀገር ፖለቲከኞች አስቦ የጻፈው ክታብ መሆኑ ተነግሮ አብቅቶለታል። ተስፋዬ የጦር ሜዳ ዘጋቢነቱን በኢትዮጵያውያን ተምሮ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለው ለሚወጉን ማገልገሉና በደል መፈጸሙ እውነት ነው። ለዚህ ውለታውም የዘመናት ታሪክ ያለውን ድርጅት ያለምንም ክህሎት በአዛዥነት ይዞ እንዳሻው እንዲፈነጭበት ተሰጥቶት ነበር። ቁንጮ ሆኖም የሚበቃውን መረጃ ከክምችቱ እንዲያገኝ ሆኖ መሰየሙንና ክምችቱንም ለፕሮፓጋንዳ መሳርያነት እንዲጠቀምበት ሙሉ መብት ተሰጥቶት እንደነበረም እናውቃለን። ተስፋዬ አገር የለቀቀበትን ጊዜ መለስ ብለን ብንመለከት ለሻዕብያ ያለው ቅርበት ከወያኔ ጋር ለመቀያየም ምክንያቱ መሆኑን መገመት ይቻላል። በተስፋዬ ስራዎች ውስጥ የኤርትራ ጉዳይ ልዩ ቦታ እንዳለውና ከጻፈም ጀግና ብልህና አስተዋይ እንደሚያደርጋቸው የታወቀ ነው።Tesfaye Gebreab's New Book: “Yesidetegnaw Mastawesha
ስለዚህ ኤርትራዊነት አያደላበትም ወይም ለኤርትራ መረጃ አያቀብልም ብሎ ያለመገመት ከመነሻው የሚገርም ጉዳይ ነው። በቅርብ ድርሰቶቹ ወያኔዎቹን በተመለከተ የአሉባልታ ዶፍ ማውረዱና ይልቁንም ዱላው የጠነከረው ለሻዕብያ ወገንተኛ አይደሉም ባላቸው ላይ መሆኑም የሚያመለክተው ይህንኑ ነው። በማሩ ቃላት አሉባልታዎች ከመገለጻቸው በቀር የፖለቲካ ፋይዳ ያላቸው የማይታወቁ ድብቅ ምስጢሮች የሚባሉ ነገሮችም የሉበትም። ስለዚህ ተሥፋዬ የት እንደሰፈረ የሚሸሽግ አንዳች ነገር ከሌለ ፈቅደን የታለልንለት ድንገት መባነናችንና ምስጢሩ እንደተገኘ ያለማሳወቃችን ለምን በዚህ ጊዜ ሆነ ብለው ለሚጠይቁ ጠርጣሪዎችም የውይይት ማንደርደርያ ቢሆን አይገርምም። የአብርሃ ደስታን ምልከታ እጋራዋለሁ። የተሰጡ አስተያየቶችን አንብቤያለሁ። ጥሩ የሚባል ነገር ሲጻፍ ማመስገን ስህተት ሲኖርም ስህተት እንደመጠቆም የዘር ሀረግ ላይ ተንጠልጥሎ መራገም ውይይታችንን ጤናማ ያደርገዋል የሚል እምነት የለኝም። የቀረበበት ማስረጃ ግን አንዳንድ የዋሆች ለኦሮሞ ካለው ፍቅርና አክብሮት አንጻር የተንገበገበ ሳይሆን የእልቂት ድግሳችንን እያጧጧፈ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ያደርጋል ብዬ አምናለሁ።
ተስፋዬ የቢሾፍቱ ልጅ ነው ሥጋና ደሙን የቢሾፍቱ አፈርና ወሀ ገንብተውለታል፣ አንደበቱን የገራለት ሀሳቡን በዚህ መልክ ይገልጥበት ዘንድም የቋንቋ ቁልፉን ያስጨበጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ይሁን እንጂ ወንድማችን ተሥፋዬም የማንነት መምታታት የማያውቀውን አገር የመናፈቅ ግራ መጋባት ውስጥ አይደለም ብዬ አልገምትም። ከጠባው ጡት ጋር ሲነገረው የኖረ የጥላቻ መርዝ መኖሩንም በጻፈው ማስታወሻ ላይ  ግልጽ ብሎ ተቀምጧል። አብሮ አደጎቹን ወይም በስደት ዘመን ያገኛቸውን ሁሉ ለዚህ የፖለቲካ ጥቅም በቢሾፍቱ አድባር ስም እየማለ ሊጠቀምባቸው ቢሞክር አይደንቅም። እንዲያውም ለአባት አገሬ አደረኩ የሚለውን እያሰበ በበግነታቸው ድዳቸውን ማስገልፈጡንና የበግ ነጋዴነቱ ውስጡን ያስቁት ያኩራሩትም ይሆናል። “በግ እሰራ” ነበር ማለቱ ድንገት የተጻፈች አረፍተ ነገር ናት ብሎ ማሰብ እንዲከብደን ሆኗልና። እንዲያም ሆኖ ወንድማችን ያለኢትዮጵያዊነት ነብሱ ባዶ መሆንዋን አልጠራጠርም። ከኢትዮጵያ ሌላ ባማረ አማርኛ ለማንስ ሊጽፍ ይቻለዋል?  በሁለት ባላ ላይ ለተንጠለጠለቺው ነብሱ በጣም አዝናለሁ። የአባቱን ሀገር ለማገልገል ቆርጦ የተነሳ ቢሆንም እንደ ተበላ ሰላይ ሜዳ መውደቂያውን ማፍጠኑ ግን ብልህነት እንደሚያንሰው ያሳያል።
ለዚህም ይሆናል የስደተኛው ማስታወሻ በወቅቱ ከሕዝቡ ጆሮ ካልገባ የሚያመጣው የፖለቲካ ትርፍ ስለሚቀንስ በነጻ እንድናነበው የሆነው። እኔም ገረፍ ገረፍ አደረኩት ማለትም ለመተቸት በሚያስችል መጠን አልተመለከትኩትም። ብቻ ዘመን አቆጣጠሩን ‘በግዕዝ’ የሚል ሲቀጥልበት እንደ ኢትዮጵያ ማለት ከብዶት ይሆን? ብዬ ማሰቤ አልቀረም። በጠቅላላው ዘረፍ ዘረፍ የሚያደርጋቸው ቃላትና ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽባቸው አረፍተ ነገሮች በውል ሊታዩ የሚገባ ነው። ሳይንሱን ባለመረዳቱ ስለፍጥረት የሚሰጠው ምሳሌም የሚተች ነው። ጦስኝ ሳር አይደለም የበግ ሽንትም ሳር ማስተኛቱን እጠራጠራለሁ። ምናልባት የቢሾፍቱ በጎች ከሆራው እየጠጡ እንደ እሳት አደጋ ጎርፍ ይሸኑ አንደሆን አላውቅም።
ሌላው ምሳሌ አንበጣ ብሎ የጻፈው ስለ ምስጥ ነው። አንበጣማ ከፊቱ ያለውን እየጠረገ ጥቁር ደመና መስሎ  ብዙ ኪሎሜትሮችን ያካልላል። ምስጥ ክንፍ የሚያወጣው ሩቅ ለመብረር አቅዶ አይደለም እንደ ተስፋዬ ግምትም ክንፋቸው ሲረግፍ ባጭር መቅረታቸው አይደለም። የምስጥ ንግስትና ንጉስን ለመፍጠር ከተለያየ መኖርያ ቤታቸው (ኔስት) በተመሳሳይ ጊዜ ወጥተው ወንድና ሴት የሚፈላለጉበት ተፈጥሮ የምትደግሰው ድንቅ ሰርግ ነው። ጋብቻ ካንድ ቤተሰብ እንዳይሆን የዚህኛው ቤት ልጃገረድ ምስጥ ከዚያኛው ቤት ኮበሌ ጋር ዝናብ ሲያባራና አመሻሹ ላይ እየበረሩ ትንሽ ይዳራሉ። ወንድየው ሴቲቱን ተጠግቶ “ሁኚኝ” ይላታል ከፈቀደች ትሆነዋለች። ያኔ ፍቅር መስራት ይጀምራሉ፣ ክንፋቸውን አራግፈውም ጎጆ ለመቀለስ የክረምቱ ዝናብ ያለሰለሰውን አፈር ማስ ማስ አድርገው ሃኒሙን ይጀምራሉ። የነርሱን ጋብቻ ደግሞ የእረኞች የቡሄ ጅራፍ ያደምቀዋል። ተስፋዬ ይህን አውቆ ቢሆን ባማሩ ቃላት ወሲብ ወሲብ እያሰሸተተው ይህንን ጋብቻ ለመፈጸም ከየጉድጓዱ እየወጡ ከወፎች አደን ተርፈው አዲስ ጎጆ የሚቀልሱትን የህይወት ታሪክ በጻፈው ነበር። ንግስቲቱ በቀን ከሺህ በላይ እንቁላል እየጣለች በሰራተኛና በወታደር የታጀበ መንግስት እንደምታቋቁምና ኩይሳ የምንለውን ከኢንጅነሮች ሙያ የላቀውን ቤተመንግስትም እንደምታስገነባና ሌላም ሌላም በነገረን ነበር። ያወቅን የሚመስለን ብዙ የማናውቀው የተፈጥሮ ምስጢር ቢገለጽልን ኖሮ እርስበርስ ለመጠፋፋት ጦር ባላመዘዝን ነበር። ሆኖ ያለፈን ነገር ወይም እየሆነ ያለን ስህተት በቅንነት ተነጋግረን አብሮነታችንን ማስዋብ የሚቸግረን አይደለንምና ወዳጅ መስለው መርዝ የሚረጩትን ማጋለጥ ተገቢ ነው።
ስለ አንድ የሶማሌ ህጻን እሱን አይቶ ማልቀስ ሲጽፍ ይህ የሶማልያ ህፃን እኔን ሲመለከት ለምን እንዳለቀሰ ማሰላሰል ያዝኩ… “አበሻ እባብ” እንደሚለው ነባር የሶማሌ ብሂል እባብ መስዬ ታይቻቸው ይሆን…. የሚል መንደርደርያ ከጻፈ በሁዋላ ወረድ ብሎ ደግሞ በብዙ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ የኤርትራና የሶማሌ ጠላት እንደሆኑ ይነገራል ይለናል ይህንን ቅጥፈት ካስነበበ በሁዋላ ደግሞ እባብ ስለመግደሉ ሲነግረን እግዚአብሄር.. የእባብን አናት ቀጥቅጠህ ትገድለዋለህ ሲል ያዘዘውን እኔ በተደጋጋሚ ፈጽሜዋለሁ የፈጣሪን ቃል በማክበር ረገድ በተሟሉ ሁኔታዎች ተሳኩልኝ ብዬ ከምኮራባቸው ትዕዛዛት ዋናው “የእባብን ጭንቅላት ቀጥቅጡ” የተባለው ሳይሆን አይቀርም በሚል ይደመድመዋል። እነዚህ በተን ተደርገው የተረጩት በመጀመርያ አበሻና እባብ ከዚያ አበሻ የሶማሌና የ ኤርትራ ጠላት በመጨረሻም አግዜር እባብን ቀጥቅጡ ባለው መሰረት እባብ መቀጥቀጥ ተሳክቶልኛል የሚሉ እንደ እባብ ቃላት ውስጥ እየተሹለከለኩ የሚሄዱ መርዘኛ መልዕክቶቹን አስፍሮበታል። መጽሃፉን ለመተቸት ሳይሆን አንዲት በየምዕራፎች ተብትና የተቀመጠችውን ስራውን በተመለከተ ብቻ ጥቂት ለማለት ነው። ሌሎቹ ዋናው ተልዕኮአቸው ማዳመቅ ይመስለኛል።
ዛሬ ሰለ ጫልቱ ሄለን መሆን በተጻፈው ላይ ትንሽ እላለሁ። ጫልቱ በለጠች ማለት ነው ጫላም በለጠ። ለኢትዮጵያዊ ጫልቱ ወይም በለጠች ከሄለን የበለጠ ትርጉምና ቅርበት ያለው ስም ነው። በጣም ደስ ያለኝ አቤ ቶኪቻው ተመሳሳይ ነገር ማንሳቱና የአዱገነት ልጆች ይህንን ጉዳይ የሚመለከቱት ለየት ባለ መነጽር መሆኑን ማሳየት መቻሉ ነው።
የቢሾፍቱው ልጅ ተስፋዬ በልጅነቱ አዲስአበባን ሁለቴ ብቻ ስላያት ያልተረዳው ነገር መኖሩን መግለጽና እግረመንገዱንም ያዘኑብን ይቅር እንዲሉን በሸገር ልጆች ስም ያለውክልና ለመጻፍ በመሻቴ ነው።  አዲስ አበባ ውስጥ የትኛውም አካባቢ የኖረ ሰው ሶስት አመት ሙሉ ኦሮምኛ ሲነገር አልሰማሁም ቢል በጣም ያስቃል። አዲስ አበባንም ያለማወቅ ይመስላል። እንኳን ኦሮምኛ ችሎ ለመጣ አዲስ አበባም ኖሮ ኦሮምኛ ማቀላጠፍ ይቻላል። ብዙዎቻችን ለዚህ ምሳሌ ልንሆን እንችላለን የኦሮሞ ልጆች መሆናችን አስፈርቶንም አሳፍሮንም አያውቅም። ተረብና ቀልድ ደግሞ ለሁሉም ዘር የሚሰጥ በመሆኑ በተለየ መልኩ ኦሮሞን ብቻ አንገት የሚያስደፋ አይደለም። ስለ ሌላ አገር የተጻፈ እስኪመስለን ድረስ የተቀባባ ነገር ነው። እንኳን ሀዘን ኖሮ በኦሮምኛ ማልቀስ ይቅርና የመስቀልን በዐል ውብ የሚያደርገውስ የማን ዘፈን ነበርና? ኦሮምኛ ሳይሞከርስ ከገጠር የመጣ ሸቀጥ እንዴት ይገዛ ነበር? በራሱ ዝቅተኛ ስሜት ውስጥ የገባና ራሱን መደበቅ የሚፈልግ ካልሆነ በቀር ኦሮምኛ መናገር የተከለከለባት ከተማ እስክትመስል ድረስ አዲስ አበባን ማጠልሸት በጣም አሳዛኝ ነገር ነው ውሸትም ነው። አማርኛ የስራ ቋንቋ በመሆኑ ብዙዎች ቋንቋውን እስኪማሩ ይቸገራሉ ይህ እውነት ነው። ሁዋላ ቀርነት በመኖሩ ቋንቋ ያለመቻልን መቀለጃ የሚያደርጉ ነበሩ ይህ ደግሞ ሁሉንም ይመለከታል። ኦሮምኛውን ስናወላግደው ዘመዶቻችን ይስቁብን ነበር። አንዳንዴም የአማርኛውን ቃል እንደ ኦሮምኛ ስናደርገው “ይሄ ደግሞ የሚበላ ነው የሚጠጣ” እያሉ የሚስቁብንን ጭምር አስታውሳለሁ።
አቴቴ የተከለከለ ነገር ሆኖ ሳይሆን ክርስትናን ከመቀበል ጋር የቀረ ነገር ነው። የግንቦት ልደታ አድባርም እንደዚሁ። ይህ ‘ዘመናዊነት’ በሚል ፈሊጥ የራስን የማጣጣል አባዜ እንጂ ሲስተሚክ ቫዮለንስም አይደለም። የተደራጁ ሃይማኖቶች የብዙዎችን አምልኮ አረመኔ የሚል ቅጥል እየለጠፉለት መስፋፋትን አድርገዋል። ይህ በመላው ዐለም የሆነ ነው። ይህ ማለት ምንም ጎጂ ነገር ማለትም ማንጓጠጥና መተረብ አልነበረም ለማለት አይደለም። የነበረ ነገር ነው በጣምም ስህተት ነው። ቋንቋችን ሀብታችን ነው ታሪካችን ነው ልንጠቀምበት ይገባል። አንድ ሁላችንንም ሊያገናኘን የሚችል ቋንቋ መኖሩ ደግሞ እንደ ሀገር አብረን እንድንኖርበት ያመቻቻል። አንዱ አንደኛው ላይ ሲሰለጥንበትና ሲጎዳው ይሁን ማለት ተገቢ አይደለም።
በጫልቱ ላይ የደረሰው ነገር ከልብ የሚያሳዝን ነው የዚህ አይነት ስነልቦና እንዲኖራቸው ለተገደዱት ሁሉ ልናዝን ተገቢ ነው። ሆኖ ያለፈን ነገር ፈጽሞ እንዳልነበር መካድም አይቻልም። ቢሆንም ይህ ድርጊት አንድን ዘር ለማዋረድ ሆን ብሎ የተነጣጠረ ክፋት እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው። አንዳንድ ጊዜም ለመብት መቆም ያለመቻልና ካለው ሁኔታ ጋር ተስማምቶ ለመኖር የሚደረግ ስህተትም ነው። ልክ እንደ ጫልቱ  ማንጠግቦሽ፣ ኩሪባቸውና አቻምየለሽ ከስማቸው ጋር በተያያዘ ብዙ ይተረቡ ነበር። አዝብጤና እርገጤን ሙደስርና ሙሽሪንም የማራቸው አልነበረም ከተሜ ያልሆነው ሁሉ ቅጽል ስም አያጣም ነበር። ከሸገር ልጆች ተረብ ያመለጡ ነብሶች ካሉ የታደሉ ናቸው። ከጎጃምም ይምጣ ከደሴ አዲስ ላይ ቅጽል ስም አይታጣለትም። ትክክል ነው ማለት አይደለም ግን ፈጽሞ በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ልዩ ጥቃት አይደለም። የሰውን ስሜት በዚህ ደረጃ ሊጎዳ የሚችል ቅጽል ስምም ሆነ ተረብ ጎጂ ከሆነ መስቀሉን መሸከም ያለባቸው አማርኛ የሚናገሩ የአዲስ አበባው ድብልቅ ኢትዮጵያውያን እንጂ አንድ ዘር የጥቃት ዒላማ ሊሆን አይገባም። አማርኛ ስለተናገሩ ብቻ አማራውን ሀጢአት ማሸከም ተገቢም ትክክልም አይደለም። ስህተትን በጥፋት ማረምም አይቻልም።
የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና አማራን ማጥፋት ኢትዮጵያን የማፍረሻ ቁልፍ ነው ያሉትን የፋሺስት ጣልያኖች መርህ ለሚያስፈጽሙ ደግሞ፣ እንኳን የሰደበ የገደለም ይቅር የሚባባልበትን ባህል ያዳበረ ሕዝብ እንዳለን ልናስታውሳቸው ይገባል። የፋሺስቶቹን መርህ አራማጆቹንም ወገን ብለን አቅፈን ይዘን ብዙ ተጉዘናል። ለኛ ሞት ለመደገስ አይኑን የማያሸውን ተስፋዬንም እንደዚሁ። ያኔ ተቀለደባቸው ተሰደቡ ነው አሁን በኦሮሞ ልጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ምን ስያሜ ይሰጠዋል? ዘረኞች የራሳቸውን ጎሳ ብቻ ሽቅብ ሰቅለው በሌሎች ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን በደል የተመለከትነው አሁን ነው። ምናልባት ተስፋዬ ወደ ወለጋ አላቀና ይሆናል እንጂ እዚያ ደግሞ ጉራጌና አማራው ላይ ብዙ የሚያስቁ ቅጽል ስሞች ይሰጥ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከዚያም ያለፉ ነገሮች ሆነዋል ግን ተማርን የሚሉ ጥቂት ሰዎች ያደረጉትን  የኦሮሞ ሕዝብ በሌላው ላይ እንዳለው ጥላቻ አድርጎ መውሰድ አላዋቂነት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሸበትን አሳድሮ የራበውን አብልቶ የሚሸኝ ደግ ሕዝብ ነውና የጥቂቶቹን ክፋት ለሕዝቡ ማሸከም አይቻልም።
አዲስ አበባ ያለው አማርኛ ከዚህም ከዚያም ቃላት ተውሶ ኢተዮጵያንኛ ሆኖአል። እኔ ባደኩበት አካባቢ ስድስትም እንሁን ደርዘን ሁላችንም አንድ ዘር ሆነን አናውቅም። ድብልቅልቅ ነን። እናትና አባትም ከተለያየ ብሄረሰብ የተውጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ለኛ ምንም ዋጋ አልነበረውም። ዘር ለመጥላት የሚያነሳሳ ምክንያትም እውቀትም አልነበረንም። ጥርት ያልኩ አማራ የሚለውም የአዲስ አበባ አማርኛ ሲቸግረው እናያለን።  ትልቁ ጥያቄ ይህ ሰዎችን እንደሚያሳዝን በመረዳት አሁን እንዳይደገም ማድረግና ከአንደበታችን የሚወጣውን መመዘን መቻልን ተምረናል ወይስ እዚያው ነን? የሚለው ነው። ባህላችን ሊያድግ ይገባዋል። መፍትሄው ወዲያና ወዲህ መሰነጣጠቃችን አይደለም መጥፎ ወይም ጎጂ የምንለውን ልማድ ማረም ማስተካከልና ከህግም አንፃር ተጎጂዎችን መታደግ የሚቻልበትን መንገድ በጋራ መፈለግ ይመስለኛል። ተስፋዬም ወደ መዝጊያው ላይ ወደዚያው የሚያንደረድር አረፍተነገር ማከሉ ከቡርቃ ዝምታ ጭፍን ጥላቻ ለመውጣት መሞከሩ ይመስለኛል። በዚህኛው ቅጹ ላይ ከአማራ ጥላቻ ወደ ሲስተሚክ ቫዮለንስ ዝቅ ብሎልናል ይህም የኦሮሞ ነጻ አውጪዎች የመገንጠል ጥያቄን ተወት ከማድረጋቸው ጋር ሊቀራረብበት የፈለገበት የብልጥ መንገድ ይመስለኛል። ተስፋዬ ስለ ኢትዮጵያ ግድ የሚለው ቢሆን ኖሮ ሌሎችንም በማማከር የአዲስ አበባው ባህል ምን ይመስል ነበር? ብሎ ትንሽ ምርምር ሊያደርግ በተገባው ነበር። አዲስ አበባ ተወልዶ ላደገ ኦሮምኛ በከተማው ብርቅ ነበር ቢለን ምናልባት መስማት የተሳነው ሰው ወይም በኦሮሞው ስም የፖለቲካ ትርፍ ፈላጊ መሆን አለበት እንላለን።
አዲስ አበባችን ከየትም መጣ ከየት ሰው ጦሙን የማያድርባት ከተማ ነበረች። የኢትዮጵያ ብሄር በሄረሰብ ጭማቂና ራሱን ዘመናዊ አድርጎ የሚጠራ ድብልቅልቁ የወጣ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ ናት። በስልጣኔና ዘመናዊነት ስም ዝርጠጣ፣ ተረብ፣ ስድብና ድብድብም እንደዚያው ጎላ ብሎ የሚታይባት ከተማ ነበረች። ንቅሳታሟን ኒቂሴ ብሎ የሚጠሩት ኦሮሞ ስለሆነች አይደለም መተረብ ስላለባቸው ነው። በዚህ አጠራር የኦሮሞ እናትና አባት ያላቸው ቋንቋውንም አሳምረው የሚናገሩ ልጆች ዘመዶቻቸውን ይተርባሉ። ከወሎም ትምጣ ከጎጃም ‘ኒቂሴ’ የሚለው ስም ሊለጠፍላት ይችላል። ትክክል ነው ማለት አይደለም። ፈጽም ‘ቡሊ’ ማድረግን አጥብቄ የምቃወም ነበርኩ። በልጅነት እድሜዬ በዚህ ምክንያት ቅር የሚሰኙ መኖራቸውን አሳምሬ አውቃለሁ። አንዳንዶችም ከተረብ ለመዳን የመጡበትን ጎሳ ይደብቁ እንደነበር አውቃለሁ። በመጡበት ጎሳ ምክንያት ትምህርት መማር ያልቻሉ ወይም የስራ እድል የተነፈጋቸው ካሉ በኔ እድሜ የማውቀው ባለመኖሩ መመስከር አይቻለኝም። በኦሮምኛ  ቅላጼ ብቻ የሚሳቅ የሚመስላቸው ሰዎች በጣም ተሳስተዋል። ኦሮሞው ግዕዝን ራብዕ ሲያደርጋት ወሎዬውም ‘ደ’ን ሲያጠብቃት ተረብ አለ። በወሎ ቅላጼ የአዲስ አበባ ልጆች በጣም ያፌዙ ነበር፣ በጎጃሙም በጎንደሩም እንደዚሁ። በትግሪኛውም ባልተለየ መልኩ ይቀለድ ነበር። ጉራጌስ ቢሆን ምኑ ተርፎ። ግን ይህ ሁሉየከተሜው ጉራ እንጂ  የዘር ጥላቻ አልነበረም። ይህን ሁሉ ጠልቶስ ማን መሆን ይቻላል? አሁንም ብዙ የአደባባይ ቀልዶች የዚህ አይነት አኪያሄድ አላቸው በሰላም ጊዜ ሊያስቅ ቢችልም በቀውጢ ሰዐት ግን መታረጃም ሊሆን እንደሚችል ሰዎች ልብ ሊሉት ይገባል። ከዚህ አይነት ቀልድ መታቀብም አለባቸው።
አዲስ አበባ ዘር የለም ‘ወልመካ’ ነው ድብልቅልቁ የወጣ። ለዚህም ነው ብዙ የአዲስ ልጆች ዘርህ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት የማይችሉት።  አዲሰ አበባ ጥቁር መሆን ያስተርባል፣ ቀይ መሆን ያው ነው። ትልቅ አይን ያለው ጉጉት ትንሽ ዐይን ያለው ጭልፊት ሊባል ይችላል። ቀጭኑ ሲምቢሮ ወይም ወፍ ሲባል ወፍራሙ ወደል ወይም ‘ቦዬ’። ረዥሙም ቀውላላ ነው አጭሩም ኩሩሩ። አፍንጫ ሲተልቅም ስም አለው ልጥፍ ሲሆንም እንደዚያው። እንደጊዜው መለዋወጥ ስም የመለዋወጡ ነገርም ያለ ነው። ይህ የሁላችንንም ስነልቦና የሚነካ ነው። አሁን ኦሮሞም አማራም ወደ መጽሀፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁርዐን በመዝለቅ የአይሁድና የአረብ ስም መስጠቱን በሰፊው መያዙም የዚሁ ምሳሌ ነው። ኢዮብ የሚባል ደግና ትዕግስተኛ የመኖሩን ያህል ኢዮብ የሚባል ቀማኛ ሊኖር ይችላል። ስለዚህ አንድ ምሳሌ ሊገልጸው አይችልም። ተስፋዬ ሲባል ግን ወላጆች ራቅ አድርገው የሚመኙትን ይገልጻል። የተስፋዬ ወላጆች የተመኙትን በልጃቸው እያዩ ከሆነ ምንኛ ደስ ይላቸዋል። አርቲስቶቻችን ወደፈረንጅ ጠጋ የሚል በሁለት ፊደል የሚገለጥ ስም ፍለጋ ሲባዝኑ የምናስተውለውም ከዚህ ከጊዜ ጋር የሚመጣ ጉዳይ ነው። ማንጠግቦሽን ማኒ፣ ጎሳዬን ጆሲ ቴወድሮስን ቴዲ አይነት እንደማለት ነው። ይህ ግን ሲስተሚክ ቫዮለንስ ተብሎ ሊፈረጅ የሚችል አይመስለኝም።
ቀደም ባለው ጊዜ አንዳንድ ደካማ መምህራን ተማሪዎቻቸውን የሚያሳቅቁ ነገሮችን አላደረጉም ማለት አይቻልም። በርካታ የኦሮሞ ልጆች በዚህ አይነት ተረብና አስተማሪዎች አማርኛ ለመናገር ሲሞክሩ በሰደቧቸው ምክንያት አቂመው ከፍ ሲሉ ወደ ትግሉ እንደተቀላቀሉ ሲናገሩ ይደመጣል።  ይህ አገር ለመገንጠል ምክንያት ባይሆንም የፖለቲካ ትርፍ ተዝቆበታል። ይህ ባሁኑ ትውልድ እንዳይኖር ማስተማር አስፈላጊ ነው። እንደ ተስፋዬ ግምት ወይም ታሪኩን እነዳጫወቱት ሰዎች ግምት ከተማ ውስጥ የሆነው አማራ ኦሮሞ ላይ ያደረሰው በደል ሳይሆን ከተሜው በጅምላው ገጠሬው ላይ የነበረው ግብዝነት እንደሆነ መረዳቱ አስፈላጊ ነው። በደል አልነበረም፣ አልተደረገም ወይም ሆኖ አያውቅም የሚል የሚኖር አይመስለኝም። ማንም ቢሆን ተፈጥሮ በሰጠው መልኩ፣ ቤተሰብ በሰጠው ስሙና፣ አዲስ ቦታ ላይ አላዋቂ ሆኖ በመታየቱ ሊሰደብ አይገባም ብሎ መነሳቱ የተሻለ ነው። ከዚህ የፖለቲካ ትርፍ መፈለግ ግን ደካማነት ነው።የሆነው ሆኖ አልፏል በዚህ አይነት ሰው የማንኳሰስ ተረብ ምክንያተ ያዘኑ ወገኖች ለደረሰባቸው የስሜት መጎዳት በግሌ በጣም አዝናለሁ። እንደ ከተማው ልጅነቴም ይቅርታ እጠይቃለሁ የሸገር ልጆችም ይህንን ሰሜት እንደሚጋሩኝ አምናለሁ። እንደ አንዳንድ የጭቃ ወስጥ እሾሆች ደባ ግን የዘር ጥላቻ እንዳልሆነ አጥብቄ እሞግታለሁ።
ዘመናዊ ትምህርት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን መሸርሸሩን ልብ ያለማለት የራሳችንን ጥፋት ለመሸፈንም ምክንያት ሊሆን ይችላል። ምሁራን ባህላችንን ባህላዊ እውቀታችንን እንደ ሁዋላ ቀር በመቁጠር የፈረንጆቹን በመኮረጅ የነበረንን ሁሉ ሲኮንኑ መኖራቸውን ልንክድ አይገባም። በዚህ ምክንያት የኦሮሞውም ሆነ የአማራው ባህላዊ እሴቶች ወደ ጎን ተገፍተው ነበር። በዚህ ውስጥ ከኦሮሞው የወጡ ምሁራንም አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ሊቀበሉ ይገባል። ፈቅደን የተውነውን ተነጥቀን ነበር ብንልም ወደ እውነት የሚያመጣን አይመስለኝም። የሚበጀን ጣት መጠነቋቆልና ወንጀል መፈለጉ ሳይሆን ከዘመናዊ ኑሮ ጋር አጣጥመን ልናሳድጋቸው የሚገቡንን ባህሎቸ መመርመርና ጠቃሚ በሚሆን መልኩ መልሶ ማሳደጉ ተገቢም አስፈላጊም ነው። ተስፋዬም ሲስተሚክ ቫዮለንስን ሲተነትንልን ሀሳቡ ይገባን ይሆናል። እስከዚያው ግን ተስፍሽ ስለ አባት አገሩ እድገትና ብልፅግና ቢጨነቅና የኛን ለኛ ቢተውልን ይሻለዋል እላለሁ።

Exiled Awramba Times Editor going back to Ethiopia (+Video)

Dawit Kebede
Dawit Kebede
Awramba Times (Washington DC) – Dawit Kebede, editor -in- Chief of the Awramba Times website is going back home after two years of stay as a political asylee in the United States.
In an interview with political analyst Yared Tibebu, in Washington DC, Dawit officially announced his decision to end his political asylum and head back home tomorrow, October 25, 2013.
Editor Dawit iterated his assessment that good journalism cannot be done away from the homeland and going back to the roots is important. Responding to the questions whether recent disagreements with some diaspora based political ‘activists’ had any weight in his decision to go back to Ethiopia, Dawit insisted that his love for the profession and his inability to excel in the field given immigrant life is the only decisive factor in his decision to go back to Ethiopia. Please watch his interview below.

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ እና የፕራይቬታይዜሺን ኤጀንሲ በፖለቲካ ጫና ስራውን በአግባቡ እየተወጣሁ አይደለም አለ፡፡

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የልማት ኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ድርጅቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት የተለያዩ የመንግስት ይዞታ የነበሩ ተቋማት በጥናት ለህዝብ ጥቅም የመሸጥ የመለወጥ ፤ ስልጣን ተሰጥትቶታል፡፡ ይህን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋች ሁኖብኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እስካሁንም የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ፣ የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት፣  በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው ኦሞራቴ እርሻ ልማት በመንግስት አመራሮች ጫና በብዙ ሚሊየን ብር ኪሳራ ወደ ግል ተዛውሯል፡፡
በባለሃብቶች እጅ ባሉ ባለስልጣኖች ምክር የሚመነዘሩት የባለሃብቶች እና የባለስልጣናት ትስስር ለሰፊው የህዝብ ጥቅም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ኪስ የሚያደልቡ አሰራሮች መጠቀሚያ እንደሆነ ነው ያመለከቱት ፡፡
ካሁን በፊትም ፤ የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ ወደ ግል የተዛወረበት መንገድ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ነበር ፡፡
የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት በሊዝ ተሺጦ ያለ አግባብ በሚልየኖች የሚቆጠር ብር በአየር ላይ ባክኖ ቀርቱዋል፡፡ በዚህም  ከ98 በላይ ቤተሰብ አሰተዳዳሪ ሰራተኛች ያለ የስራ ዋስትና ተብትነዋል፡፡
በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው የሚገኘው ሞራቴ እርሻ ልማት ያለበቂ ተመን ከተሸጡት ድርጅት መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ በስጦታ እንደ ተላለፈ የሚቆጠረው ይህ  የኮሪያ ባለሃብቶች የልማት ፕሮጀክት ወደ ግለሰቦች ሲዛወር ከህግ እና አሰራር ቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ነው በማለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ለልማቱ የተገዙትን መኪናዎች ጨምሮ  ከመሳሪያዎች ጋር ከ32 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ባለበት ሁኔታ፣ ከገበያ ዋጋ በታች በሆነ ሁኔታ ለሺያጭ ውሎዋል፡፡
ኤጅንሲው የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መቆጣጠር በአግባቡ የመስራት አቅሙን ያዳከመው የኢህአዴግ መንግስት ፣  ሸበሌ ትራንስፖርት  ኮምቦልቻ ፤ ወይራን የመሳሰሉ ድርጅቶች  ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፈው እንዲሰጡ  ከባለስልጣናት በቃል በተላለፈ ትእዛዝ ያለማንም መስረጃ ለሶስተኛ ወገን ተላልፈው ተሰጥተዋል።
የሸበሌ ማዴአዎች  ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፉ ከ 397 በላይ ተቀጣሪዎች ያለ ስራ ካሳ ወይም ምትክ የስራ ዋስትና ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
የየረር የዱቄት ፋብሪካ ተዘግቶ 41 ሰራተኛች ተፈናቅለው የስራ ዋስትና አጥተዋል፡፡ የሰራተኞች መብት እና ጥቅም እንዲሁም ውለታቸውን ባላከበረ ሁኔታ ተላልፈው ተሺጠዋል፡፡ የመንግስት ሃብቶች ወደ ግል ሲዛወሩ የሰራተኞችን መብት ባከበረ እና የስራ ዋስትናቸውን በተጠበቀ መካሄድ አለበት ቢልም ህጉ  ሳይተገበር ቀርቱዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች  በቁሳዊ እና የማህበራዊ ኪሳራ እንዲኖሩ መገደዳቸውን እና ልጆቻቸውን ለማስተማር እና  በልቶ ለማደር አቅም እንዳጠራቸው ለዘጋቢያችን ግልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኤጀንሲው ወደ ግል እንዲዛወሩ በ ንግድ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ግብርና ሜካናይዜሽንና ግዮን ሆቴል ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ከሁለት ወራት በፊት በወጣው ጨረታ ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር ሌሎች ሦስት የመንግስት የልማት ድርጅቶችም የባሌና የአርሲ እርሻ ልማት ድርጅቶች፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎችና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለሽያጭ መቅረባቸው ይታወቃል፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታቸውን አየር ላይ እንዳለ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ሦስቱ ድርጅቶች እንዳይሸጡ በመወሰኑ ከጨረታ ሒደቱ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ሁለቱ ማለትም ባሌና አርሲ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ለኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ እንዲሁም የኮንስትራክሽንና ቡና ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ኢንስቲትዩት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡
በ2004/5 በጀት አመት ጊዮን ሆቴል፣ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ፣ ቡና ቴክኖሎጂና ምህንድስና እንዲሁም የኢትዮጵያ ማእድን አክሲዮን ማህበር ወደ ግል የዛወራሉ ቢባልም ሳይሸጡ ቀርተዋል።
ቢሊቶ እርሻ ልማት፣ ሀማሬሳ የምግብ ዘይት አክሲዮን ማህበርና አርባ ጉጉ እርሻ ልማት በአዲስ ለጨረታ ከሚቀርቡ ድርጅቶች ውስጥ ሲካተቱ ፥ በሰኔ ወር መጨረሻ ለጨረታ ከቀረቡት ውስጥ የባቱ ኮንስትራክሽን ጨረታ ተሰርዞ በሌላ የመንግስት ድርጅት ስር እንዲተዳደር በቦርዱ መወሰኑን በኤጀንሲው የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ይናገራሉ።
ወደ ግል ሳይዛወሩ በመንግሥት እጅ ይቆያሉ የተባሉትና ኤጀንሲው ስትራቴጂክ ካላቸው ተቋማት መካከል የጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ)፣  ሙገር ሲማንቶ ፋብሪካ፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ድርጅት (ኢትፍሩት) ይገኙበታል፡፡
የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ቀደም ሲል በእጁ ላይ 287 ኢንተርፕይዞች ነበሩት፡፡ እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ 236 ኢንተርፕራይዞችን ለግል ካዛወረ በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት የቀሩት 51 የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ሃያዎቹን በ2005 ዓ.ም. ወደ ግል ለማዛወር  አውጥቷል፡፡ ኤጀንሲው የመንግሥትን ኢንተርፕራይዞች በሽያጭ ወደ ግል ማስተላለፍ በጀመረበት በ1987 ዓ.ም. አምስት ኢንተርፕራይዞችን ብቻ ነበር ወደ ግል ያዛወረው፡፡ በቀጣዩ ዓመት እስከዛሬ ድረስ ክብረወሰን ሆነው የተመዘገቡትን 127 ኢንተርፕራይዞች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሽያጭ አስተላልፏል፡፡
ከፍተኛ ሙስና እንደተፈጸመባቸው በተነገረው በዚህ ሽያጭ፣ ግብር ከፋዩ ክብረተሰብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ለዘረፋ ተጋልጧል።


የጎሳ ፌዴራሊዝም

የአማራው ጎሳ የጅምላ መፈናቀልና አማራውን ለማጥፋት የሚደረገው ስልታዊ የወያኔ ትግሬዎች ዘመቻ

article 39


ክፍል አንድ
የወያኔ ትግሬዎችና ስለ አማራ ህዝብ ያላቸው ግንዛቤና የቆየ ጥላቻ ምን ይመስላል?
የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው የትጥቅ ትግላቸውን ሲጀምሩ ለትግራይ ህዝብ ችግርና ኋላ ቀርነት ተጠያቂዎቹ ከዳግማዊ ዐጼ ምንሊክ ጀምሮ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በስልጣን ላይ የነበሩት ወያኔ አማራ ብሎ የሚጠራቸው መንግስታት እንደ ነበሩ በፖለቲካ ፕሮግራም ደረጃ ቀርጸው የትግራይን ህዝብ እንዳስተማሩ ቀድሞ የወያኔ ድርጅት አባል የነበረውና ዛሬ በስደት በሚኖርበት አስውስትራሊያ ሆኖ የወያኔን እኩይ ዓላማ በቆራጥነትና በሃቅ እያጋለጠ ያለው አቶ ገብረ መድህን ዓርዓያ በቅርቡ “እነማን ነበሩ” በሚል ርእስ በመረጃ አስደግፎ አሳውቆናአል። የወያኔ ድርጅት የአማራው ህዝብ በእነዚህ የአማራ መንግስታት ብሎ በሚጠራቸው ከዐጼ ምንሊክ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በነበሩት መንግስታት ዋነኛ ተጠቃሚ እንደነበረና የእነዚህም መንግስታት የስልጣን መሰረት እንደ ነበረ ሲያስተምር ቆይቶአል፤ ዛሬም ይህንኑ እያደረገ ነው ያለው። በዚህ ዓይነት የአማራን ህዝብ የእነዚህ ያለፉት መንግስታት የስልጣን መሰረት ነው በማለት ወያኔ የአማራውን ህዝብ ሲፈርጅ ቆይቶአል። የወያኔ ትግሬ መሪዎች የትግራይ ህዝብ ዐጼ ምንሊክን በመሳሰሉት የአማራ ተወላጆች የሆኑ የኢትዮጵያ መሪዎች እንደ ኢትዮጵያዊ እንደማይታይ ለትግራይ ህዝብ ያስተምሩ ነበር። እነዚህም የትግራይን ህዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ የማይቆጥሩ የአማራ መሪዎች የትግራይን ህዝብ ሆን ብለው እንዴት ለችግር፤ ለጎስቁልናና ለእንግልት እንዳበቁት የወያኔ ድርጅት መሪዎች (ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉትም ሆኑ ድርጅቱን ጥለው በመውጣት ዛሬ ተቃዋሚ ነን ብለው የዛሬው የትግራይ ህዝብ ሰቆቃ ከደርግ ጊዜው የባሰ ነው ብለው የሚነግሩን ጭምር) በሰፊው አስተምረዋል። እንግዲህ የወያኔ መሪዎች የአማራ ንጉስ ብለው በሰየሟቸው በዐጼ ምንሊክ ተጀመረ ያሉት የትግሬዎች ጭቆና ተከታዮቻቸው ናቸው በሚሏቸው የዐጼ ሃይለ ስላሴና የደርግ መንግስታትም ዘመን ቀጥሎ የትግራይ ህዝብ በመጨረሻ ተማሮ “የአማራውን የደርግ” መንግስት ለመጣል እንደ ተነሳ እንረዳለን። የወያኔ መሪዎች የትግራይን ህዝብ ችግር የአማራ ተወላጆች በሚላቸው የኢትዮጵያ መሪዎች እንደተፈጠረ አድርገው እንዴት እንደሚያዩና እንደሚቀሰቅሱ ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ እኔ በምኖርበት በሆላንድ ሀገር በስደት የሚኖረው የቀድሞው የወያኔ ድርጅት መሪና ጠቅላይ የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ ወያኔን ተቃዋሚ ነኝ ብሎ ካለ በኋላ እንኩዋን በሚከተለው መልክ ከጻፈው ጽሁፍ እንረዳለን።
menelik
እምዬ ምንሊክ
የሸዋው የፊውዳል ባላባት የሃይለ መለኮት ልጅ (ምንሊክእንደማናቸውም የሸዋ መኳንንቶች ሁሉ ከጥንት ጀምሮ በጣም የስልጣንጥመኛና ፀረ-ትግሬ የነበረ ሰው ነበረ። በንግስ ዘመኑ ሁሉ ዳግማዊምንሊክ የዘመናዊ የጎሳ ቅራኔና ግጭት ዋና ፈጣሪ ነበር። ዳግማዊምንሊክ በአድዋ በጣሊያን ላይ የተጎናፀፈውን ድል ተቀናቃኞቹ ሊሆኑበሚችሉት በተለይም በመንገሻ ዮሃንስና በአሉላ አባ ነጋ አመራር ሥርበነበሩት የትግራይ መኩዋንንቶች ላይ ከፍተኛ የበላይነትን እንዲቀዳጅአደረገው። ዳግማዊ ምንሊክ ትግራይን የመከፋፈልና የማዳካም ዕድልነበረው። የምንሊክ ጦር የጣሊያኑ የቅኝ ገዢዎች ጦር ያደረሰውን ያህልጥፋት እንዲያደርስ በትግራይ ላይ መረን ተለቀቀ። የትግራይ ህዝብይህንን ጊዜ ዘመነ ሸዋ ብሎ ያስታወሰዋል፤ ይህም ማለት ትግራይበሸዋ አገዛዝ ሥር  የወደቀብት ዘመን ማለት ነው። የምንሊክ አቋምየተመሰረተው በሥልጣን ወዳጅነቱና ትግራይ ሊናቅ የማይገባው ጠላትነው በሚለው አመለካከቱ ላይ ነበር። በርካታ የትግራይ ምሁራንምንሊክ ትግራይን እንደራሱ ህዝብ የማያይ አድርገው ይቆጥሩታል።የምንሊክ ሰሜኑን የመከፋፈልና የማዳከም ሃሳብ የትግራይን ግማሽጣሊያን በቅኝ ግዛትነት ይገዛው ዘንድ በመስጠት ሂደት የታጀበ ነበር።ምንሊክ አፍሪካ ለቅርጫ በቀረበችበት ዘመን ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝየማድረግ ፍላጎት እንደነበራት እምብዛም እውቀት አልነበረውም።ምንሊክ ትግራይ አንዴ ለሁለት ከተከፈለች እሷን እንደፈለጉ መግዛትይቻላል ብሎ ያምን ነበር። ትግራይን ለመቅጣት ምንሊክ በየዋህነትየወቅቱ የቅኝ ገዢዎች ወጥመድ ውስጥ ገባ። ኢጣሊያ የምንሊክንድክመት በመጠቀም ወደ ደቡብ (ማለትም ከኤርትራ ወደ ትግራይመስፋፋት ቀጠለች። ምንሊክ ጣሊያኖች ኤርትራን ይዘውእንዲቆዩ ያደረገበትን ምክንያት በተመለከተ ክርክር ውስጥ ሳንገባ አንድ የማይካደው ሃቅ ግን ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ለሁለት ጌቶችማለትም ከመረብ በላይ ያለው ህዝብ ለጣሊያን፤ ከመረብ በታች ያለው ህዝብ ደግሞ ለምንሊክ ተከፍሎ ተሰጠ። ይህ ለወትሮውአንድ ወጥ በነበሩትና አንድ ላይ ቢሆኑ (የምንሊክንሥልጣን ለመቀናቀን በሚችሉት ትግሬዎች መካከል የተፈጠረው ከፋፋይመስመር (fault line) መነሻ ወይም ምንጭ ነው። በዚህም ምክንያት ነው የሸዋ አማራ የገዢ መደብ ትግሬዎችን የማዳከም ዘመቻበዚህ ታሪካዊ ወቅት የተጀመረው:: (Aregawi Berhe,  ”Origins & Development of the National Movement in Tigrai; a Socio-historical Analysis”,  Institute of Social Studies, the Hague, 1993 (Aregawi Berhe was former chairman of the TPLF አረጋዊ በርሄ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ ዓ.ም ሆላንድ ውስጥ ሄግ ከተማ በሚገኘው ኢንስቲትዩት ኦፍ ሶሻል ስተዲስ በተሰኘው ተቋም ውስጥ ለማስተርስ ዲግሪው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከጻፈው የተወሰደ (ጥቅሱን ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ የተረጎምኩት እኔው እራሴ ነኝ)።
ከላይ ከጠቀስኩት የአረጋዊ  ጽሁፍ እንደምንረዳው አረጋዊና ተከታዮቹ ታሪክን በመከለስ ኢትዮጵያን ከጣሊያን የቅኝ አገዛዝ እንዲከላከልና ነጻነቷን እንዲያስጠብቅ የተደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ በዐጼ ምንሊክ መሪነት የዘመተውን ከመላው የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጣ የኢትዮጵያ አርበኛ ትግራይን ወሮ ዘረፈ፤ አደኸየ ብለው ወነጀሉ። በዚህም ምክንያት የአድዋ ዘመቻ አዝማችና መሪ የነበሩት ምንሊክንና  የአማራ ህዝብ በትግራይ  ልሂቃን ዘንድ እንደ ጠላት ተቆጥረው ከትውልድ ትውልድ የተላለፈ የትግሬዎች ጥላቻ ዒላማ ሆኑ። እስቲ ከዚህ በታች የወያኔ ድርጅት የፖለቲካ ፕሮግራም ስለ አድዋ ጦርነትና እሱን ተከትሎ መጣ ስለሚለው የትግራይ መጨቆን ያለውንእንመልከት።
1881 ..  ትግራይ እንደገና በሸዋ አማራ ገዢዎች አፈናና ጭቆና ስር ወደቀች። ከባድ ታክስ በትግራይ ህዝብ ላይ ተጣለ።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሆን ተብሎ ካለ ስንቅ የተላኩ የምንሊክ ጦር ወታደሮች የትግራይን መንደሮች ዘረፉት። ባጭር ጊዜ ውስጥየትግራይ ህዝብ የኢኮኖሚና የማሀበራዊ ሁኔታ በፍጥነት አሽቆለቆለ። ከዚህ በተጨማሪ ሆን ብሎ የትግራይን ህዝብ ቋንቋ ባህልናታሪክ ለመጫን እርምጃዎች ተወሰዱ። እነዚህ የጭቆና እርምጃዎች የትግሬዎችን ብሄረተኛ ስሜት በመቀስቀስ ኃይለኛ የሆነ ብሄራዊቅራኔን ፈጠሩ TPLF Political Program adopted at the Second Congress,1983 (ለዝርዝሩ በሁለተኛው  የወያኔ ሀርነት ድርጅት ጉባኤ ላይ የጸደቀውን የ1975 ዓ.ም. የፖለቲካ ፕሮግራም ይመልከቱ) (ከላይ የጠቀስኩትን ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ የተረጎምኩት እኔው እራሴ ነኝ)።
የትግራይ ብሄረተኞች እየሰሙ ያደጉትን ሀሰተኛ የምድጃ ዳር ታሪክ በተመለከተ የሚከተለውን ለአንባቢ ላስተዋውቅ፤
በዚያ ቀን የሸዋ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ዘረፈው፤ በአካባቢው የነበሩ መንደሮችም በሙሉ ተዘረፉ። እንደርታምእንዳልነበረች ሆነች። በየመንገዱ ትልቅ ትንሽ ህፃን ሳይሉ ሰለቡት። ቀጥሎም የምንሊክ ሰራዊት እንደርታን አወደማት። እንዳልነበረችሆነች። ብቻ የወንድ ልጅ ይሁን እንጂ የተገኘ ሰው ሁሉ ይገደላል። የእንደርታ ሰዎችም ቢሆኑ ዝም ብለው አልታረዱም። በየቋጥኙናበየጫካው እየተደበቁ የምንሊክን ሰራዊት ሲፋለሙት ነበር። የምንሊክ ሰራዊት የመግደልና የመስለብ ሱስ ያለበት ነው። ሰዎችንበገደለና በሰለበ ቁጥር ይፎክራል። ሌላው ይቅርና በመላ ኢትዮጵያ የተከበረውን የአብርሃ ወአጽብሃ ገዳምም እንዳለ ዘርፈውታል(ምንጭ፤ ገብረ ኪዳን ደስታ የትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትላንት እስከ ዛሬ በሚለው መጽሃፉ ውስጥ ከጠቀሰው ታሪክኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በትግርኛ ቋንቋ ከታተመው መጽሃፍ የተጠቀሰ።
ስለ አማራ ህዝብና ስለ እነ ዐጼ ምንሊክ፤ ዐጼ ሃይለስላሴ ወዘተ በወላጆቻቸው ጥላቻን እየተጋቱ ያደጉት የዛሬዎቹ የወያኔ መንግስት መሪዎች ከልጅነት ጀምሮ ጥርሳቸውን ሰብረው ያደጉበትን በምድጃ ዳር የተማሩትን የጥላቻና የውሸት ታሪክ ከዘመናዊ የብሄረተኛነት አስተሳሰብ ጋር አዳቅለው አክራሪውንና ዛሬ ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለውን የትግራይ ብሄረተኛነት በማቀንቀን ኮትኩተው አሳደጉ። ዛሬ የትግራይ ብሄረተኛነት ጥቂቶች የሚጋሩት እብደት ሳይሆን እንደ ጀርመኑ የናዚ ወይም Aregawi-berhe-እንደ ጣልያኑ የፋሽዝም ርዕዮተ ዓለም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የጎሳ ተወላጆቹን አስተሳሰብ በመቀየርና ከሰውነት ደረጃ በማውጣት የወያኔ ትግሬዎች ከትግሬ ጎሳ ውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ በተለይ ደግሞ የታሪክ ደመኛችን ነው የሚሉትን የአማራን ህዝብ እንደ አደገኛ አውሬ የሚያዩበትና የዚህንም ህዝብ ህልውና ጨርሰው ለማጥፋት የተነሱበት ደረጃ ላይ አድርሶአቸዋል። የትግሬዎች አካላዊ ገጽታ፤ መልክ፤ ባህልና ታሪክ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር መመሳሰል ሌላው ኢትዮጵያዊ የወያኔ ትግሬዎችን እንደ እራሱ ወገን እንጂ ለኢትዮጵያና ትግርኛ ተናጋሪ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ይህን ያህል ጥላቻ ያላቸው ወገኞች ናቸው ብሎ እንዳይገምት አድርጎታል፤ አዘናግቶታልም። ስለዚህም የኢትጵዮጵያ ህዝብ የወያኔ ትግሬዎችን እዚህ ደረጃ ላይ ሳይደርሱና ብዙ ጥፋት ሳያደርሱ ሊያቆማቸው የሚችልበት ብዙ አጋጣሚዎች አልፈውታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በሀገራችን በህዝቡ ዘንድ ቀርቶ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን በሚሉት ዘንድ ስለ ጎሳ ብሄረተኛነት (ethnic nationalism) ያለው ግንዛቤ እጅግ የሚያሳዝን በመሆኑ ዛሬ ወያኔ እያደረሰ ያለውን የጎሳ ጽዳትና ጎሳን መሰረት የጅምላ ፍጅት ይከሰታል ብለው ለማሰብ አልቻሉም። በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ውስጥ ያንድ የኢትዮጵያ ጎሳ አባሎች (ትግሬዎች) የመንግስት ስልጣን ይዘው አንተ ይኸ ክልልህ ስላልሆነ ከዚህ ለቀህ ውጣ በማለት የሌሎችን ጎሳ አባላት (አማራን፤ አፋርን፤ አኑዋኮችን ወዘተ) እንደ አውሬ በጦር መሳሪያ የሚያሳደዱበትን፤ ህጻናትና አሮጊቶች ሽማግሌዎችና አቅመ ደካማዎችን ለሞትና ለዘግናኝ ስቃይ የሚዳርጉበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም።
የወያኔ ትግሬዎች ዓላማ አማራ ብለው የሰየሙትን ጨቋኝ የደርግ ስርዓት ጥለው ለትግራይ ህዝብ ህይወት የሚያሻሽል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ማምጣት ነበር። ይህንን ዓላማቸውን አስመልክቶ የቀድሞው የወያኔ መሪ በ ዓ.ም በጻፈው ጽሁፍ የሚከተለውን ብሎ ነበር። የትግራይ ህዝብ የወል ምኞት ጨቋኙን የአማራ (የደርግ) መንግስት መጣል ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን (የትግሬዎችን) ህይወት የሚያሻሽል የማህበራዊና የኢኮኖሚ ለውጥን ማምጣት ነበር”። አረጋዊ በርሄ “How the Media of the TPLF Emerged and Countered the Dominant Media of the Ethiopian State: Can it be a Viable Alternative for Social Transformation?”, a paper written by Aregawi Berhe for a degree at the Hague Institute of Social Studies, 1992) (ጥቅሱን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ትርጉም የራሴ የአሰፋ ነጋሽ ነው)። ይህን ከላይ አረጋዊ በርሄ የገለጸውን የወያኔ ዓላማ በማሳካት በኩል ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ምን እንዳደረገ፤ እንዴት የትግራይን ገጽታና የትግራይ ተወላጆችን ህይወት ጉልህና አዎንታዊ በሆነ መልክ እንደቀየረ ማንም የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተል፤ እንደዚሁም በራሱ ሀገር የበዪ ተመልካች የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚያውቀው ዝርዝር ውስጥ ለመግባት አልፈልግም። የትግራይ የጎሳ ብሄረተኞች ግን ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ለህዝባቸው ያለሙትን ልማትና ማህበረሰባዊ ለውጥ እንዳመጡ መካድ አይቻልም።
የጎሳ ፌደራሊዝም፤ ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካና የጎሳ ግጭት በኢትዮጵያ
የወያኔ መንግስት የተመሰረተበትና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የመንግስታዊ ስርዓት መሰረት የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም የጎሳን ማንነትና ልዩነትን ዓይነተኛ የፖለቲካ ማደራጃ አድርጎአቸዋል። የጎሳ ፌዴራሊዝም ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው። ዲሞክራሲ ሁሉን አሳታፊ እንጂ አንድን ግለሰብ በጎሳ ማንነቱ ምክንያት ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርግ አይደለም። ፖለቲካ በጎሳ ማንነትና መስፈርት ላይ ተመስርቶ አንድን ሰው አንተ የእኔ ጎሳ አባል አይደለህም ብሎ በጎሳ ማንነቱ ምክንያት ሲያገል፤ ሌላውን ደግሞ አንተ የጎሳ አባሌ ነህ ብሎ ሲያሳትፍና ሲያቅፍ፤ ይህን አይነቱ ጎሳን መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ዲሞክራሲ የሚባለውን አስተሳሰብ በጽኑ ይቃረናል። በዚህም ምክንያት በጎሳ ማንነት ላይ ተመስርቶ የሚደራጅ የፖለቲካ ስርዓት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ የተለያየ የእምነት ተከታዮች፤ የተለያዩ የጎሳ ተወላጆች እንደ ሰው ወይም እንደ ሰብዓዊ ፍጡር በሚያስተሳስሯቸውና በሚጋሯቸው በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደ አንድ ሀገር ዜጎች እንዳይገናኙ የሚያደርግ በመሆኑ አፍራሽ እንጂ ገንቢ አይደለም። የጎሳ ፌዴራሊዝም በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በልዩነቶቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ ሊያቋርጥ የማይችል ጥላቻን በማራገብ ለጋራ ጥፋትና እልቂት የሚጋብዝ፤ በባህል መጠበቅ፤ በጎሳ መብት መጠበቅ ስም ያንድ ጎሳ ልሂቃን እኛ የዚህ ጎሳ ብቸኛ ተወካዮች ነን ብለው ባንድ ነጻ ማህበረስብ ውስጥ ሊደረግ የሚገባውን በጎሳ ማንነት ሳይሆን በፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ጤናማ የፖለቲካ ውድድር ወይም ፉክክር የሚሸሹበትን ኢ-ዲሞክራሲያዊ አመለካከትና አሰራር ያራምዳል። ይህም የጎሳን ማንነት መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ስርዓት ወደ ፋሽስታዊ የዘር ፍጅትና የእርስ በርስ ጥላቻ የሚያመራ አደገኛ ርዕዮተ ዓለም ነው። የፈረሰችው የትላንትናዋ ዩጎዝላቪያ የጎሳ ፌዴራሊዝም በአንድ ሀገር ላይ የሚያስከትለውን ጥፋትና ፍጅት አሳይታናለች። የጎሳ ፌዴሊዝም አንዱን ሕዝብ በሌላው ላይ ያነሳሳል ምክንያቱም የጎሳ ፌደራሊዝም ባፈጣጠሩ ህዝብን በሚለያይ ማንነት ላይ የተመሰረተና በልዩነት ላይ  ያተኮረ ስለሆነ ነው። የጎሳ ፌደራሊዝም የጎሳን ማንነት ብቻ በማጉላት ሌሎች የማንነት መገለጫዎችንያደበዝዛል፤ ያንድ ሃገር ዜጋዎች በመካካላቸው የግንብ አጥር እንዲሰሩ ያደርጋል፡ ያለያያል፡ ያቃቅራል። አንድ-ወጥ ጎሳ ለመፍጠርና “ንጹህ ደም ያላቸውን የአንድ ጎሳ ተወላጆች” ባንድ ኩታ-ገጠም ክልል ውስጥ ለማሰባሰብ የሚደረገው ጥረት በግድ ከዚያ ከንጹሁ ጎሳ ተወላጆች ውጭ ያሉትን የሌሎች ጎሳ  ተወላጆችን “ከንጹሁ ጎሳ ተወላጆች” ክልል በሃይል ወደ ማስወጣቱ የጭፍጨፋ ሂደት ያመራል። ትላንት በምስራቅ ወለጋ፤ በጉራ ፈርዳ ዛሬ ደግሞ በቢኒሻንጉል የታየው ዘግናኝ ድርጊት የጎሳ ፌዴራሊዝም ውጤት ነው። የጎሳ ፌዴራሊዝም ዋና አራማጅ
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ (ፎቶ: addis fortune)
የሆኑት የኦሮሞ ብሄረተኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አሜሪካን ሀገር ይታተም በነበረ ኢትዮጵያን ኤክዛምነር (Ethiopian Examiner) በሚባል መጽሄት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በሰኔ ወር 1993 በጻፉት አንድ መጣጥፍ ውስጥ የሚከተለውን ሃሳብ አስፍረው ነበር።  “ኦሮሞዎች የኦሮሞ ዞኖች ወይም ቀጠናዎች ሁሉ ባንድ ላይ ተጠቃለው አንድ የኦሮሞ ክልል ሥር እንዲሆኑ ይፈልጋሉ (Bulcha Demeksa, Ethiopian Examiner, June 1993)። ይህ የአቶ ቡልቻ ሃሳብ በረጅም ትልሙ አንደ-ወጥ (ethnically homogenous) የሆነ ያንድ ጎሳ ተወላጆች ብቻ የሚኖሩበት ክልል ለመፍጠር፤ ብሎም ከኦሮሞ ጎሳ ውጭ ያሉ ሌሎች ጎሳዎችን በማስወገድ ራሱን የቻለ አንድ ነጻ ሀገር ለማቋቋም ያለመ ሂደት መሆኑን ማንም የማገናዘብ ችሉታ ያለው ሰው ይረዳል። ጎሳን መሰረት ያደረገ ክልል በመጨረሻ እናንተ የእኛ ጎሳ አባሎች ስላልሆናቸሁ ከዚህ ውጡ ወደሚለው የጎሳ ጽዳት ( ethnic cleansing ) እንደሚያመራ ትላንት በምስራቅ ወለጋ፤ በጉራ ፈርዳ፤ በቤኒሻንጉልና በኦጋዴን የተከሰተው ሁኔታ ያሳየናል። አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ተቀባይነት ያለውና ጭራሽ ሊቀለበስ የማይችል እውነታ መሆኑን በሚከተለው መንገድ እርግጠኛ ሆነው በዚሁ ኢትዮጵያን ኤክዛምነር በተሰኛው ባንድ ወቅት በአሜሪካ ይታተም በነበረው ወርሃዊ መጽሄት ላይ እ. አ. አቆጣጠር በግንቦት 1993 በጻፉት ጽሁፍ ውስጥ ይነግሩናል። “በኢትዮጵያ በጎሳ ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝም ወደ ኋላ ሊመለስ አይችልም ምክንያቱም አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፈልገዋልና”( Bulcha Demeksa, Ethiopian Examiner, May 1993) አቶ ቡልቻ ይህንን ከፍተኛ ድፍረት የተሞላበት፤ በጥናትና መረጃ ላይ ያልተመሰረተ አስተያያት ሲሰጡ ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቶ እሳቸው በደንብ አውቀዋለሁ፤ ጥቅሙን አስጠብቅለታለሁ የሚሉትን የኦሮሞን ህዝብ እንኳን ጠይቀው፤ አስተያየቱንና ፍላጎቱን ሰብስበው አይደለም። በወያኔ ትግሬዎች መንግስት ከተደረገው ከአስራ አራት ዓመታት የጎሳ ፖለቲካ ሰበካ እንኳን በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ለጎሳ ፌዴራሊዝም ልቡን እንዳልሰጠ በግንቦት ወር 1997 ዓ. ም የተደረገው ብሄራዊ ምርጫ አሳይቷል። በጎሳ ሳይሆን ሀገር-አቀፍ አጀንዳ አንግቦ ውድድር ውስጥ የገባው የቅንጅት ድርጅት ያገኘው ከፍተኛ ድጋፍ የአቶ ቡልቻንና ከወያኔ ጀምሮ እስከ ዛሬዎቹ የመድረክ አባሎች ድረስ ያሉትን የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ክፉኛ አስደንግጦአል። መድረክም የዚህ የጎሳ ፖሊቲካ ክስረት ያስደነገጣቸው የጎሳ ፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ ሆኖ ብቅ ያለው ይህንን የጎሳን ፖለቲካ ውድቀት በጋራ ሆኖ ለመከላከል፤ ጎሳ-ዘለልና ሀገር-አቀፍ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸውን ወገኖች በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ያላቸውን ተቀባይነት ለመዋጋት ነው። የእነ ሰዬ አብርሃም ከወያኔ ወጥቶ መድረክ መግባት አልሸሹም ዞር አሉ ነው፤ ወደዚያው ጥርሱን ወደነቀለበት የጎሳ ፖለቲካ የደራበት የመድረክ ሰፈር ተመልሷል።  የዚህ ጽሁፍ ሁለተኛው ክፍል ከዚህ ቀጥሎ ይቀርባል!!!!!!
ክፍል ሁለት
የጎሳ ፌዴራሊዝምና የኢትዮጵያዊ ዜግነት መብት በኢትዮጵያ
በቅርቡ የአማራ ጎሳ ተወላጆችን መፈናቀል አስመልክቶ አስያየታቸውን ከሰጡ ግለሰቦች መካከል አፍቃሪ-ኦነግ የሆነው የኦሮሞ የጎሳ ብሄረተኛ ጃዋር መሀመድ ለአንድነት ጋዜጣ የአማራው ህዝብ ችግር ተቆቋሪ በመምሰል በሰጠው ቃለ መጠየቅ አማራው ከቤኒሻንጉል የተፈናቀለው በወያኔ ተንኮል እንጂ የጎሳ ፌዴራሊዝም ባመጣው ችግር ምክንያት አይደለም በማለት የጎሳ ፌዴራሊዝም ውጤት የሆነውን ችግር ለማስተባበል ሞክሮአል። ጃዋር የአማራው ህዝብ መፈናቀል ምክንያት የወያኔ መንግስት ተንኮል እንጂ የጎሳ ፌዴራሊዝም ፖሊሲ የፈጠረው ችግር አይደለም በማለት የጎሳ ፌዴራሊዝም የዜግነትን መብትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገበት ክልል ሂዶ የመኖርና ህይወቱን የመምራት መብት እንዳለው አድርጎ ለማቅረብ ሞክሮአል። ይህ እጅግ ስህተተኛና የጎሳ ፌዴራሊዝምን አጥፊነትና ሀገር-አፍራሽነት፤ የጎሳ ግጭትና የጥላቻ ፈጣሪነት ለመካድና ለመሸፋፈን የሚደረግ ጥረት ነው። እንደ ጀዋር መሃመድ ያሉ የነጻይቱን ኦሮሚያ ሀገር መፈጠር የሚጠባበቁ የኦሮሞ ብሄረተኞችም ሆኑ በሀገር ቤት ተደራጅተው በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (የአቶ ቡልቻ ደመቅሳና የዶክተር መረራ ጉዲና ድርጅቶች ተዋህደው የፈጠሩት የጎሳ ፌዴራሊዝም አራማጅ ድርጅት ነው) ድርጅቶች፡ እንደዚሁም ሌሎች የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ይህ ዛሬ በወያኔ ትግሬዎች መንግስት ስራ ላይ የዋለው የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት በመጨረሻ ኢትዮጵያን በጎሳ ወደሚበታትንንና የሚመመኙትን ነጻ ኦሮሚያን፤ ኦጋዴንያን፤ ወዘተ ምስረታ ሂደት እያመራ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ። በጎሣ ማንነት ላይ የተመሰረተው የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት የግለሰብን መብትና ነጻነት የዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገለጫ አድርጎ ስለማያይ፤ እንዲያውም ይህንን የግለሰብ መብት ስለሚጻረርና ከግለሰብ መብት በፊት የቡድንን መብት ስለሚያስቀድም በተፈጥሮው ዴሞክራሲን ይጻረራል። ቬስና ፖፖቭስኪ የተባለች ጸሀፊ እንዳለችው “ዘመናዊ የዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ የተመሰረተው በጎሳ ወይም በብሄር-ብሄረሰብ ማንነት ላይ ሳይሆን በግለሰብ ነጻነትና ምርጫ ላይ ነው። አንድ ግለሰብ የፖለቲካ ነጻነቱን (የዜግነት መብቱን) የሚቀዳጀው በጎሳው አማካይነት ሳይሆን ራሱ ነጻ ሰው ሆኖ የሚፈልገውን መምረጥ ሲችል ብቻ ነው። በትክክለኛ መንፈሱ አንድ ግለሰብ የፖለቲካ ነጻነቱን የሚጎናጸፈው በጎሳው አማካይነት ሳይሆን ራስ-በቅ ዜጋ ሆኖ ነው” (Vesna Popovski, Yugoslavia: Politics, Federation, Nation, 1995) (ጥቅሱን ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ የተረጎምኩት እኔው እራሴ ነኝ).
እስቲ የወያኔ ህገ መንግስት የሚደነግገውን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ከዚህ ቀጥለን እንመልከት።
የወያኔ መንግስት የደነገገው ህገ መንግስት አካል የሆነው ጠንቀኛው አንቀጽ ፰ ፡
አንቀጽ ፰ የህዝብ ሉዓላዊነት ።
፩ – “ኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው።
፪ – ይህ ህገ መንግስት የሉዓላዊነታቸው መገለጫ ነው።
፫ – ሉዓላዊነታቸውም የሚገለጸው በዚህ ህገ መንግስት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት ይሆናል”።
ይህ ከላይ የተጻፈው አንቀጽ ከውጭ ሲያዩት ለኢትዮጵያ ህዝብ መብት የሚያጎናጽፍ ቢመስልም፤ መብትና ስልጣን የሚያጎናጽፈው ወያኔብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለሚላቸው ምንነታቸውና ልዩነታችው እንኳን በቅጡ ተለየተው ላልታወቁ ስብስቦች ነው። በዚህም ምክንያትይህ አንቀጽ በማንኛውም ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ የሚታወቀውን የአንድን ሰው የዜግነት መብት በህገ መግንስቱ ውስጥ አይደነግግም። በዚህም ምክንያት ይህ ህገመንግስት መብት ከየሚሰጠው ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለሚባሉ በቋንቋ መስፈርት ለተለዩ ክልሎች ነው። በዚህ ህገ መንግስት መሰረት አንድ ግለሰብ መብቱ የሚታወቅለት የጎሳ ማንነትን መሰረት አድርገው በተሰየሙት ብሄር፤ ብሄረሰብና ህዝቦች በሚባሉት ስብስቦች በኩል ነው። አንድ ሰው መብት የሚኖረው የእነዚህ ብሄር፤ ብሄረሰብና ህዝቦች የሚባሉ ስብስቦች አባል በመሆን ነው እንጂ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ዲሞክራሲያዊ ሀገሮች ውስጥ እንደሚታየው በግለሰብ ሰውነቱ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለም። ስለዚህ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚኖረው መብት በጎሳ ማንነት ላይ ተመስርተው በታወቁት ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሚባሉ ስብስቦች አማካይነት ብቻ ነው የሚረጋገጥለት።  አንድ ኢትዮጵያዊ መብቴ ነው ብሎ የሚለውም ነገር ተቀባይነት ያለው በእነዚህ በጎሳና በቋንቋ መስፈርት ተለይተው በታወቁት ክልሎች ውስጥ ነው እንጂ በመላው የኢትዮጵያ ክፍሎችና ክልሎች ውስጥ አይደለም። ስለዚህ ዛሬ ኢትዮጵያ በምትደዳደርበት ህገ መንግስት አንድ ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ከክልሉ ውጭ ይዞት የሚሄደው፤ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል መብቴ ነው ብሎ እንዲከበርለት የሚጠይቀው መብት አልተሰጠውም።
yacob
ዶክተር ያዕቆብ ሃይለማርያም
በዚህ ምክንያት አንድ የአማራ ጎሳ ተወላጅ ዛሬ ኦሮሚያ፤ ደቡብ፤ ትግራይ፤ ሱማሌም ሆነ ቢኒሻንጉል ወዘተ ተብለው በተከለሉት የኢትዮጵያ የጎሳ ክልሎች ውስጥ እንኳን ቢወለድ አንተ የዚህ አካባቢ ጎሳ ተወላጅ ስላልሆንክና አማራ ስለሆንክ ከዚህ ወጥተህ ወደ ራስህ የአማራ ክልል ሂድ ተብሎ ሊባረር ይችላል። ዶክተር ያቆብ ሃይለማርያም ዛሬ አማራውም ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የኢትዮጵያ ክልል ሂዶ መኖር ይችላል ይህንንም ህገ መንግስቱ ይፈቅዳል እያለ በአሜሪካን ሬድዮ የአማርኛ ክፍል እየቀረበ ሲያስረዳ ቆይቶ አል። እውነቱ ግን ይህ አይደለም። ዶክተር ያቆብ ዛሬ በስራ ላይ የዋለው ቋንቋንና የጎሳ ማንነትን መሰረት አድርጎ የተቀረጸው ህገመንግስት መብትን ከጎሳ ማንነት ጋር በማያያዝ የአንድ ኢትዮጵያዊ መብት በጎሳ ማንነቱ ከተከለለት ክልል ውጭ እንደማይሻገር አይገልጽም። ይህን መግለጽ የጎሳን ፌዴራሊዝም አጥፊነትና አፍራሽነት ስለሚያጋልጥ የጎሳ ፌዴራሊዝም ደጋፊ የሆነው ዶክተር ያቆብ ሃይለማርያም ይህንን ጉዳይ በጭራሽ አያነሳውም። ዶክተር ያቆብ የጎሳ ፌዴራሊዝም ደጋፊ መሆኑን የሚያረጋግጥልን አንዱ ማስረጃ ከቅንጅት መፍረስ በኋላ የተመሰረተውን ህብረ-ብሄራዊ ይዘት ያለውን የአንድነት ፓርቲ በጎሳ ፌዴራሊዝም መርህ የሚያምነው የመድረክ አባል እንዲሆን የተጫወተው ከፍተኛና ቁልፍ ሚና ነው። ዶክተር ያቆብ በሚሰጣቸው የሬድዮ መግለጫዎች የዛሬው ህገመንግስት የኢትዮጵያን ዜጎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመኖር መብት ያረጋግጣል ሲል የዛሬው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ዋና የማእዘን ራስ የሆነውን የአንቀጽ ስምንት ትርጉምና አንድምታ አጥቶት ወይም ዘንግቶት አይደለም።
እንደሚታወቀው መድረክ የኢትዮጵያ ህዝብ ለቅንጅት በግንቦት 1997 ዓ.ም የሰጠው ሰፊ ድጋፍ ያስደነገጣቸው የጎሳ ፌዴራሊዝም አራማጆች የመሰረቱት ስብስብ ነው። የህግ ባለሙያ የሆነው ዶክተር ያቆብ ሃይለማርያም ሊነካው የማይፈልገው ጉዳይ ዛሬ አማራው ከቢኒሻንጉልም ሆነ ከጉራ ፈርዳ የሚፈናቀልበት ምክንያት ይህ በወያኔ ህገ መንግስት ውስጥ የተሰነቀረውና አንቀጽ 8 ስር የሰፈረው የጎሳ ፌዴራሊዝም ዋና መገለጫ የሆነው ድንጋጌ ነው። ኢትዮጵያ የብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሀገር ነች በሚል የቡድን መብትን ከግለሰብ መብት በሚያስቀድም ህገ መንግስት ውስጥ የተሰነቀረው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ህይወቱን ሊመራ ይችላል የሚል አንቀጽ የአንድን ኢትዮጵያዊ መብት ሊያስጠብቅ እንደማይችልና አንድ ኢትዮጵያዊም እኔ የኢትዮጵያ ዜጋ ስለሆንኩኝ መብቴ በማናቸውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ሊከበር ይችላል ለማለት እንደማያስቸለው ያለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ልምዶች አሳይተውናል። ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ኦሮሚያ ክልል በሚባለው የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የሚገኙ አያት ቅድመ አያቶቻቸው እዚያ ተወልደው ያደጉ ኦሮሞ ያልሆኑ ተወላጆች በተለይም በዚህ የኦሮሚያ ክልል ተብሎ በተሰየመው ክልል ውስጥ በስፋት የሚኖሩት የአማራ ተወላጆች እናንተ መጤዎች ስለሆናችሁ የትምህርትም ሆነ የስራ እድል አይገባችሁም፤ ቅድሚያ የሚሰጠው ለኦሮሞ ተወላጆች ነው ተብለው ከማናቸውም አንድ ኢትዮጵያዊ ሊያገኝ ከሚገባው ጥቅምና መብት ተሳታፊ እንዳሆኑ ተደርገው ኖረዋል። የሌሎችም ከኦሮሞ ጎሳ ውጭ ያሉ ተወላጆች እንደዚሁ በኦሮሞ ክልል ውስጥ በኢትዮጵያዊነት የሚገባቸውን መብት ተነፍገዋል። ይህንን ጎሳን መሰረት ያደረገ አስከፊና ጎሰኛ አሰራር ኢትዮጵያ እየተመላለሰ ለረጅም ጊዜ ቆይታን ያደረገው ዶክተር ያቆብ አይቶአል፤ ድርጊቱ ከደረሰባቸውም ሰዎች ሳይሰማ አልቀረም። ለምን ግን ይህንን የኢትዮጵያ መተዳደሪያ ሆኖ ዜጎችን የአድልዎ ስርዓት ሰለባ ያደረገ ህገመንግስት ጉልህ የሆነ ጉድለትና አጥፊነት ዶከተር ያቆብ ማየት እንዳቃተውና በህገመንግስቱ መሰረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደፈለገበት የኢትዮጵያ ክፍል ሄዶ ህይወቱን ሊመራ ይችላል እያለ በአሜሪካን ድምጽ የአማርኛ ክፍል እንደሚነግረን አይገባኝም።
ለዚህም ነው ከሃያ ሁለት ዓመት ጥፋት በኋላ እንኳን ዶክተር ያቆብ ይህንን የጎሳ ፌዴራሊዝምን መሰረት አድርጎ የተጻፈውን የዛሬውን ህገመንግስት ላለመንካት፤ ለላመተቸት የፈለገው። ለነገሩ ያቆብ የሚያምንበትን የጎሳ ፌዴራሊዝምን ፍልስፍና እንዴትስ አድርጎ ይቃወም? እነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፤ እንደዚሁም ከአንድነት ፓርቲ ወጥተው ዛሬ የሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱት ወጣቶች የአንድነት ፓርቲ የጎሳን ፖለቲካ ከሚያራምደው የመድረክ ድርጅት አባል መሆን አይገባውም
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ብለው በመቃወም፤ የአንድነት ፓርቲም በዚህ ጉዳይ ላይ ስብሰባ አድርጎ እንዲነጋገሩበትና እንዲከራከሩበት ሲጠይቁ፤ ዛሬ በአመራር ላይ ያሉት የአንድነት ፓርቲ መሪዎችና ዶ/ር ያቆብ ኃይለማርያም ይህንን አሻፈረን ብለውና ሽንጣቸውን ገትረው የጎሰኞች ስብስብ የሆነውን መድረክ የተባለውን ዛሬ ኢትዮጵያ በምትደዳደርበት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት ተከታይ ቡድን ተቀላቅለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰራበት ያለው በቡድን መብት ላይ የተመሰረተ ህገመንግስት ዛሬም በወያኔ ይሁን ነገ እነ መድረክ በለስ ቀንቶአቸው ስልጣን ቢጨብጡ የኢትዮጵያውያንን መብት ሊያረጋግጥ አይችልም፤ ዛሬ እየሆነ እንዳለው ኢትዮጵያን በጎሳ በታትኖ ከማፍረስ የዘለለ ዓላማና ግብ የለውም። ለምን ቢሉ ይህ ህገመንግስት መብት የሚሰጠው በጎሳ ማንነት ላይ ተመስርተው በተከለሉ ክልሎች ውስጥ ላሉ ያንድ ጎሳ ተወላጆች ሲሆን እነዚህ የአንድ ጎሳ ተወላጆችም ከእነሱ ክልል ውጭ ይዘውት ወደ ሌላ ክልሎች የሚወስዱት መብት የላቸውም። አማራው የጎሳ ፖለቲካ ሰለባ የሆነበትም መሰረታዊ ምክንያት ይህ ነው። የጎሳ ፌዴራሊዝም ዛሬ በወያኔ ትግሬዎች ዘመን እየተደረገ እንዳለው የኢትዮጵያዊነት ሀገራዊ ስሜትን የሚያፈርስ፤ ጥላቻንና ጥርጣሬን የሚያስፋፋና ለእርስ በርስ እልቂት የሚጋብዝ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር መቀጠል እንዳትችል የሚያደርግ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረታዊ የመብትና የእኩልነት ጥያቄዎች የማይፈታ ነው። ዛሬ መንግስታዊ ስልጣን በመቆጣጠራቸው በጎሳ ፌዴራሊዝም መርህ ላይ የተመሰረተው ህገ መንግስት አተገባበር ችግር የማይፈጥርባቸው የምርጡ የትግራይ ተወላጆችና ለእንደሱ በባርነት አድረው የሚያገለግሏቸው ጥቂት የሌሎች ጎሳ ተወላጆች ብቻ ናቸው።
አንድ በኢትዮጵያ ስላለው የጎሳ ፌዴራሊዝም ጥናት ያደረገች ሎቪስ አለን የምትባል የኖርዌይ ተወላጅ  እንዳመለከተችው የኢትዮጵያን በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም በዓለም ውስጥ ከሚገኙ የፌዴራል ስርዓቶች ሁሉ የተለየ የሚያደርገው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዜግነት መብት የሚቀዳጀው በጎሳ ማንነቱ አማካይነት ብቻ መሆኑና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዜግነት ከጎሳ አባልነት ውጭ ሊታሰብ ያለመቻሉ ሁኔታ ነው።ዛሬ አማራው ከተወለደበት፤ አድጎና ከብዶ፤ ልጆች አፍርቶ ከሚኖርበት የደቡብ፤ የኦሮሞ፤ የሶማሊ፤ የቢኒሻንጉል ወዘተ ክልሎች እንዲወጣ የተደረገው የጎሳ ፌዲራሊዝም በደነገገው ኢ-ዲሞክራሲያዊና ፋሽስታዊ የሆነ ህገ መንግስት ምክንያት ነው። ስለዚህ ስለ አማሮችም፤ ሰለ አፋሮችም፤ የጋምቤላ ተወላጆችም፤ ወዘተ መፈናቀል ሆነ በተደጋጋሚ ባለፉት ሃያ ሁሉት ዓመታት ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለተካሂዱት በርካታ አውዳሚ የጎሳ ግጭቶችና ፍጅቶች፤ የህዝብ መፈናቀል፤ ስደትና መከራ መንስኤ ስንነጋገር ክርክራችንም ሆነ ውይይታችን ትኩረቱን ማሳረፍ ያለበት ጥላቻና ግጭትን አራጋቢ የሆነው የጎሳ ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እንድትቀጥል የሚያደርግ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ መሆን አለበት የሚል አስተያየት አለኝ። ዛሬ የፖለቲካውን መድረክ ያጣበቡት በሀገርም ሆነ በውጭ ያሉት የወያኔ መንግስት ተቃዋሚዎች (የመድረክ ቡድን አባሎች፤ አዲሱና በቅርቡ ራሱን ያስተዋወቀው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር፤ በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦነግ ክንፍ፤ ወዘተ) እንዲሁም ግንቦት ሰባትን የመሳሰሉት አዲሱን ኦነግንና የኦጋዴን ነጻ አውጭዎችን እያጀቡ በየመድረኩ ብቅ የሚሉት ጭምር የሚያራምዱትና የሚደግፉት የጎሳ ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እንድትቀጥል የማያስችል፤ ኢትዮጵያን የሚበትንና የእርስ በርስ ጦርነት አውድማ፤ የተፋፋመ ጅምላ የጎሳ ፍጅት የሚዳርግ መሆኑን ገደምም ጠመም ሳላደርግ መግለጽ እፈልጋለሁኝ። አስገራሚው ነገር ኢሳት የተሰኘው ሬድዮና ቲሌቪዥን የጎሳ ፌዴራሊዝም አራማጅ ለሆነው ለአዲሱ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ወደ አንድ ጎን ያደላ ሽፋን ሲሰጥ (ኢሳት ከቀድሞው የኢሰፓ ካድሬ ዛሬ ደግሞ የአዲሱ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አንዱ መሪ ከሆነው ከዶክተር በያን ሁሴን ኦሶባ፤ ጋር ያደረገውን ሰፊና ተከታታይ ቃለመጠይቅ ያሰተውሏል) እንደ “ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም” ይህንን አዲሱ የኦነግ ክፍል ያነገበውንና በወያኔ የሃያ ሁለት ዓመታት አስተዳደር ስራ ላይ ውሎ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እያፈረሰ ያለውን የጎሳ ፌዴራሊዝም የሚቃወም አመለካከት ለማስተናግድ ግን ፈቃደኛ አልሆነም። በዚህም ሳቢያ የእሳት ባለቤት የሆነው የግንቦት ሰባት ድርጀት አሻራ ከምንጊዜውም በላይ ጉልህ ሆኖአል።
ከላይ እንደ ገለጽነው ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚባሉትን የወል ስብስቦችን መሰረት ያደረገው የዛሬው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መብት የሚሰጠው ለእነዚህ ስብስቦች እንጂ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አይደለም። በማናቸውም ዲሞክራሲያዊ ሀገር እንደሚታየው ሉዓላዊነት የሚሰርጸው ነጻ ከሆነው እያንዳንዱ ዜጋ ነጻ ምርጫ እንጂ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከሚባሉ የማይጨበጡ ስብስቦች አይደለም።በዲሞክራቲክ መንግስታዊ ስርዓቶች ህገ መንግስት ውስጥ ተገልጾ የምናነበው ሉአላዊነት የሚሰርጸው ከእያንዳንዱ ግለሰብ ነጻ ፈቃድ ሲሆን እያንዳንዱ ነጻ ያንድ ሀገር ዜጋ ድጋፉን የሚሰጣቸው የህዝብ ተወካዮች ፓርላማ ገብተው በዚያ በተሰጣቸው የእያንዳንዱ ዜጋ ህዝባዊ ውክልና መሰረት ዲሞክራሲያዊ የህዝብ መንግስት ያቋቁማሉ። ይህም በእያንዳንዱ ዜጋ ነጻ ፈቃድ ላይ ተመስርቶ የተቋቋመ መንግስት ተጠሪነቱ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለሚባሉ የማይዳሰሱና የማይጨበጡ የወል ስብስቦች ሳይሆን ለእያንዳንዱ የመምረጥ መብት ላላው ነጻ ዜጋ ይሆናል። በዚህ ዓይነት የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት የሚሰርጸው ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከሚባሉ የወል ስብስቦች ሳይሆን ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዜጋ ነጻ ፈቃድ ይሆናል። የአንድ ሀገር ዜጎች በዚህ ዓይነት በየግላቸው በፈቃዳቸው በሚሰጡት ህዝባዊ ውክልና የሚመሰረት መንግስት ተጠሪነቱ ለዚያ ለመረጠው ህዝብ ስለሚሆን ይህ ተጠሪነቱ ለህዝብ የሆነ መንግስት የመረጠውን፤ በስሙም መንግስት እንዲመሰርት የወከለውን ህዝብ በደንብ ሳያገለግል ሲቀር ይህ ነጻ ህዝብ በምርጫ ድምጹን በመንፈግና ውክልናውን በማንሳት ይህንን መንግስት በሌላ የተሻለ መንግስት ሊተካ ይችላል። የዲሞክራቲክ ሀገሮች ለህዝቦቻቸው ልማትና እድገትን፤ ሰላምና ደህንነትን፤ የተረጋጋ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ህይወትን ያረጋገጡት በዚህ ዓይነት ከእያንዳንዱ ነጻ የሆነ ዜጋ ፈቃድና ምርጫ በተቋቋሙ መንግስታት እንጂ ስልጣን-ወዳድ ልሂቃን በብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሚባሉ የወል ስብስቦች ስም የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ወኪል ነን ብለው በህዝብ ላይ በሚጭኑት፤ ከፋፋይና የማያባራ የጥላቻና የእልቂት መንሥኤ ሊሆን በሚችል የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት አይደለም።
በዚህ ጸሃፊ እምነት ተማርኩ ነኝ ባዩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ክፍል ላለፉት ሃምሳና ስልሳ ዓመታት ጥናትና ምርምር ላይ ያልተመሰረቱ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረታዊ ችግሮች ያልቃኙ ዝም ብለው በመፈክር ደረጃ የሚገፉ ሃሳቦችን (የብሄረሰብ መብት፤ የመደብ ትግል፤ ወዘተ) በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ላይ በመጫን የኢትዮጵያን ህብረተሰብ እንደ ቤተ-ሙከራ (ላቦራቶሪ) የአውዳሚ ሃሳቦችና ድርጊቶች ሰለባ አድርጎአል። ይህ የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊም በለጋ የወጣትነት እድሜው ለሶስት ዓመታት ኢህአፓን በጀሌነት ተቀላቅሎ ለዚህ በእንጭጭ አይምሮ ለተቀፈቀፈ አፍራሽና አውዳሚ ሃሳብ ተግባራዊነት የበኩሉን የጥፋት አስተዋጽዖ አድርጐአል። በዚህ ትውልዳችን በፈጸመው ጥፋት ከመኩራራት ይልቅ በተደጋጋሚ በአደባባይ ይቅርታም ጠይቆአል። ዳሩ ግን ይህ ያልተመረመሩና ጥናት ያልተደረገባቸውን ጎጂ የሆኑ የፖለቲካ ሃሳቦችን በማህበረሰባችን
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
ላይ የመጫኑ አዝማሚያ ዛሬም ቀጥሎአል።፡ ቢያንስ በውጭ ሀገር በነጻው ዓለም የምንኖረው ኢትዮጵያውያን እንዲሁ በጀሌነት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያራግቧቸውን የፖለቲካ መፈክሮች ተቀባይና እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋቢ ደጋፊዎች ከመሆናችን በፊት የጎሳ ፌዴራሊዝም የሚባለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ፋይዳው ምን ይመስላል?፤ የጎሳ ፌዴራሊዝም አራማጅ የነበሩ የቀድሞዋን ዩጎዝላቪያና የሶቬዬት ህብረት የመሳሰሉት ሀገሮች መጨረሻ ምን ሆነ? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። በጎሳ ማንነት ላይ የተደራጀ አግላይ ፖለቲካ አግላይነትን ከሚጻረረው የዲሞክራሲ ጽንሰ-ሃሳብ ጋር ያለውን ርቀት መገንዘብ ያስፈልጋል። የጎሳ ፌዴራሊዝም ከዲሞክራሲ ጋር ምንም ግኑኝነት የለውም። እኔ የጎሳ ፌዴራሊዝም የዲሞክራሲም መገለጫ አይደለም ብዬ እከራከራለሁኝ እሞግታልሁኝ። እስቲ በዚህ በጎሳ ፌዴራሊዝም ዙሪያ የዚህ አራማጅ የሆኑት በርካታ በኢትዮጵያም ሆነ (የመድረክ አባሎችን ያጠቀልላል) ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ በጎሳ ማንነት ላይ በተመሰረተ የፖለቲካ ስርዓት የሚያምኑ ወገኞች በአደባባይ ክርክር ያድርጉበት። የጎሳ ፌዴራሊዝም እኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዬ ለምጠራው፤ የጎሳ ፌዴራሊዝም ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ብለው ለሚጠሯቸው ኢትዮጵያውያን ለምን እንደሚበጅ ወይም እንደማይበጅ ቢያንስ ከሃያ ሁሉት ዓመታት የጋራ ጥፋት በኋላ ውይይትና ክርክር ሊደረግበት ይገባል ብዬ እሞግታለሁኝ፤ እከራከራለሁኝ። ይህንንም ክርክር እነዚህ የጎሳ ፌዴራሊዝም አራማጆች እና ደጋፊዎች በብልጠት እንደሚያደርጉት ወደፊት የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት ሲሆን ይወስነዋል የሚለውን ማታለያቸውን ትተው ዛሬ ገና እነሱ ወደ ስልጣን ሳይወጡና የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ወያኔ ትግሬዎች የጭቆና ቀንበር ሳይጭኑበት በአደባባይ ሃሳባቸውን ህዝብ በተሰበሰበበት መድረክ ወጥተው ለከራከሩበት ይገባል። ይህ በየመድረኩ ለፖለቲካ ተቃዋሚዎች የሚያጨበጭበው በስደትም ሆነ በሀገር ቤት የሚኖር ህዝብ ቢያንስ አማራጭ እንሰጥሃለን ብለው ድጋፉን የሚሹትን ተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች ስለ ትልማቸውና አንግበውት እንታገልለታለን ስለሚሉት የጎሳ ፌዴራሊዝምን መሰል አጀንዳ ጥያቄዎችን መጠየቅ አለበት። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል የሞኞች ብሂል ወያኔን የተቃወመ ሁሉ ወዳጄ ነው አማራጭ ይሆነኛል ማለትን ማቆም አለበት። የጎሳ ፌዴራሊዝም  የአንድ የባለ-ብዙ ጎሳዎችና እምነቶች ባለቤት ለሆነች ኢትዮጵያን ለመሰለች ሀገር አይረባትም ብዬ በጽኑ ከሚያያምኑት ሰዎች መካከል ነኝ። በዚህም ጉዳይ የመድረክን አባሎች ከመሳሰሉት የጎሳ ፌዴራሊዝምን ጠቃሚነት ከሚሰብኩ ወገኖች ጋር በሃሳብ በአደባባይ በአካልም ሆነ በጽሁፍ ወጥተን፤ ጸሃይ እየሞቀን፤ ሰው እያያን እንድንከራከርበት በትህትና እጠይቃለሁኝ።
በዚህ በጎሳ ፌዴራሊዝም ጉዳይ ላይ ህዝብ የተሳተፈበት ግልጽ ክርክር በአደባባይ እንዲካሄድ ቢያንስ በነጻው የምእራቡ ዓለም የሚኖረውና በየጊዜው ስብሰባ እየተጠራ ስለሀገሩ ጉዳይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ነን የሚሉ ወገኖችን የሚያዳምጠውና የሚደግፈው ኢትዮጵያዊ መጠየቅ ይኖርበታል። ይህ ግልጽ የሆነ ክርክር እንዳይካሄድ ባገር ቤትም ሆነ በውጭው ሀገር አልተቻለም። ያ የኢትዮጵያ ተማሪዎችና የግራው እንቅስቃሴ ውላጅ የሆነው ጸረ-ምሁራዊ ልማድ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል። የተለያዩ አመለካከት ያላቸውን ወገኖች ባንድ መድረክ ላይ አቅርቦ ሃሳባቸውን ለህዝብ እንዲያቀርቡ ማድረግ እስካሁን ተቀባይነትን አላገኝም። ከዚያ ይልቅ በደጋፊዎች የታጀበ፤ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ነን የሚሉ ወገኞች የራሳቸውን ሀሳብ (በሞኖሎግ መልክ) ብቻ ተናግረው የሚሄዱበት፤ የእነሱን ሃሳብ የሚቃወሙ ድምጾች በስልት የሚታፈኑበት ከዚያው ከግራው ፖለቲካ የቀጠለ አሰራር ቀጥሏል። በዚህ በምእራቡ ዓለም በስደት ያለነው ኢትዮጵያውያን እንኩዋን በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ እየተገኘን ያንድን ወገን ድምጽ እየሰማን ከማጨብጨብ በስተቀር የፖለቲካ ድርጅቶች ለሀገርና ለህዝብ ይጠቅማሉ ብለው የሚያራምዿቸው ሃሳቦች በአደባባይ ክርክር እንዲደረግባቸው ተጽዕኖ ማድረግ አልቻልንም። በቅርቡ የቀድሞው የወያኔ ካድሬ፤ የዛሬው የግንቦት ሰባት ዋና ጸሀፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ዋሽንግተን ላይ ሆኖ ካለአንዳች ሃፍረትና ይሉኝታ የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል በኤርትራ ህዝብና መንግስት እየተረዳ ኢትዮጵያን ነጻ ሊያወጣ እንደሚችል ተረት ሲነግረንና ሊያሳምነን ሲሞክር እዚያ ተሰብስበው የሚያዳምጡትና የሚያጨበጭቡለት ወገኖች ክቅርብ ታሪካችን ምን ተማሩ? ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል። አንዳርጋቸው እንደማናቸውም ዓይነት ህሊና እንደሌለው ሳይካትሪስቶች ሳይኮፓቲክ ፐርሶናሊቲ እንደምንለው መዋሸት፤ መቅጠፍ ለህሊናው አይከብደውም፤ ህሊናውን አይቆረቁረውም።
አሳዛኙ ነገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትላንት መንግስቱ ኃይለማርያምን፤ መለስ ዜናዊን ዛሬ ደግሞ አንዳርጋቸውን የመሳሰሉ ሳይኮፓቲክ (ህሊናቢስ የሆነ ተክለሰውነት ያለው፤ መቅጠፍ መዋሸት የማይሰቀጥጠው፤ ሰው ማለት ነው) ግለሰቦች መፈነጫነት ምቹ ሜዳ መሆኑ ነው። ይህ ኢትዮጵያውያን ልናጠናው የሚገባን አሳሳቢ ብሄራዊ ችግር ነው። የዛሬ ሃያ ሁለት ዓመት ከወያኔ ትግሬዎች ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን በመቆጣጠር እንደ ማናቸውም የወራሪ ጦር የኢትዮጵያን ግማሽ ሚሊዮን ጦር ከነቤተሰቡ የበተነውን፤ ትጥቃቸውን ፈተው እጃቸውን በሰላም የሰጡ አራት ሽህ የኢትዮጵያ መኮንኖችን ካለአንዳች ርህራሄ የፈጀውን ሻቢያን፤ የወርቅ ጥርስ ሳይቀር ነቅሎ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ከኤርትራ ያባረረውን ሻቢያን፤ እስከ ባድሜ ጦርነት ድረስ ከወያኔ ትግሬዎች መንግስት ጋር ሆኖ የኢትዮጵያን ሃብት እንደ ጠላት ንብረት ሲዘርፍና ወደ ኤርትራ ሲያሸሽ የነበረውን ሻቢያን፤ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አውታሮችን ተቆጣጥሮ ሲመዘብር የነበረውን ሻቢያን፤ በቅንጅት ድል ማግስት ኬንያ (ናይሮቢ) እና ሆላንድ (ዩትሬክት ከተማ ላይ) ከእነ ኦነግ ጋር በመመሳጠር አላያንስ ፎር ዲሞክራሲ (ኤፍዲ) በሚል ስም የኢትዮጵያን ህዝብ የምርጫ ውጤት ለመንጠቅ የሞከረውን ሻቢያን እኩይ ድርጊት የኢትዮጵያ ህዝብ ፈጽሞ አይረሳም። መርሳትም የለበትም።
ትላንትም ዛሬም የኢትዮጵያን ህዝብ ጠላቶች በጎሳ እያደራጀ የሚያሰማራው ሻቢያ፤ ዛሬ በወያኔ ግፍና ጎሰኛ አገዛዝ ተማረው ወደ ኤርትራ የሚገቡትን የኢትዮጵያ ወታደሮች በጎሳ እየለያየ (አማራ፤ ኦሮሞ፤ አፋር፤ ሶማሊ፤ ሲዳማ ወዘተ እያለ) የሚከፋፍለው ሻቢያ ለኢትዯጵያ በጎ ነገር ያስባል ብለው የግንቦት ሰባት መሪ ካድሬዎች ሊያሞኙን ሲሞክሩ ምን ያህል የኢትዮጵያውያንን የማሰብ ችሎታ ዝቅ አድርገው እንዳዩት ያሳየኛል። የግንቦት ሰባት መሪ ካድሬዎች (አንዳርጋቸውም ሆነ ብርሃኑ ነጋ፤ ወዘተ) እነሱ በማይቆጣጠሯቸው የህዝብ መድረክ ላይ ቀርበው ሌሎች የእነሱን ሃሳብ ከሚቃወሙ ወገኖች ጋር መድረክ በመጋራት የያዙትን አቋም ለማቅረብ ድፍረቱም ሆነ ችሎታው እንደሌላቸው አውቃለሁኝ። ነገር ግን ዛሬ በሞኖፓል በሚቆጣጠሩት የኢሳት ሬድዮና ቴሌቭዥን አማካይነት በአእምሮ ችሎታቸው ዝቅ ያሉ ወገኖችን ሊያሞኙ ይችሉ ይሆናል። እንኳን ሻቢያ ይቅርና ኤርትራ የሚባለውን የጣሊያን ቅኝ ገዢዎች የፈጠሩትን የባርነት መገለጫ የሆነውን አዲስ ጸረ-ኢትዮጵያ ማንነት የተላበሱ ወገኖች ምንጊዜም ለኢትዮጵያ በጎ እንደማያስቡና እንደማይተኙላት አንባቢ ልብ እንዲል ይህ ጸሀፊ አበክሮ ያሳስባል። አንድ ስለ ኤርትራ ብሄረተኞች ሰፊ ጥናት ያደረገ ኢትዮጵያዊ የታሪክ ምሁር ባንድ ወቅት እንዳለው “ውሃ ጠማኝ ተብሎ መርዝ አይጠጣም”።እንደዚሁም ዛሬ በወያኔ ትግሬዎች ጎሰኛ ስርዓት የተበሳጨ የጠላቴ ጠላት በሚል የሞኝ ብሂል ምንጊዜም ጠላትነቱን ለማይተወው የሻቢያ ኤርትራ ልቡን ሊሰጥ አይገባም። ወደፊት ይህንን የኤርትራን ማንነትና ጉዳይ አስመልክቶ ሌላ መጣጥፍ ለማቅረብ አስባለሁኝ። በዚህ ጽሁፌ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱት ግለሰቦች ወይም የድርጅት ወኪሎች፤ መሪዎች ያነሳኋቸውን የተቃውሞ ነጥቦች አስመልክቶ የሚኖራቸውን አስተያየት ለማስተናገድ፤ አስፈላጊም ከሆነ በማንኛውም መድረክ ላይ ቀርቤ ለመከራከር ዝግጁ መሆኔን በትህትና አሳውቃለሁኝ።
አሰፋ ነጋሽ *